ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 481፦
፲፫. ኣንድ ኣንባቢ ኮምፕዩተር፣ የእጅ ስልክና የመሳሰሉት ላይ የሚመለከተው የግዕዝ ዩኒኮድ ፊደል መሣሪያው ላይ በኣለው ፊደል ነው። ፊደሉ ትክክል ከኣልሆነ ትክክል ኣለመሆኑንንም ላይረዳ ይችላል። ለምሳሌ ያህል የ"ጨ" ቀለበቶች ሁለት ናቸው ሲባልና ቢያነብ ባለ ሁለት ቀለበቶች ትክክለኛ ፊደል ከሌለው ፊደሉን የሚያነበው ሦስት ቀለበቶች በኣሉት የተሳሳተ ፊደል ነው። የዶክተሩ የግዕዝ ቁምፊ ከኣሥር ዓመታት በላይ እዚህ የዩናይትድ እስቴትስ ፓተንትና ማመልከቻው ውስጥ ኣሉ። [https://patentimages.storage.googleapis.com/fb/53/db/a5c1c13fa86e20/US20090179778A1.pdf] ፲፬. ኣንድ በቅርቡ የተለቀቀ ቁምፊ ውስጥ የዓይኑ "ዓ" ፊደል መልክ ወደ ኣረቡ ዘጠኝ (9) የቀረበ ሲሆን የሌላው "ፃ" መስመሩ የኣለው በ"ዓ" ክብ ውስጥ ነው። ፲፭. ዶክተር ኣበራ ሞላ ከዓለም ፊደል ሠሪዎች ኣንዱ ናቸው። [https://web.archive.org/web/20190309221057/http://www.e-engraving.com/fonts/Font_Designers.htm] ፲፮. በማተሚያ ቤቶች ከታተሙ የግዕዝ ቁምፊዎች የሚከተሉት ይገኙበታል። [https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8A%9B_%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%8A%E1%8B%9D%E1%8A%9B_%E1%88%98%E1%8B%9D%E1%8C%88%E1%89%A0_%E1%89%83%E1%88%8B%E1%89%B5_1833]
 
፲፯. በተሳሳተ ፊደል የተጻፈ በመሆኑ ኣስተማማኝ የኣልሆነ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። [https://www.cdc.gov/anthrax/pdf/evergreen-pdfs/anthrax-evergreen-content-amharic-508.pdf] ከእዚህ ጽሑፍ ኣንድ ሁለት ኣንቀጾች ኮፒ ተደርገው http://www.freetyping.geezedit.com ገጽ ላይ ቢለጠፉ ችግሮቹን መመልከት ይቻላል። ፲፰. ኣንድ ቆንጆ የቁም ፊደል አጣጣል እዚህ ኣለ። [https://www.youtube.com/watch?v=L3iXWW9eJ1Y] ፲፱. በግዕዝ ፊደል ወግ ስምንተኛው ፊደል የሚቀርበው ግዕዙ ወይም ራብዑ ላይ መስመር በመጨመር ነው ። "ፏ" የተሠራው መስመሩን "ፋ" ኣንገት ላይ በመጨመር ነው። በኣሁኑ ጊዜ ብዙዎቹ ቅጣዩን በስሕተት ከታች ሲያቀርቡ ኣንዱ በቅርቡ "ፍ" ላይ ኣድርጎታል። መሳሳታቸውን ከቆዩ ጽሑፎች ውስጥ ማየት ይቻላል። እንዲህ ዓይነቶችን ስሕተቶች ስር ሳይሰዱ ማረም ከኣልተቻለ ዛሬ "ኣበበ"ን እሞታታለሁ እንጂ በ"አበበ" ከኣልሆነ ኣልጽፍም እንደሚሉት ጥቂቶቹ በኋላ በትምህርት ማቃናት ሊያስቸግር ይችላል። ፳. ኣንድ የግዕዝ ቁምፊ ቢያንስ ኣንድ ኣብሮት የኣለ የእንግሊዝኛ ፊደል ጋር መቅረብ ይኖርበታል። ስለዚህ ለሰው የሚቀርበው የላቲን ፊደልም እንደግዕዙ የፊደል ሠሪው መሆን ይገባዋል። የግዕዙና የላቲኑም ፊደላት ቅርጾች የተቀራረቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
 
፳፩. ዩኒኮድ ለፊደላቱ መደበ ሰጠ እንጂ ፊደል ኣላቀረበም። የግዕዙ ፊደል ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ላይ ከሌለ የግዕዝ ፊደል ኣይታይም። የሚታየውም እንደፊደሉ ሊለያይ ይችላል። ስለዚህ ኣንድ ተጠቃሚ የሚጠቀምበትን መሣሪያ ላይ ያለውን የፊደል ስምና መልክ ማወቅ ኣለበት። ፳፪. ኣንድ የግዕዝ ፊደል ተጠቃሚ ሁሉንም የግዕዝ ቀለሞች ቅርጾች ማወቅ ይጠበቅበታል። በኣሁኑ ጊዜ ግን ሁሉንም የዓማርኛ ቀለሞች እንኳን የማይለዩ ኣሉ።
 
===ትርጕሞች===