ከ«ሰፍነግ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «ሰፍነጎች በእንስሳት የዘር ግንድ ላይ እጅግ ጥንታዊውንና የታችኛውን ቦታ ይዘው ይገኛሉ። == ልብም...»
 
No edit summary
መስመር፡ 21፦
ብዙ ሰፍነጎች ለገላ መታሻ እንደምንጠቀምባቸው ሰፍነጎች ለስላሳ ሳይሆኑ ሻካራ ወይም ጠንካራ ናቸው። እነዚህ ሰፍነጎች [[ስፔኪዩልስ]] የሚባሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጥቃቅን የመስታወት ቅንጣቶች አሏቸው። ስፔኪዩሎች በአጉሊ መነጽር ሲታዩ ያላቸው ውበትና ዓይነታቸው የተለያየ መሆኑ በጣም የሚያስገርም ነው። እነዚህ ስፔኪዩሎች በተለያየ መንገድ እንደ ሰንሰለት ሲያያዙ በጣም ውስብስብ የሆነ አጽም፣ የመከላከያ መሣሪያ እንዲያውም ቁመቱ እስከ 3 ሜትር ውፍረቱ ደግሞ እስከ 1 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ገመድ ይፈጥራሉ። አንድ ሥጋ በል ሰፍነግ ፍጥረታትን አድኖ የሚይዝበት [[ባለ መንጠቆ መረብ]] አለው።
 
ጥልቅ በሆነ ባሕር ውስጥ የሚገኘውና [[የቬነስ አበባ ቅርጫት]] እየተባለ የሚጠራው የሰፍነግ ዝርያ ስፔኪዩሎችን ተጠቅሞ በጣም ውብ የሆነ የአበባ ጥልፍ መሥራት ይችላል። እነዚህ እንደ ብርሌ የጠሩ የመስታወት ቃጫዎች ለስልክ ማስተላለፊያ የሚያገለግሉትን ዘመናዊ ፋይበር ኦፕቲክ ገመዶች ይመስላሉ። አንድ ሳይንቲስት “እነዚህ ሕያው ቃጫዎች በጣም ጠንካራ ናቸው” ብለዋል። አክለውም “በኃይል ብትቋጥራቸው እንኳ እንደ ሰው ሠራሾቹ ቃጫዎች አይበጠሱም” በማለት ተናግረዋል። እነዚህ ውስብስብ ቃጫዎች በባሕር ውስጥ እንዲሁም ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ባለበት አካባቢ እንዴት ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ሳይንቲስቶች በውል ሊረዱት አልቻሉም። የቤል ቤተ ሙከራ ባልደረባ የሆኑት [[ቼሪ ሙሬይ]] “በዚህ መንገድ፣ ውስብስብነት የሌለው ይህ ፍጥረት ፋይበር ኦፕቲክ ገመዶችንና እንደ ሴራሚክ ያሉ ነገሮችን በመሥራት ረገድ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት አገልግሏል” ብለዋል።<ref>በአውስትራሊያ የሚገኘው ''የንቁ!'' ዘጋቢ</ref>