ከ«ንሥር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
አንድ ለውጥ 356615 ከ197.156.103.10 (ውይይት) ገለበጠ, undo (possible SPAM or VDA) m:SWMT
Tags: Replaced Undo blanking
 
መስመር፡ 7፦
 
[[መደብ:አዕዋፍ]]
ደብ የለሽ ዕይታ
የንስር አይን
‹ › Home
View web version
Thursday, May 10, 2018
tesfayenigussie21.blogspot.com at 7:31 AM
የንስር አሞራ ሚስጥራዊ ተፈጥሮ
ፍጥረታት ሁሉ ይችን ምድር ሲወርሱ የተሰጣቸው አስገራሚና ልዩ ውብ
ተፈጥሮ አላቸው፡፡ ከነዚህ የተፈጥሮ ፀጋ ከተሰጣቸው ድንቅ የምድራችን
ፍጥረታት መካከል አንዱ የንስር አሞራ ነው፡፡ የንስር አሞራ ምድቡ
ከአእዋፍ ወገን ሲሆን ተፈጥሮ የሰጠችው ድንቅ ሚስጥራዊ ተፈጥሮ ግን
የተለየ ያደርገዋል፡፡
ዛሬ በዓለማችን የሰው ልጆች አማካኝ የዕድሜ ጣሪያ 65 ዓመት
በሆነበት ዘመን ንስር አሞራ ከአዕዋፋት ዘር 70 ዓመት የመኖር ፀጋ
ተፈጥሮ የቸረችው የእድሜ ባለጸጋ ነዉ። አስገራሚው ነገር ይህ ድንቅ
አእዋፍ ዕድሜው 40 ሲሆን ተፈጥሮ ሁለት አማራጮችን በፊቱ
ታቀርብለታለች፤ እንደ አማረበት መሞት ወይም እድሜውን ወደ 70
አመት ከፍ ለማድረግ ተፈጥሮ ያዘጋጀችለትን የመከራና የስቃይ ጽዋ
ምሬት አጣፍጦ በመጎንጨት ተጨማሪ የ30 ዓመት የድል ዋንጫ
መቀዳጀት፡፡
ንስር አሞራ ከተፈለፈለ ጀምሮ 40 ዓመት ከኖረ በኋላ ምግቡን ለማደን
የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን መሬት ላይ
ማንሳት ያቅተዋል፡፡ አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው መንቁሩ
ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል፡፡
ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት፤ያ ሰማየ ሰማያትን
እየሰነጠቀ እንደ ሚግ ጀት ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል፡፡ በዚህ
ወቅት ያ ድንቅ የአእዋፍ ዘር ንስር አሞራ በሁለት ዉሳኔዎች አጣብቂኝ
ውስጥ ይወድቃል፡፡ የመጀመሪያው አማራጭ ከዚህ ካረጀ አካሉ ጋር ዝም
ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ፤ ወይም 5 ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ
ያለበት መስዋእትነትን ከፍሎ ቀሪውን 30 አመቱን መውለድ፡፡
የንስር አሞራ ከቀረበለት ሁለት ምርጫዎች ቀሪ 30 ዓመቱን መቀጠል
ከሆነ ምርጫው ተፈጥሮ ያዘጋጀችለትን የመከራ ጽዋ መጎንጨት ግድ
ይለዋል፡፡ ይኸውም ከፍተኛ ተራራ ላይ በመዉጣት የብቻውን ጎጆ ቀልሶ
ሱባኤ መግባት ይኖርበታል። በሱባኤውም ወቅት የመጀመርያ ስራዉ
የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ መጣል ነው፡፡ ይህን ካደረገ
በኋላ አዲስ መንቁር ያወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ
በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ በፆም መቆየት ግዴታው
ይሆናል፡፡
የትዕግስቱ ፍሬ በሆነው በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር
ነቃቅሎ ይጥለዋል። አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ
ይህንን አዲስ ጥፍር እንደመሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን
እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል።
በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። የሱባኤውን 5ወር በዚህ መልኩ
በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ
ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡ በእድሜው ላይ 30 አመት ጨምሮ በበረራው
ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ከፍ ብሎ እየበረረ ህይወትንና ደስታን
በውሳኔው ባተረፈው 30 አመት ሙሉ በከፍታዎች ሁሉ ላይ በድል፣
በግርማና በሞገስ ይበራል ፡፡አስደናቂው "# የንሥር " ተፈጥሮ
*★★★*
[ በዲን ዳንኤል ክብረት ]
~ ውኃ እየተጎነጩ ቀስ ብለው የሚያነቡት ጦማር ነው። እርስዎ ማንበብ
ከሰለችዎ
በጽሑፉ የሚጠቀም ሌላ ሰው ይኖራንና ሳይሰስቱ ይኽን ጦማር #
SHARE_SHARE
እንዲያደር ይመከራሉ። ገለቶማ።
# ETHIOPIA | ~ ሰሞኑን የንሥር ምስል ያለበትን [ የአብን ] ዓርማ
ያዩና የተመለከቱ
ወገኖች ዓርማውን እንደተለመደው ከዚያ ከፈረደበት 666 ጋር በማያያዝ
ግርግር ሊፈጥሩ
ሲሞክሩ ባየሁ ጊዜ እኒህን ወገኖች ስለ ንሥር በቂ ግንዛቤ ይኖራቸው
ዘንድ በአንድ ወቅት
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለ ንሥር የጻፈው አስደናቂ ጽሑፍ ትዝ አለኝና
ታነቡት ዘንድ
አምጥቼ ለጠፍኩላችሁ። ረጋ ብላችሁ ደጋግማችሁ አንብቡት። ስለ
እውነት ሁላችሁም
ከጦማሩ እንደምታተርፉ ተስፋ አደርጋለሁ።
ንሥር (eagle) እጅግ ግዙፍ ከሆኑ የአዕዋፍ ዝርያዎች አንዱ ነው፡፡
ክብደቱ እስከ 6.7
ኪሎ ሲደርስ ቁመቱ ደግሞ ከአንዱ ክንፉ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ
2 ሜትር ተኩል
ይደርሳል፡፡ በዓለም ላይ እስከ ስድሳ የሚደርሱ የንሥር ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ንሥር የትንሣኤ ሙታን፣ አርቆ
የማሰብ፣ ወደ ላይ
የመምጠቅና የመነጠቅ፣ የጥበቃና የምናኔ ተምሳሌት ሆኖ ተገልጧል፡፡
ግብጻውያን
ደግሞ የተቀበሩ ሰዎችን አጋንንት እንዳይደርሱባቸው በመቃብራቸው በር
በድንጋይ ላይ
የንሥርን ምስል ያስቀርጹ ነበር፡፡ ይጠብቃቸዋል ብለው፡፡ በግሪክ አፈ
ታሪክ የአማልክት
ንጉሥ የሚባለው ዜውስ በንሥር የሚመሰል ነበር፡፡ ጥንታውያን የአሜሪካ
ሕዝቦች እጅግ
ለሚያከብሩት የሌላ ወገን ሰው የንሥርን ላባ በመስጠት ክብራቸውንና
ፍቅራቸውን
ይገልጡ ነበር፡፡ ሞቼ የተባሉት የፔሩ ሕዝቦችም ንሥርን ያመልኩት ነበር
ይባላል፡፡ ንሥር
ይህንን ያህል ቦታ በሕዝቦች ባሕል ውስጥ ሊይዝ የቻለው በተፈጥሮው
በታደላቸው
የተለያዩ ጸጋዎች የተነሣ ነው፡፡
ንሥር ከእንስሳት ሁሉ ወደ ሰማይ በመነጠቅ የሚስተካከለው የለም፡፡
እርሱ
የሚደርስበትን የሕዋ ከፍታ የትኛውም ዓይነት ወፍ አይደርስበትም፡፡
አንዳንድ አዕዋፍ
እስከ ተወሰነ ድረስ ቢከተሉትም እንኳ እርሱ ግን ጥሏቸው ማንም
በማይደርስበት የሰማይ
ጥግ ብቻውን ይንሸራሸራል፡፡ ለዚህም ነው ጥንታውያን ሰዎች በሐሳብ
የመምጠቅ፣
ማንም ከማይደርስበት የጸጥታ ሕዋ ላይ አእምሮን የማሳረግ፣ ተራ ነገር
ማሰብና ተራ
ነገር መሥራት ከሚችሉ ደካማ ልቦች ርቆ በሉዓላዊ ሐሳብ ላይ
የመምጠቅ ምሳሌ
ያደረጉት፡፡
ታድያ ይኼ ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ከቁራዎችና፣ ከሌሊት ወፎች፣
ከጥንብ አናሣዎችና
ከድንቢጦች፣ ከተባዮችና ከነፍሳት ጋር እዚህ ምን ታደርጋለህ? በወረደ
ሐሳብ ለምን
ትመስላቸዋለህ? ውጣ ወደላይ፤ ሂድ ዐርግ፣ ምጠቅ ተመሰጥ፣ እስከ
ተወሰነ ቦታ ድረስ
ዝንብና ትንኝ፣ እስከ ተወሰነ ቦታ ድረስም ነፍሳት፣ እስከ ተወሰነም ቦታ
ድንቢጦችና
የሌሊት ወፎች፣ እስከ ተወሰነውም ቁራዎችና ጥንብ አንሣዎች ይከተሉህ
ይሆናል፡፡
ሐሳብህን ከፍ፣ አእምሮህንም ሉዓላዊ፣ ልቡናህንም ምጡቅ፣
አመለካከትህንም ከፍ ያለ
ባደረግከው ቁጥር ግን ደካሞቹ ከሥር እየቀሩ ከሚመስሉህ ከንሥሮች ጋር
ብቻ
በጸጥታው ሕዋ ላይ ትንሳፈፋለህ፡፤ሂድ ዐርግ፡፡
ንሥር እጅግ አስደናቂ የሆነ የማየት ችሎታ የተሰጠው ፍጡር ነው፡፡ እስከ
አምስት ኪሎ
ሜትር በሚደርስ ርቀት ውስጥ አንዲትን ትንሽ ጥንቸልን አንጥሮ ማየት
ይችላል፡፡ የንሥር
ዓይን ከጭንቅላቱ በተነጻጻሪ ሲታይ እጅግ ታላቅ ነው፡፡በንሥር ዓይን
ውስጥ በአንድ ሚሊ
ሜትር ስኩዌር ረቲና አንድ ሚሊዮን ለብርሃን ስሱ የሆኑ ሴሎች አሉት፡፡
ሰዎች ስንት ያለን
ይመስላችኋል? ሁለት መቶ ሺ ብቻ፡፡ የንሥር አንድ አምስተኛ ማለት ነው፡፡
ሰው ሦስቱን
መሠረታዊ ቀለሞች ብቻ ማየት ሲችል ንሥር ግን አምስቱን ማየት
ይቻለዋል፡፡
እንዲያውም ከሩቁ አንጥሮ በማየት ንሥርን የሚተካከለው እንስሳ የለም
የሚሉ
ጥናቶችም አሉ፡፡
ንሥር የሚፈልገውን ለማሰስ እስከ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ዙሪያ ይዞራል፡፡
ሲያገኝ ግን
ሌላውን ነገር ሁሉ ትቶ በሚያድነው ነገር ላይ ብቻ ያተኩራል፡፡ ‹ሁሉ
አማረሽን ገበያ
አታውጧት› የሚለውን የአማርኛ ብሂልና ‹jack of every thing
master of non›
የሚለውን የእንግሊዝኛ አባባል በደመ ነፍስ ዐውቆታል፡፡ ከትኩረቱ ፈጽሞ
ንቅንቅ የለም፡፡
ምንም ዓይነት ግርዶሽ፣ ምንም ዓይነት መሰናክል፣ ምን ዓይነት መደለያ
አያዘናጋውም፣
ተስፋም አያስቆርጠውም፡፡ የዚያን የአደኑን ነገር በንቃትና በትጋት እስከ
መጨረሻ
ይከታተለዋል፡፡ እንዲሁ አይወረወርም፤ ጊዜና ሁኔታ ይመርጣል፡፡ ጊዜና
ሁኔታ ሲገጥሙለት
ትኩረቱን ሰብስቦ በመወርወር ታዳኙን ይሞጨልፈዋል፡፡
ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ደጋግመህ አስብ፤ ለመወሰን ጊዜ ውሰድ፤ ዙር
ተዟዟር፡፡ ልፋ
ድከም፤ አንድ ጊዜ ለመቁረጥ ሺ ጊዜ ለካ፡፡ በመጨረሻም ዒላማህን ለይ፡፡
አስተካክል፡፡
ትኩረትህንም በዒላማህ ላይ ብቻ አድርግ፤ ምንም ዓይነት ማታለያ፣ ምንም
ዓይነት
መደለያ፣ ምንም ዓይነት ማሰናከያ፣ ምንም ዓይነት ፈተና፣ ምንም ዓይነት
ተስፋ መቁረጥ
ከዓላማህ ሊያግድህ አይገባም፡፡ ማየትና ማሰብ ያለብህ ሁሉም ሊያየውና
ሊያስበው
የሚችለውን ተራ ነገር አይደለም፡፡ ሊታይ የማይችለውን ለማየት፣ ሊለይ
የማይችለውን
ለመለየት፣ ሊተኮርበት ያልቻለውን ለማተኮር ጣር፡፡ ዒላማህን ካገኘህ
አትልቀቅ፤ ጊዜና
ሁኔታ አመቻችና ዒላማህ ላይ ተወርወር፡፡ ያንተ ከመሆን ማንም
አያግደውም፡፡
ንሥር በምንም ዓይነት የሞቱ እንስሳትን አይበላም፡፡ እርሱ እቴ፡፡ በሕይወት
ያለውን እንስሳ
የገባበት አሳድዶ፣ ከተደበቀበት ጠብቆ አድኖ ይበላዋል እንጂ እርሱ እንደ
ቁራና ጥንብ
አንሣ የሞተ ላይ አያንዣብብም፡፡ እንደ አራዳ ልጆች ከተበላ ዕቁብ ጋር
አይጨቃጨቅም፡፡
ቀላል ነገር ቢያጣ በግና ፍየልም ቢሆን ተወርውሮ አድኖ፣ ከዐለት ላይ
ፈጥፍጦ እንደ
አጥንት ወዳጅ አበሻ ቅልጥም ሰብሮ ይበላል እንጂ የሞተ ጥንብ
ሲያልፍም አይነካው፡፡
ያቺን ከባዷንና በድንጋይ የተሸፈነችውን ዔሊ እንኳን ከዐለት ስባሪ ላይ
ከስክሶ ድንጋይዋን
አራግፎ ይበላታል እንጂ እንደ አበሻ ማን እንዳረደው ያላወቀውን ነገር
አይበላም፡፡
ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ልቡናህንና ኅሊናህን፣ አእምሮህንና መንፈስህን
ምን
እንደምትመግባቸው አስብ፡፡ የሞተ፣ የማይሠራ፣ የተበላሸ፣ ጊዜው
ያለፈበት፣ ቁራና ጥንብ
አንሣ የሚጫወቱበትን አትመግበው፡፡ ፊልምና ፕሮፓጋንዳ፣ ዋዛና ፈዛዛ፣
የወረዱና የበከቱ
አስተሳሰቦችን አትመግበው፡፡ ከተፋና ለብለብ ሐሳቦችን አትጋተው፡፡ ይልቅ
አድን፣ ድከም፣
ልፋ፣ ተሟገት፣ ተመራመር፣ እንደ ዔሊ ድንጋይ የከበደውን አስተሳሰብ
ገልብጠህ፣
ፈንክተህ ተመገብ፤ ድካምና፣ ጽሞና፤ ማሰብና መመርመር የሚሻውን
ንባብ ውደድ፤
ሳይለፉና ሳይደክሙ እንደ ሞተ እንስሳ ሥጋ የትም የሚገኘውን ነገር
ሳይሆን ጥረትና
ግረት የሚሻውን፤ ላብ ጠብ የሚያደርገውን ሞያና እንጀራ ፈልግ፡፡
ንሥር ዐውሎ ይወዳል፡፡ ሰማዩ ሲጠቁርና ደመናው ሲሰበሰብ ወጀቡም
ሲያይል ሌሎች
አዕዋፍ በዐለት ንቃቃትና በጫካው ችፍርግ ውስጥ ይደበቃሉ፤ በቤት ታዛ
ሥርም
ይሠወራሉ፡፡ ንሥር ግን ደስ ይለዋል፡፡ ወጀቡና ዐውሎው ሲጀምር ንሥር
የንፋሱን ኃይል
በመሞገት የራሱን ጥንካሬ ይለካበታል፡፡ የነፋሱን አቅጣጫ በመከተልም
ይበራል፡፡ ራሱን
ወደ ላይ ለማምጠቅና የከፍታውን ጫፍ ለመጨበጥ ይጠቀምበታል፡፡
በዚያ ጠንካራ
ነፋስ ትከሻ ላይ ሲጫን ነው ንሥር ዕረፍት የሚወስደው፡፡ ክንፉን ብቻ
ዘርግቶ በዕረፍት
ስሜት ከደመና በላይ የኃያሉን ዐውሎ ዐቅም ተጠቅሞ ይንሸራሸራል፡፡
አንተንም ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- መከራንና ፈተናን አትፍራ፤ በወጀብና
በዐውሎ ነፋስ
ውስጥም ቢሆን መንገድ አለና፡፡ መከራውንና ችግሩን፤ ፈተናውንና
ግብግቡን የአዳዲስ
ሐሳቦች መነሻ፤ የጥንካሬህ መለኪያ፤ ዐቅምህን የምትሰበስብበት
አጋጣሚ፣ ወደላይ
የምትመጥቅበትና ከችግር ደመናዎች በላይ የምትንሳፈፍበት ዕድል
አድርገው፡፡ እንደ
ሌሎች ወፎች ከመከራው አትሽሽ፤ ከችግሩም አትደበቅ፤ መከራን
ለበረከት ተጠቀምበት፡፡
ንሥር ሳይፈትን አያምንም፤ አይተማመንምም፡፡ ሴቷ ንሥር ባል ማግባት
ስትፈልግ አንድ
እንጨት ታነሣና ወንዱ እየተከተላት ወደ ላይ ትመጥቃለች፡፡ እስከ ሰማይ
ጥግ ከደረሰች
በኋላም ያንን እንጨት ትለቀዋለች፡፡ ያን ጊዜ ወንዱ እንጨቱ መሬት
ከመድረሱ በፊት
በፍጥነት በመወርወር መያዝና ለሴቷ መልሶ ማምጣት ይጠበቅበታል፡፡
ሴቷም እንጨቱን
ተቀብላ እንደገና ወደ ቀጣዩ ከፍታ ትመጥቅና እንጨቱን መልሳ
ትጥለዋለች፡፡ አሁንም
ወንዱ ንሥር ከእንጨቱ የውድቀት ፍጥነት ቀድሞ ያንን እንጨት በመያዝ
ለሴቷ ማቅረብ
ይጠበቅበታል፡፡ እንዲህ ያለው ፈተና ወንዱን ለሰዓታት ያህል
ይጠብቀዋል፡፡ ከፍታው
እየጨመረ፣ እንጨቱም ይበልጥ እየተወረወረ ይሄዳል፡፡ ሴቷ ንሥር ወንዱ
ንሥር ፈጣንና
የተወረወረለትን ለመያዝ ያለውን ቆራጥነት እስክታረጋግጥ ድረስ ፈተናው
ይቀጥላል፡፡
በመጨረሻም ቆራጥና ፈጣን፣ ማንኛውም ችግር የማይበግረው መሆኑን
ስታረጋግጥ
ባልነቱን ትፈቅድለታለች፡፡
ንሥርም እንዲህ ትልሃለች፡- በግላዊ ሕይወትህ፣ በንግድህም ሆነ
በሌላው ኑሮህ
ከሰዎች ጋር መወዳጀት፣ አብሮ መሥራትና መንገድ መጀመር ያለብህ
ለዓላማቸው ምን
ያህል ጽኑና ቆራጥ፣ ትጉና አይበገሬ መሆናቸውን አረጋግጠህ መሆን
አለበት፡፡ ሳታረጋግጥ
መግባት ትርፉ ፀፀት ነው፡፡ እንኳን ሌሎችን ራስህንም ለአዲስ ተልዕኮ
ከማሠማራትህ
በፊት ፈትነው፡፡
ንሥር በሕይወቱ የሚመጡ ለውጦችን እንደመጡ በአጋጣሚ
አይቀበላቸውም፡፡
ተዘጋጅቶና ዐቅዶ እንጂ፡፡ ሴቷ ዕንቁላል የመጣያ ጊዜዋ ሲደርስ ባልና
ሚስቱ ዕንቁላል
ለመጣያ ምቹና ተስማሚ የሆነውን ቦታ ያፈላልጋሉ፡፡ ያ ቦታ ማንኛውም
ዓይነት ጠላት
የማይደርስበት፣ ከከፍታዎች ሁሉ በላይ የሆነና ከማንኛውም ዓይነት አደጋ
ራስንና ልጆችን
ለመከላከል የሚመች መሆን አለበት፡፡ ቦታው በባልና ሚስቱ ከተመረጠ
በኋላ ወንዱ ወደ
መሬት ወርዶ እሾህ ለቅሞ ወደ ተራራው ንቃቃት ያመራል፡፡ በዚያም
ይደለድለዋል፡፡
ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ ወርዶ አስፈላጊ የሆኑትን እንጨቶች ሰብስቦ ወደ
ንቃቃቱ ይመጣና
በእሾሁ ላይ ይረመርመዋል፡፡ እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ወደ ምድር ይመለስና
እሾህ ሰብስቦ
ወደ ጎጆው ያመራል፤ በእንጨቱም ላይ ይረበርበዋል፡፡ ለአራተኛ ጊዜ ወደ
መሬት
ተመልሶም ለስላሳ ሣር ያመጣና በእሾሁ ላይ ያነጥፋል፡፡ በአምስተኛ
ጉዞውም እሾህ
አምጥቶ በሣሩ ላይ ያደርጋል፡፡ በስድስተኛ ጉዞውም በእሾሁም ላይ ሣር
ይነሰንሳል፡፡
በመጨረሻውና በሰባተኛ ሥራው ላባዎቹን በመካከል ላይ ያደላድላቸዋል፡፡
በጎጆው ዙሪያ
የተደረገው እሾህም ዙሪያውን ከጠላት ያጥርለታል፡፡
እነሆ ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ምንጊዜም ለለውጥ ራስህን አዘጋጅ፡፡
ነገሮች ድንገት
እንዲደርሱብህ ዕድል አትስጣቸው፡፡ አስበህ፣ ተዘጋጅተህ፣ ወስነህ፣ ሂሳብ
ሠርተህ
እንጂ፡፡ ኑሮህ በድንገቴና በአጋጣሚ የተሞላ አይሁን፡፡ የቻልከውን መጠን
ያህል ተዘጋጅ
እንጂ፡፡ መጽሐፉስ ‹ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ› አይደል የሚለው፡፡ ለማደግ
ተዘጋጅ፣
ለመማር ተዘጋጅ፣ ለጓደኝነት ተዘጋጅ፣ ለማግባት ተዘጋጅ፣ ለመውለድ
ተዘጋጅ፣ አዲስ
ሥራ ለመሥራት ተዘጋጅ፣ ቤት ለመሥራት ተዘጋጅ፣ መኪና ለመግዛት
ተዘጋጅ፣
ለምትለውጣቸው ነገሮች ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ይኑርህ፡፡
ንሥር ትዳሩን በእኩልነት ነው የሚመራው፡፡ ወንዱ ንሥር ጎጆውን ሠርቶ
ሲጨርስ ሴቷ
ወደ ጎጆው ትገባና ዕንቁላል መጣል ትጀምራለች፡፡ ትዳርን በእኩልነት
ነው የሚመሩት፡፡
እርሷ ዕንቁላል ስትጥል እርሱ ደግሞ አካባቢውን ከጠላት ይጠብቃል፡፡
ወደ መሬት
እየተመላለሰም ምግብ ይሰበስባል፡፡ ልጆችን መመገብ፣ ማሳደግ፣ በረራ
ማለማመድ፣
ከጎጇቸው ርቀው እንዲያድኑ ማሠልጠን የሁለቱም የጋራ ኃላፊነት ነው፡፡
ድርሻ ይካፈላሉ
እንጂ አንዱ የበላይ አንዱ የበታች አይሆኑም፡፡
ስለዚህም ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ትዳር የእኩልነት ጉዞ ነው፡፡ የሥራ
ድርሻ ክፍፍል እንጂ
የበታችና የበላይ ክፍፍል አይኖረውም፡፡ ሁሉም የችሎታውንና የተፈጥሮውን
የሚያደርግበት፣ የጋራ ኃላፊነት የሚወሰድበት ቤት ነው ትዳር፡፡
ንሥር ልጆቹን ደስታንም መከራንም ያስተምራቸዋል፡፡ የንሥር ጫጩቶች
አምሮና ደኅንነቱ
ተጠብቆ በተሠራው ጎጆ ይፈለፈሉና ወላጆቻቸው እየመገቧቸው እዚያ
ጥቂት ያድጋሉ፡፡
ለዐቅመ ንሥር ሲደርሱ የምቾቱ ድልቅቂያ ያበቃና ሴቷ ንሥር ጫጩቶቹን
ከጎጆዋ
እያወጣች ዐለቱ ላይ ትጥላቸዋለች፡፡ ጫጩቶቹ በፍርሃት ይዋጡና
ተመልሰው ወደ ጎጆው
እየዘለሉ ይገባሉ፡፡ ይህ እንግዲህ ማደፋፈሪያ ነው፡፡ የማያድሩበት ቤት
አያመሻሹበትም
ይባል የለ፡፡‹ሰው እናትና አባቱን ይተዋል› የሚለው በእነርሱም መጽሐፍ
ላይ ሊኖር
ይችላል ማን ያውቃል፡፡ ለጥቂት ጊዜያት እንዲህ ታለማምዳቸውና በቀጣዩ
ጊዜ ከጎጆው
አውጥታ ወደ ዐለቱ በመጣል የጎጆውን ለስላሳውን ክፍል
ታነሣባቸዋለች፡፡ እነርሱም
እንደለመዱት ወደ ጎጆው ሮጠው ዘለው ሲገቡ እሾሁ ይቀበላቸዋል፤
ያቆስላቸዋል፣
ያደማቸዋልም፡፡ እነርሱም እንዲያ የሚወዷቸው እናትና አባታቸው ለምን
እንደሚያሰቃዩዋቸው ግራ እየገባቸው ወደ ዐለቱ ተመልሰው ይወጣሉ፡፡
ከጎጆው ውጭ በአድናቆት መቆማቸውን የምታየው እናታቸው ከዐለቱ ገፋ
ታደርጋቸውና
አየር ላይ እንዲንሳፈፉ ትለቃቸዋለች፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ አየሩን የቀዘፉት
ጫጩት
ንሥሮች በፍርሃትና በድንጋጤ ተውጠው ወደ ታች ሲወረወሩ አባታቸው
ይመጣና
ከመውደቃቸው በፊት ቀልቦ በትከሻው ተሸክሞ ወደ ዐለቱ ያወጣቸዋል፡፡
እነርሱም
በደስታ ይዋኛሉ፡፡ እናት ስትወረውር፣ አባት በአየር ላይ ሲቀልብ፣ ልጆችም
ሲወረወሩና
ሲጨነቁ፣ አባታቸው ሲቀልባቸው ሲደሰቱ ጥቂት ጊዜያት ያልፋሉ፡፡ በአካል
እየጠነከሩ፣
ከመከራውም ከደስታውም እየተማሩ፣ አካባቢውንም እየለመዱት ይሄዳሉ፡፡
በመጨረሻም
ራሳቸውን ችለው ይበራሉ፡፡ ከወላጆቹ ጋር ኖሮ የሚያረጀውን እንደ ኡመሬ
ያለዉን ቢያዩ
ኖሮ ንሥሮች ምን ይሉ ይሆን? (ኡመሬ በድሬዳዋ ከተማ በተወለደበት
በእናትና አባቱ ቤት
አድጎ ስራ ይዞ፤ አግብቶና ወልዶ ጡረታም ከወጣ በኃላ አሁንም በወላጆቹ
ቤት የሚኖር
ወዳጃችን ነዉ፡፡)
ለዚህ ነው ንሥር እንዲህ የሚለው፡- ለልጆቻችን ከልክ ያለፈ ክብካቤ
መስጠት የትም
አያደርሳቸውም፡፡ መከራውንም፣ ችግሩንም፣ ፈተናውንም፣ ትግሉንም፣
ተግዳሮቱንም
እንዲለምዱት ማድረግ አለብን፡፡ አፈር አይንካህ፣ የፈሰሰ ውኃ አታቅና፣
ማንም በክፉ
አይይህ፣ እንደ ዕንቁላል ትሰበራለህ፣ እንደ መስተዋት ትሰነጠቃለህ እያሉ
ነገ በእውኑ
ዓለም የማያገኙትን ቅንጦትና ምቾት ብቻ ማሳየቱ የትም አያድርሳቸውም፡፡
እሾሁንም፣
ዐለቱንም፣ መወርወሩንም፣ መውደቁንም፣ መታገሉንም፣ ማሸነፉንም
ይልመዱት፡፡ ነገን
በጥቂቱ ዛሬ እናሳያቸው፡፡ የሚወዱን ሰዎች ማለት የሌለ ገነት ፈጥረው
የሚከባከቡን
ማለት ብቻ አይደሉም፡፡ ሰው መሆን ለሚያጋጥመው ተግዳሮት ሁሉ ዝግጁ
እንድንሆን
የሚያደርጉን እንጂ፡፡ ቤት ሣርና ላባ ብቻ ሳይሆን እሾህም ሊኖረው
ይገባል፡፡
ንሥር ሲዳከም የት መሄድ እንዳለበት ያውቃል፡፡ ንሥር ሲዳከም ላባዎቹ
ደካሞች ይሆናሉ፡፡
እንደቀድሞው በፍጥነት እንዲበር፣ ወደ ላይም እንዲመጥቅ
አያስችሉትም፡፡ እንደ በረቱ
መዝለቅ የለ፡፡ ጉልበቱ ሲደክም፣ ላባው ሲነጫጭና የሞት ሽታ ሲሸተው፣
ጉልበቱ
ሳይከዳው በፊት ወደ አንድ ማንም ወደማይደርስበት የተራራ ጫፍ
ያመራና በንቃቃቶቹ
መካከል ጎጆ ሠርቶ ይቀመጣል፡፡ እዚያ ምግቡን አከማችቶ ያርፋል፡፡
የጽሞና ጊዜም
ይወስዳል፡፡ የተረፉትን ላባዎቹን እየነጨ መለመላውን ይቀራል፡፡ ቀስ
በቀስም አዲስ ላባ
ያበቅላል፡፡ ኃይሉም እንደ ጥንቱ ይታደሳል፡፡ ያን ጊዜ ወደ ቀድሞ ኑሮው
በአዲስ ጉልበትና
በአዲስ መንፈስ ይመለሳል፡፡
እናም ንሥር እንዲህ ይልሃል፡- ጉልበትህና መንፈስህ፣ ሐሳብህና
የማመንጨት ዐቅምህ
ሲዳከም ዝም ብለህ አትናውዝ፤ እስክትደከርትም አትሟዘዝ፡፡ ነገሮች
እንጨት እንጨት
ሲሉህ፣ የማስቲካው ቃና ሲያልቅ፣ የሸንኮራው ጣዕም ሲሟጠጥ ‹ደኅና
ነኝ› እያልክ
ራስህን አትሸንግል፡፡ ይልቅ የት መሄድ እንዳለብህ አስብ፡፡ የጽሞና ጊዜ
ውሰድ፤
ለአእምሮህ ምግብ የሚሆኑህን ሰብስብና መንን፡፡ የማሰቢያ፣ የማሰላሰያም
ጊዜ ውሰድ፡፡
የድሮ ሐሳቦችህን እንደ ላባዎቹ ነቃቅል፡፡ በቃኝ በል፡፡ ጊዜ ወስደህ
ካሰብክ፣ ካነበብክ፣
ከመረመርክ፣ ካሰላሰልክ፣ ካወጣህና ካወረድክ አዳዲስ መንገዶች፣
አዳዲስ ሐሳቦች፣
አዳዲስ ነገሮች፣ አዳዲስ አመለካከቶችን ማብቀል ትችላለህ፡፡ ያን ጊዜ
በአዲስ ጉልበት
እንደገና ለመመለስ ትበቃለህ፡፡
እንደ ሰው ብትፈጠርም እንደ ንሥር ኑር፡፡
የአእዋፍ ንጉሥ በመባል የሚታወቅ የወፍ ዘር ነው ።ታላላቅ ነገስታት
ንሥርን ለተለያዩ
ነገሮች መግለጫነት እንደ ምሳሌ ተጠቅመዋል። ለነጻነት፣ ለሥልጣን፣
ለግርማና
ለመሳሰሉት። ከአዋፋት ዘር ለ70 ዓመት የህይወት ዘመን መቆየት
የሚችል ነዉ። ንሥር
አሞራ70 ዓመት እድሜዉን ለመኖር ወይም ለመጠበቅ በ40ኛ ዓመቱ ላይ
ከፍተኛ
መስዋዕትነት የሚጠይቅ ውሳኔ ይወስናል። የንሥር አሞራ የእግር ጥፍር
በአግባቡ
መሥራት የሚችለዉ ለ40 ዓመት ብቻ ነዉ። ንሥር አሞራ ከተፈለፈለ
ጀምሮ 40 ዓመት
ከኖረ በኋላ በሰውነት ክፍሉ ላይ በሚታየዉ ለውጥ የተነሳ ፤ የአፍ
መንቁሩ(peak) ፤
የእግሩ ጥፍርና (talon) ላባዉ እንደበፊቱ ሊያገለግሉት አይችሉም።
የእግሩ ጥፍር
ደካማ በመሆን አደኑን ወይም ምግቡን አይዝለትም ፤ረጅምና ስል መንቁሩ
ይታጠፍና
ምግቡን አይዘነጥልለትም፤ ላባዉ በሰዉነቱ ይለጠፍና ክብደት ስለሚፈጥር
እንደልቡ
አይበርም ። በዚህ ወቅት ንሥር አሞራ በሁለት ውሳኔዎች ላይ ይወድቃል።
ዝምብሎ
በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ወይም 5 ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ
ያለበት
መሰዋዕትነትን በመክፈል ቀሪ 30 ዓመቱን እንደ ወጣት ንሥር መኖር።
ሠላሳ ተጨማሪ
ዓመት ለመኖር የአምስት ወር መስዋዐትነት መክፈል፤ ንሥር አሞራ ቀሪ
30 ዓመቱን
ለመቀጠል ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት ጎጆ ይቀልሳል።ንሥር
በተራራው ላይ ጎጆ
ከቀለሰ በኃላ የመጀመርያ ሥራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በመፋቅና
በማጋጨት ነቅሎ
መጣል ነዉ። ይህም ከፍተኛ ህመምና ስቃይ አለው። ይሁን እንጂ አዲስ
መንቁር (አፍ)
ለማውጣት ይህንን ማድረግ የግድ ነው ከዚያም አዲስ መንቁር
ከወጣላት ወይም
ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁር የእግሩን አሮጌ ጥፍር ነቅሎ ይጥለዋል
። አዲሱ
የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ይህንን አዲስ ጥፍር አፉን እንደመሳርያ
በመጠቀም
በሰውነቱ የተጣበቀውን ጥቅጥቅ ያለውን ላባ ነቃቅሎ ጥሎ አዲስ ላባ
እንዲበቅል
ያደርጋል። ይህ እራሱን የመለወጥ ሂደት 5 ወር ወይም 150 ቀናቶች
ውስጥ ከተጠናቀቀ
ቦኋላ ንሥሩ በ 40 ዓመቱ ላይ ተጨማሪ 30 ዓመት በጥረቱ ይጨምርና
በሰማይ ላይ
በድጋሚ መብረር ይጀምራል ።
እኛስ እንደንሥሩ መለወጥ ያቅተን ይሆን? በህይወታችን ውስጥ
የምንፈልጋቸው ለውጦች
አንዳንድ ግዜ በአስቸጋሪና መራራ ሁኔታዎች ውስጥ እንድናልፍ ግድ
ይሉናል። የሰው ልጅ
በህይወቱ መከራ ሲገጥመው ከችግሩ ለመውጣትና ለመለወጥ ፤ ብሎም
ደስተኛ
ለመሆን አሮጌ ልምዱን ፤ትዝታዎቹንና አመለካከቱን አሽቀንጥሮ መጣል
ግድ ይለዋል ፤
ይህንን መስዋዕትነት ከከፈልን ልክ እንደንሥር አሞራው ቀሪ ህይወታችንን
በደስታ ልንኖር
እንችላለን። አሮጌ አስተሳሰባችንን፣ የማያስማሙንን፣ እኔ ብቻ የሚለዉን
ስሜታችንን፣
የሚያለያዩንን፣ መንቁራችንን፣ ጥፍራችንን እና ላባችንን ወደዚያ ነቅለን
ጥለ
በሚያስማሙን ፣በሚያቻችሉን እንተካቸዉ። ይህንን ስናደርግ እራሳችንንና
ሀገራችንን እንደ
ንስር አሞራው እንለውጣለን። አስገራሚ የሆነ መመሳሰል በንሥር ባሕሪና
በሰው ልጅ
ሕይወት አለ ። አምስት የንሥር ባህሪዎችን እንመልከት ፡፡
1፦ ንሥር ስፍራውን አይለቅም፣
የተለያ አዕዋፍና አራዊት ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተዛመደ መልኩ
ጎጆዋቸውንና
ስፍራቸውን በመተው ወደሌላ ቦታ ይሰደዳሉ። ይህም ፍልሰት በመባል
ይታወቃል። ኃይለኛ
የክረምት ወቅት ሲመጣ ብዙዎቹ ወደ ሌላ አካባቢ እስከ ረጅም ርቀት
ድረስ በመጓዝ ሀገር
ሁሉ አቋርጠው ይሰደዳሉ። ንሥር ግን እንደዚህ አይደለም። ክረምት አልፎ
በጋም
እንደሚመጣ ያውቃል በመሆኑም በብዙ ድካምና ጥረት የሠራውን ጎጆውን
ጥሎ
አይሸሽም። እንደምንም ብሎ በጎጆው ውስጥ በመሆን ያን የክረምቱን
ወራት ያሳልፋል።
ንሥር ሰዎችም እንደዚህ ናቸው። ወጀብ አውሎ ንፋስ ስለበዛባቸው ብቻ
እግዚአብሔር
ካስቀመጣቸው ቦታና ከሰጣቸው ስፍራ ተነስተው አይሄዱም። ፈጣሪ
ወጀቡን ጸጥ
በማድረግ እንደሚያሻግራቸው ያውቃሉ። በመሆኑም በስፍራቸው ጸንተው
ይቆያሉ ።
2፦ የንሥር ጠላት፣
ንሥር አንድ ጠላት ብቻ አለው። ያም እባብ ነው ። ንሥር ቤቱን
የሚሠራው ከፍ ባለ አለት
ላይ ስለሆነ ከእባብ ሌላ ምንም ሊደርስበት አይችልም። እባብ ግን
ተስታኮ ወደ ጎጆው
ሊያመራና የንሥርን እንቁላሎች ወይም ጫጩቶችን ሊጎዳ ይችላል
።ከዚህም የተነሳ ሴቷ
ንስር እንቁላሎችዋንም ሆነ ጫጩቶቿን በትጋት ነው የምትጠብቀው።
እባቡ ወደ ጎጆዋ
ሲመጣ በከፍተኛ ፍጥነት በአፏ እና በጥፍሮቿ ትይዘውና ወደላይ
ትበራለች ። ከዚያም
ዓለት ፈልጋ በዓለቱ ላይ እባቡን ትለቀዋለች። እባቡም በዓለቱ ላይ
ተፈጥፍጦ ይሞታል
።የሰው ልጆችም ጠላት እባብ የተባለው ዲያብሎስ ነው። የሰው ልጅም
ዲያብሎስን
የሚቀጠቅጠው በእግዚአብሔር ስም ነው፣
3፦ ንሥር ሲታመም፣
ንሥር አንዳንድ ጊዜ ይታመማል ።በተለይ የተበከለ ምግብ ከበላ
ይታመማል።
በሚታመምበትም ጊዜ ተዘርግቶ በደረቱ ይተኛና ዓይኑን ወደ ፀሐይ ቀና
በማድረግ
ፀሐይን በቀጥታ በዓይኖቹ ይመለከታል። ፈውስንም ከፀሐይ ብርሃን
ያገኛል። ንሥር የተለየ
ዓይን ስላለው ፀሐይን በቀጥታ ዓይቶ ሳይታወር የሚቀር የተለየ ፍጥረት
ነው። ዓይኑ እስከ
40 ኪ.ሜ ድረስም አሻግሮ ማየት ይችላል።
~ ንሥር ሰዎችም በሕይወታቸው ችግር ሲገጥማቸው፣ ድካም ሲይዛቸውና
ፈተና
ሲያንገላታቸው በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር በመመልከትና እርሱን ደጅ
በመጥናት እንደ
ፀሐይ ከሚያበራው ፊቱ ፈውስን ብርታትና ኃይልን ይቀበላሉ። ንሥር
አንዳንድ ጊዜ
ካልተፈወሰ እዚያው ፀሐይን እያየ ሞቶ ይቀራል። ሰው የመጣው ቢመጣ
ፈጣውን እያየ
ይሞታታል እንጂ ፈጣውን ትቶ አይሄድም ። ንሥር እስከ 40 ኪሜ ድረስ
ከርቀት አሻግሮ
እንደሚያይ ሁሉ ሰዎችም አስቀድመው ከርቀት የሚያዩበትና
የሚያስተውሉበትን መንፈስ
ከፈጣሪ ተቀብለዋል፡፡
4፦ ንሥር በማለዳ፣
ንሥር በማለዳ ተነስቶ ሁልጊዜ ከአፉ በሚወጣ ፈሳሽ ቅባት መሰል ነገር
የክንፎቹን
ላባዎች ይቀባል። ይህም ቀን በሚበርበት ጊዜ ክንፎቹ የንፋሱን ግፊት
ለመቋቋም ጥንካሬ
እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል። ይህንንም ተግባር ባለማቋረጥ በማለዳ ተነስቶ
ያደርጋል።
~ ንሥር ሰዎችም ዕለት በዕለት በማለዳ በመንቃት በጸሎት ቃሉን
በማንበብ ለየዕለቱ
ፈተና ውጣውረድ የሚያስፈልጋቸውን ኃይልና ብርታት ከፈጣሪ ይቀበላሉ።
ይህንን
ያልተለማመዱ አማኞች ግን ብዙ ጊዜ ሽንፈት ቢገጥማቸው አያስደንቅም።
ንሥር አማኞች
ግን እንደዚህ አይደሉም። ከእንቅልፍ ይልቅ የፈጣሪያቸውን ፊት ይናፍቃሉ፣
በማለዳም
ወደእርሱ ይገሰግሳሉ ፊቱንም ይፈልጋሉ ፈጣሪም ፊቱን በላያቸው ላይ
ያበራል፣ የቀኑንም
ክፋት ሁሉ በድል ይወጣሉ፡፡
5፦ የንሥር ፍቅር፣
ንሥር ለጫጩቶቿ የምታደርገው ፍቅር በጣም አስደናቂ ነው። ጫጩቶቿ
በሚፈለፈሉበት
ጊዜ የጎጆው እንጨት እንዳይጎረብጣቸው በደረቷ አካባቢ የሚገኘውን ስስ
የገላዋን ላባ
በመንጨት ትጎዘጉዝላቸዋለች። ጫጩቶቿም በምቾት ደስ ብሏቸው
በአካሏ ቁራጭ ላይ
ይተኛሉ ። ይሞቃቸዋልም ፣አማኞች የሆኑትም ተመሳሳይ ፍቅር ለሌሎች
እንዲያሳዩ
ይጠበቅባቸዋል። ለሰዎች የምናሳየው እንክብካቤ ፍቅርን የተላበሰ ሊሆን
ይገባል፡፡
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፣ እንደ
ንሥር በክንፍ
ይወጣሉ፣ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም ፣ይሄዳሉ አይደክሙም። ንሥር ሊዘንብ
ሲል እንደሌሎች
አእዋፍት፣እንስሳትና ሰዎች መጠለያ ፍለጋ አይራወጥም ፣ወደ ላይ ይበርና
ከዳመናው
በላይ ይሆናል ፣ዝናቡ ሲያባራ ወደ ምድር ወይም ጎጆው ይመለሳል።
እናም እንደ ንሥር
ወደ ላይ እየተባለ የሚዘመረው በዚሁ ምክንያት ነው ። ስለተባለም እኛም
እንደ ንሥር
ከችግሮቻችን በላይ በመሆን መፍትሄ መፈለግንና የለውጥ ሂደትን ከንሥር
እንማር
በማለት መምህሬ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አስደማሚውን
የንሥር ታሪክ
መተረኩን ይቋጫል።
እናም ወዳጄ ያየኸውን ሁሉ ለ666 መስጠቱን ተወውና የምታየው ነገር
ምን እንደሆነ
ሊቃውንቱን መጠየቁ ይሻልሃል። ምክሬ ነው ።
ንሥር በቤተክርስቲያን ትምህርት የቅድስት ሥላሴን ዙፋን ከሚሸከሙት
አርባዕቱ እንስሳ
ተብለው ከሚጠሩት ገፀ ሰብ፣ ገፀ ላህም፣ ገፀ አንበሳ ጋር በአራተኛ
ደረጃ ገፀ ንሥር
ተብሎ የሚሣል ነው። ከዚህም በተጨማሪ ዐራቱ ወንጌላውያን
የምንላቸው ማቴዎስ፣
ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ በእነዚሁ ዐርባዕቱ እንስሳ ተብለው በሚጠሩት
ይወከላሉ።
የሌሎቹን ለመዘርዘር ቦታው ባይሆንም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ግን
በንሥር
ተመስሏል። ምክንያቱ ደግሞ የረቀቀውን የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት
አምልቶና አስፍቶ
አመስጥሮም በመጻፉ ምክንያት ነው። ንሥር ከብዙ ኪሎሜትር ርቀት ላይ
በምድር
የምትንቀሳቀስን አነስተኛ ፍጥረት ለይቶ እንደሚያይ ሁሉ ወንጌላዊው
ቅዱስ ዮሐንስም
ረቂቁን የምስጢረ ሥላሴን አኗኗር ተመልክቶ ጽፏል እና ነው በንሥር
የተመሰለው።
ሻሎም ! ሰላም !
ምንጭ፡- ከአነበብኳቸው፡፡ እና ዘመድኩን በቀለ የፌስ ቡክ ገፅ
ክቡራን አንባቢዎቼ ምን ተማራችሁ? የእኔን ለእኔ ተውት!