ከ«ፀሐይ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት
Content deleted Content added
ጥ Removing Link GA template (handled by wikidata) |
ጥNo edit summary |
||
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:OceanSun.jpg|thumb|180px|ፀሓይ በውቅያኖስ ላይ ብልጭ ስትል]]
'''ፀሓይ''' በ[[ምድር]] ሥርዐተ-ፈለክ
ምድር በፀሓይ ዙሪያ የምታደርገውን አንድ ዙር ጉዞ ለመጨረስ አንድ ዓመት ይፈጅባታል፤ ይህን ጉዞ ስታደርግም በገዛ ራሷ ዘንጎ ወይም ምሽዋር
ፀሓይ ለሥርዐተ-ፈለካችን በጣም ብሩህ የኾነ ብርሃን ትሰጣለች። ያለ ፀሓይ ብርሃን ሙቀትም ኾነ ሕይወት በምድር አይኖርም ነበር። ለምሳሌ አረንጓዴ ዕፅዋት ያለ ፀሓይ ብርሃን ሊኖሩ አይችሉም፤ ለህልውናቸው የሚያስፈልጓቸውን ካርቦን ዳይኦክሳይድ እና አልሚ ምግቦች ለማስተጻመር የሚችሉት በፀሓይ ብርሃን ብቻ ነውና።
መስመር፡ 12፦
[[ስዕል:180px-Sola.jpg|160px|thumb|left|ፀሓይ በልዩ ቴሌስኮፕ ስትታይ]]
ኮከባችን ፀሓይ በሥነ ፈለክ ሊቃውንት እጅግ ብዙ ጥናት ተደርጎባታል። ኾኖም ኮከቢቱን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች ገና አልተመለሱም። ለምሳሌ በገሃድ የሚታየው የፀሓይ ገጽ ስኂን
የፀሓይ ዕድሜ በአንዳንድ ሊቃውንት እሳቤ 4.6 ቢሊዮን ዓመት ገደማ ነውና በዕድሜ እኩሌታዋ ላይ የምትገኝ ኮከብ ተደርጋ ትታያለች። የኮከቢቱ መጠነ-ቁስ
ስለ ፀሓይ የሰው ልጅ ቀዳሚ መሠረታዊ ግንዛቤ ብርሃን-ሰጭ ሰማያዊ ጻሕል
ከችንክር ከዋክብት አንጻር ስትታይ ፀሓይ የግርዶሽ መስመርን
በምዕራቡ ዓለም ውስጥ ስለ ፀሓይ ሳይንሳዊ መግለጫ ለመስጠት ከቻሉ ቀዳሚ ሰዎች አንዱ ግሪካዊው ፈላስፋ [[አናክሳጎራስ]] ነበር። ፀሓይ በእሳታዊ ነበልባል የምትንቀለቀል እጅግ ግዙፍ የብረት ኳስ እንጂ የሄሊዮስ ሰረገላ እንዳልነበረች በምክንያት የተደገፈ ትንተና አቀረበ። ይህንን እንደ ኑፋቄ የተቈጠረ ሐተታ በማስተማሩም ታሰረ፤ በሞት እንዲቀጣም ተፈርዶበት ነበር፤ በ[[ፔሪክልስ]] አማላጅነት እንዲፈታ ተፈቀደለት እንጂ።
መስመር፡ 24፦
የባለሥልጣናት መዓት የወደቀበት ሌላው የሳይንስ ሊቅ [[ኒቆላዎስ ቆጰርኒቆስ]] ነበር። በ16ኛው ምእት ውስጥ የኖረው ቆጰርኒቆስ ምድር ፀሓይን በቀለበትማ ምሕዋር ትዞራለች እንጂ፣ ፀሓይ ምድርን አትዞርም የሚል ኀልዮ አቅርቦ ነበር። በ17ኛው ምእት [[ጋሊሌዮ]] በቴሌስኮፕ ለታገዘ የፀሓይ ጥናት ፈር-ቀዳጅ ሊቅ ኾነ። [[አይዛክ ኒውተን]] ደግሞ በፕሪዝም አማካይነት የፀሓይ ብርሃን ልዩ ልዩ ቀለማት ካላቸው ብርሃናት የተጠናቀረ እንደኾነ አሳየ። 19ኛው ምእት [[ዊሊያም ኸርሽል]] የኢንፍራሬድ ጨረር ግኝት ባለቤት የኾነበት፣ በስፔክትሮስኮፕ ስለ ፀሓይ የሚደረገው ጥናትም እጅግ የመጠቀበት ምእት ኾነ።
[[ስዕል:SunMexican.jpg|6000px|
ዛሬ በብዙ አገሮች ልማድ ፀሓይ እንደ ባህላዊ ምልክት ትታያለች። ለምሳሌ በሜክሲኮ ኪነ ጥበብ አበክራ የምትታይ ''ሞቲፍ'' በመባል ትታወቃለች።
[[ስዕል:550px-Portrait_de_famille.jpg|frame|
በኛ ሥርዐተ-ፀሓይ ዋናዋ ትልቅ አካል ራሷ ፀሓይ ናት። በመላው ሥርዐተ-ፀሓይ ውስጥ ከሚገኘው ክብደት 99.86% የፀሓይ ነው። ለምሳሌ ከታላቁ ፈለክ ከ[[ጁፒተር]] ሲነጻጸር የፀሐይ ክብደት 1000 ዕጥፍ ይበልጣል። የፀሓይ ክብደት ከምድር 1.3 ሚሊዮን ጊዜ ይበልጣል። በጣም ግዙፍ እና ከባድ የኾነችው ኮከብ ከምድር ያለችበት ርቀት በጣም የሚያስደንቅ ነው። በምድር እና በፀሓይ መካከል ያለው ርቀት የምድርን ዳያሜትር በ12,000 ጊዜ ይበልጣል። ብርሃን ይህን ርቀት ለመጓዝ 8.5 ደቂቃ ይፈጅበታል።
▲[[ስዕል:550px-Portrait_de_famille.jpg|frame|left|450px|<big>የፀሓይ ጭፍሮችን አካለ-መጠን ማነጻጸሪያ፦ ምድር ከግራ ሦስተኛዋ ፈለክ ናት።]]
[[መደብ:ሥነ ፈለክ]]
|