ከ«ዩጎስላቪያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
content copied from internet (copyrighted material)
Tag: Replaced
 
መስመር፡ 7፦
[[መደብ:ሰርቢያ]]
[[መደብ:ክሮኤሽያ]]
Christian Tadele
ዩጎዝላቪያ እንዴት ፈራረሰች? (ክፍል አንድ)
*****
ዩጎዝላቪያ የባልካን ወሽመጥን አብዛኛውን ክፍል የሚሸፍንና
የአድሪያን ባሕርን ምሥራቃዊ ዳርቻ ሰርጥ ያካለለ፤በደቡብ
በኩል ደግሞ ከመካከለኛው አውሮፓ ትርስቴ ዳርቻ ተነስቶ
እስከ ቦያና እና ፕሬስፓ ኃይቅ አፍ ደገፍ ድረስ
የተዘረጋ፤በአይረን በሮች በኩል የባልካን ተራሮችን በመታከክ
እስከዳኑብና ሚድዞር የሚደርስ አቀማመጥ የነበረው ታላቅ
የደቡባዊ ምስራቅ አውሮፓ አገር ነበር፡፡ ምድሩም በታሪኩ ሁሉ
የማያባራ የብሔር ግጭትን ያስተናግድ ነበር፡፡
ለዩጎዝላቪያ መፈረካከስ ከዩጎዝላቪያ ንጉሳዊ አገረመንግሥት
ምስረታ ጋር ተያያዥ የሆኑ ታሪካዊ ቁርሾዎችና በሁለተኛው
የዓለም ጦርነት ጊዜ የእርስበርስ የብሔር ግጭቶችና
የፖለቲካ መናቆሮችን ተከትሎ የደረሰው የዘር ማጥፋት
ራሳቸውን የቻሉ መንግስታትን የመመስረት ማለትም ታላቋ
ሰርቢያ፣ታላቋ ክሮሽያ፣ታላቋ አልባኒያ የሚል የሃሳብ ጥንስስ
ወልዶ በአንድነት ላይ የነበረውን የተስፋ ጭላንጭል ጽልመት
አላበሰው፡፡ ይባስ ብሎ እንዳዲስ ውህድ አገር ሆነችው
ጀርመን ለእነዚህ አዳዲስ ውልድ አገራት የተናጠል እውቅና
መቸር የአንድነት ጉዞውን ከምጡ ወደ ዳጡ አደረገው፡፡
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊትም ቢሆን በዘውዳዊ
ዩጎዝላቪያ ውስጥ የብሔር ብዝኃነቱ ተዘንግቶ ሰርብያውያን
የፖለቲካ ሥልጣኑን መቆጣጠራቸው በብሔሮች መካከል
ለነበረው ውጥረት የራሱ ሚና ነበረው፡፡ ይህ ብሔራዊ ቅሬታ
ስላልተፈታ እንዳዲስ ፌዴራላዊ ሪፖብሊክ በሆነው
ዩጎዝላቪያም የውጥረት መንስዔ ሆኖ ቀጠለ፡፡ ክሮሽያውያንና
ስሎቬናውያን በአውስትሪያ-ሀንጋሪ ሥር ከነበራቸው
የዘውዳዊ ግዛትነት ይልቅ በፌዴራላዊ ዩጎዝላቪያ ሥር
የተሻለ ነፃነት አግኝተው በራስ ገዝነት መቀጠልን ምርጫቸው
አድርገው ነበር፡፡ በኦስትሪያ-ሀንጋሪ ስር እያሉ እኒህ ሁለቱ
በተለይ በትምህርት፣ህግ፣ኃይማኖትና የግብር አስተዳደር
ጉዳዮች ላይ የተሻለ ነፃነት ነበራቸው፡፡ ሰርብያውያን እኒህ
ሁለት ግዛቶች በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ለአንድነት
ኃይሎች ለሰጡት ድጋፍ እንደተበረከቱላቸው ገፀበረከቶች
አድርገው ከመቁጠራቸውም በላይ የሰርቢያ ንጉሰመንግስት
ሰፊ ግዛት አካል አድርገው ይቆጥሯቸው ነበር፡፡
በዚህ የተነሳም ብዙ ጊዜ በክሮሽያውንና በሰርቦች መካከል
ግጭቶች ይነሱ ነበር፡፡ የፀጥታ መዋቅሩን የተቆጣጠሩት
ሰርቦችም የተለያዩ ጭቆናዎችን ከማድረስ ባሻገር በብሔራዊ
ሸንጎ ውስጥ የክሮሽያዎች ተወካይ የነበረውን ስቴፈን ራዲችን
ጨምሮ ሌሎች ወሳኝ የፖለቲካ መሪዎችን ግድያ እጃቸውን
ያስገቡ ነበር፡፡ ምርጫ በመጣ ቁጥርም ክሮሽያውያንን
መፈናፈኛ ያሳጧቸው ነበር፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው የሰርቢያን
ዘውዳዊ ሥርዓት አፋኝነት በመቃወማቸው ነበር፡፡ የሰብዓዊ
መብት ረገጣዎችና ግድያዎችም የሰብዓዎ መብቶች
ማኅበርንና አልበርት አንስታይንን ጨምሮ የበርካታ ምሁራንን
ቁጣና ውግዘት ከመላው ዓለም አስተናገዱ፡፡ በዚህ ግርግር
ውስጥ ነበር ነውጠኛ አፋኝ ቡድን (ኋላ ላይ አምባገነናዊ
ፋሽት) የሆነው ኡስታሴ የተመሰረተው፡፡
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የአክሲስ ኃይሎች
የዩጎዝላቪያን ውስጣዊ ችግር ለዓላማቸው ማስፈፀሚያነት
ይጠቀሙበት ነበር፡፡ በዚህም የዛሬዎቹን ክሮሽያ እና ቦስኒያ-
ኼርዞጎቪኒያ ያካለለ በክሮሽያውያን የሚመራ አሻንጉሊት
መንግስት መመስረት ችለው ነበር፡፡ ይህ አሻንጉሊት
መንግስትም የኡስታሴ አመራሮችን የነፃይቱ ክሮሽያ
መንግሥት መሪ አድርጎ ያስቀመጠ ነበር፡፡ ኡስታሶች የኅዳጣን
ሰርቦችን ተስፋፊነት ይገታል ያሉትን ፖሊሲ በማውጣት ወደ
ተግባር ገቡ፡፡ በዕቅዳቸውም ሲሶዎቹን ለመግደል፣ሲሶዎቹን
ለማሳደድ እንዲሁም ቀሪ ሲሶዎቹን ደግሞ ወደ ካቶሊክ
እምነት ተከታይነት በመቀየር በክሮሽያውን ባህል ለመዋጥ
በአንድ ድምፅ ተስማሙ፡፡ በሌላ በኩል ቼትኒኮች የራሳቸውን
የአፈናና ማሳደድ እቅድ በቦስኒያ-ኼርዞጎቪኒያና በሳንድዛክ
የተወሰኑ አካባቢዎች ለመተግበር ደፋ ቀና እያሉ ነበር፡፡ ይህ
ሁሉ የሆነው አገራዊ እሴቶችን ለማውደምና ግጭቶችን
ለማፋፋም በተነደፈው የሞልጀቪች እቅድ መሰረት ነው፡፡
ለዚህ ሁሉ የጥፋት እቅድ ስኬትም ክሮሽያውንና
ሙስሊሞችን በፀጥታ መዋቅሩ በተለይም በ13ኛው
ክፍለጦር የተራራው ዕዝ በኩል ለወታደርነት ይመለመሉ
ነበር፡፡ በአንፃሩ ደግሞ የንጉሳውያን ቤተሰብ የነበረው ጀኔራል
ሚላን ኔዲች ለአሻንጉሊቱ መንግስት ርዕሰ መንግስት ተደርጎ
በአክሲስ ኃይሎች ተቀመጠ፡፡ ይህን ተከትሎም የሰርብ
ተወላጆችን ለሚስጢራዊ ፖሊስ ጌስታፖና የሰርቢያ
በጎፈቃደኛ ዘማቾች አባልነት ምልመላ ተካሄደ፡፡ እኒህ ሁሉ
ሽርጉዶች እና መሯሯጦች ከጦሩ አፈምግጠው በወጡ እና
ከሁሉም ብሔሮች በተሰባሰቡ የኮሚዩኒስት አቀንቃኝ ፀረ-
አክሲስ ኃይሎች ተሸንፈው ለሶሻሊስታዊ ፌዴራላዊ
ዬጎዝላቪያ ሪፖብሊክ መመስረት በር ከፈተ፡፡
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ባስከተለው መዘዝ ምክንያት
በዩጎዝላቪያ ያደረሰው ይፋዊ የተጎጂዎች አሃዝ 1,704,000
ይገመታል፡፡ የታሪክ ምሁራን በሆኑት ቭላድሚር ዘሪያቪችና
ቦጎሊዩብ ኮቾቪች የመረጃ ጥንቅር መሰረት የሟቾች አሃዝ 1
ሚሊዮን የሚደርስ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ330,000 እስከ
390,000 የሚደርሱ በብሔር ሰርብ የሆኑ ሰዎች በክሮሽያና
ሰርቢያ በተፈጠሩ እልቂቶች ደብዛቸው እንደጠፋ
አመላክተዋል፡፡
ከዚህ ሁሉ በኋላ ዩጎዝላቪያ ትንግርታዊ በሆነ መልኩ
የከባቢያዊ የኢንዱስትሪ ኃይልና የኢኮኖሚያዊ ስኬቶች
አብነት ሆና ብቅ አለች፡፡ ከ1960 እስከ 1980 ባለው ጊዜም
የጥቅል ዓመታዊ የአገር ውስጥ ምርት አማካይ ዓመታዊ
እድገት 6.1% የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜም የሕክምና
አገልግሎቶች በነፃ ከመቅርባቸውም ባሻገር ማንበብና መፃፍ
የሚችለው ሕዝብ 91% እንዲሁም በሕይወት የመኖር
የእድሜ ጣሪያም 72 ዓመታት ደርሶ ነበር፡፡
በዚህም የምስራቁና ምዕራቡ ዓለም መገናኛ ድልድይ የሆነች
ልዩዋን ዩጎዝላቪያ እውን ማድረግ ተችሎ ነበር፡፡ በይበልጥም
በፕሬዝዳንቷ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ የምትመራው ጎዝላቪያ
ኃያላኑን መገዳደር የሚያስችል 77 አገራትን ያቀፈ ሦስተኛው
ዓለም የተሰኘ ኅብረትን እስከማቋቋም ደርሳ ነበር፡፡
በምዕራባውያንና በሶቭየት ኅብረት መካከል ባለው ፍጥጫም
ዩጎዝላቪያ እንደነፃ ምድር የምትቆጠር እና የተባበሩት
የሶሻሊስታዊ ሶቭየት ራሽያን ወደ ሜዲትራኒያን ባሕር
እንዳትዘልቅ የደኅንነት አጥር ሆና ነበር፡፡
የኮሚኒስት ፓርቲ የራስን እድል በራስ መወሰን ብሔራዊ
ንቅናቄን ለመደገፍ ያሳየውን ተነሳሽነትና በየግዛቱ የሚነሱ
ብሔራዊ ቅሬታዎችን ተከትሎ የዩጎዝላቪያ ማዕከላዊ
መንግስት ቁጥጥር እየላላ ሄደ፡፡ በዚህም በ1974 እንዳዲስ
በፀደቀው ሕገመንግስት በሰርቢያ ስር የነበረቺው አልባንያውን
የሚበዙባት ኮሶቮ ራስገዝ አስተዳደር እንድትሆን ፈቃድ
አገኘች፡፡ አዲሱ ሕገመንግስት በማዕከላዊ መንግስቱና
በቮያቮዲና (በርካታ ኅዳጣን ብሔሮች የሚገኙበት
የዩጎዝላቪያ ክልል ነው) በሚገኙ ራስገዝ አስተዳደሮች
መካከልም የስልጣን ክፍፍልን አደረገ፡፡
ምንም እንኳን ዩጎዝላቪያ በአዲስ ፌዴራላዊ መዋቅር
የተደራጀች ቢሆንና ክልሎችም ራሳቸውን የማስተዳደር
ስልጣን የተሰጣቸው ቢሆንም በፌዴሬሽኑ አባል ክልሎች
ውጥረቶች ነበሩ፡፡ ክሮሽያውያንና ስሎቫንያዎች የበለጠ ነፃነት
እንዲሰጣቸው ሲሞግቱ ሰርብያውያን ደግሞ ማዕከላዊ
መንግስቱ ጠንካራ እንዲሆን ይወተውቱ ነበር፡፡ ይህ የውስጥ
ሽኩቻ በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዶ የግለሰብና ብሔራዊ
መብቶች ማስከበር ተቃውሞ ሰልፎች ላይ በተለይም
በክሮሽያውያን አመፅ ወቅት በግልፅ ይስተዋሉ ነበር፡፡
ተቃውሞዎቹን ለማፈን የተደረጉ ጥረቶችም የበለጠ
ልዩነቶችን የሚያሰፉ ነበሩ፡፡ የ1974ቱ የሕገመንግስት
ማሻሻያም የፌዴራላዊ አወቃቀሩን በአዲስ መልኩ
ለማስቀጠልና ብሔራዊ የመብት ጥያቄዎችን ለመመለስ
የተወጠነ ነበር፡፡
የፌዴራል መንግስቱ ልልነት ዩጎዝላቪያን ከፌዴሬሽን ወደ
ኮንፌዴሬሽን ቀየራት፡፡ ይኸውም በፌዴራላዊ መንግስቱ
ቅቡልነት ላይ አጠላበት፡፡ በ1970ዎቹ ማገባደጃ ላይ
ይስተዋል የነበረው የክልሎች የምጣኔ ኃብት ልዩነት
የፌዴሬሽኑን ኅልውና ክፉኛ ቦረቦረው፡፡ በእጅጉ የበለፀጉ
የክሮሽያና ስሎቬኒያ ክልሎች በ1974ቱ የሕገመንግስት
ማሻሻያ የተጎናፀፉትን ነፃነት የሚጋፉ ሙከራዎችን ሁሉ
እምቢኝ አሉ፡፡ በ1987 የተካሄደው የሕዝብ አስተያየት
ጥናትም በዩጎዝላቪያ ከመቀጠል ልቅ ስሎቬኒያ ራሷን ችላ
ብትገነጠል የበለጠ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳለው
አመላከተ፡፡ ከዩጎዝላቪያ ጋር መቀጠሉ አንዳችም ኢኮኖሚያዊ
ጠቀሜታ የለውም የሚሉ አስተያየቶችም ተበራከቱ፡፡
እንደኮሶቮ ባሉ ራስገዝ አስተዳደሮች በሁለተኛው የዓለም
ጦርነት ወቅት በኢኮኖሚ ከደቀቀችው ዩጎዝላቪያ በከፋ ሁኔታ
ዓመታዊ የምርት እድገቱ ያሽቆለቆለ በመሆኑ እና ይህም
በክልሎች መካከል ያለው የኢኮኖሚ እድገትና ፍትኃዊ
ተጠቃሚነት እጅግ የተራራቀ ስለነበር ከክልል ክልል ያለው
የኑሮ ሁኔታ የሰማይና ምድር ያህል የተራራቀ ነበር፡፡
የ1973ቱን የነዳጅ ዘይት ቀውስ ተከትሎ ምዕራባውያን
በዩጎዝላቪያ ላይ የንግድ ማዕቀብ ስለጣሉ የኢኮኖሚ እድገቱ
ተገትቶ ነበር፡፡ ከዓለምአቀፍ የገንዘብ ተቋም ሥርዓቱ በብድር
መልክ በወሰደው ከፍተኛ የሆነ እዳ ምክንያትም አገሪቱ
ከምጡ ወደ ዳጡ ገባች፡፡ ተጨማሪ ብድር ለማግኜትም
በዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም በኩል ገበያውን ነፃ ማድረግ
በቅድመሁኔታነት ተቀመጠባት፡፡ በ1981 ዩጎዝላቪያ
አጠቃላይ የውጭ እዳዋ 19.9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር
ደርሰ፡፡ ሌላው እንቅልፍ የሚነሳው ጉዳይ 1 ሚሊዮን
የደረሰው የሥራአጥ ዜጎች ቁጥር ነው፡፡ ችግሩም የደቡባዊ
ዩጎዝላቪያ ኢ-ምርታማነት ጋር ተያይዞ የተከሰተ በመሆኑ
ስሎቬኒያና ክሮሽያ ፊታቸውን እንዲያዞሩ አደረጋቸው