ከ«ኅሩይ ወልደሥላሴ (ብላቴን ጌታ)» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot-assisted disambiguation: እንግሊዝ - Changed link(s) to ዩናይትድ ኪንግደም
የጸሐፊ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ የማበረታቻ ምክር
መስመር፡ 3፦
'''ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ''' በ[[ኢትዮጵያ]] መኻል አገር በሰሜን [[ሸዋ]] [[በመርሐ ቤቴ]] አውራጃ በታች ቤት ወረዳ ረመሸት ቀበሌ ደን አቦ ገዳም በተባለ ሥፍራ በ [[1871|፲፰፻፸፩]] ዓ.ም ተወለዱ። ሲወለዱ የተሰጣቸው ስም ገብረመስቀል ነበር። በቤተ ክህነት ትምህርት እንጦጦ ራጉኤል ደብር መጥተው የመጻሕፍትን ትርጓሜ በዘመኑ ከነበሩት የደብሩ ሊቃውንት ዘንድ ተምረው አጠናቀዋል። እዚህ ነው አንዱ መምህራቸው «አንተ የቀለም ቀንድ ስለሆንክና በምግባርህም የተመሰገንህ ነህና፡ ኅሩይ የተባለውን ስሜን ሸልሜያሃለሁ፡ ከንግዲህ ኅሩይ እየተባልክ ተጠራ!» አሏቸው። <ref>''የኢትዮጵያ ታሪክ፡ ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የአድዋ ድል'' በብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ - [[1999|፲፱፻፺፱]] ዓ.ም</ref>
 
በቅኔና በ[[ሥነ ጽሑፍ]] ሞያቸውም እጅግ የሚመሰገኑ ታላቅ ሊቅ ስለበሩ፡ [[ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ ወልደ አረጋዊ]] ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴን፤ የኢትዮጵያ ሊቃውንትን ቅኔ አሰባስበው እንዲያሳትሙ ያነቃቁአቸውና ያበረታቱአቸው እንደነበር የታሪክ ዘገባዎች ያረጋግጣሉ። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ሃያ አንድ መጻሕፍትን የደረሱ ሲሆኑ፤ የመጨረሻው መጽሐፋቸው «የኢትዮጵያ ታሪክ፡ ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የአድዋ ድል» ለመጀመሪያ ጊዜ በ [[1999|፲፱፻፺፱]] ዓ.ም የልጅ ልጃቸው ወይዘሮ ሠናይት ተክለማርያም አሳተሙት። [[የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር]] እና [[የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት]] በመተባበር [[ጳጉሜ ፪]] ቀን [[2004|፳፻፬]] ዓ/ም በ[[አዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ]] የተመረቁትን እና [[ኅሩይ ወልደ ሥላሴ (ብላቴን ጌታ)|ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ]] እንዲሁም የደራስያን፤- ቀኝ-ጌታ [[ዮፍታሄ ንጉሤ]]ን፤ ነጋድራስ[[አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ]]፣ እና አቶ [[ተመስገን ገብሬ]]ን ምስል የተቀረጸባቸውን አራት ቴምብሮችን ገበያ ላይ አውለዋል።<ref> ‘ሪፖርተር’ Ethiopian Reporter, “የአራት ደራስያን መታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ” 09 SEPTEMBER 2012 </ref> ደራሲው ፋሽሽት [[ኢጣልያ]] ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ከ[[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ]] ጋር አብረው ወደ [[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]] አገር ስደት ላይ እንዳሉ በስልሳ ዓመታቸው [[መስከረም 9|መስከረም ፱]] ቀን [[1931|፲፱፻፴፩]] ዓ.ም. አረፉ።
 
ሥርዓተ ቀብራቸው [[መስከረም 10|መስከረም ፲]] ቀን እዚያው እንግሊዝ አገር ሲፈጸም ንጉሠ ነገሥቱ የሚከተለውን ንግግር አደረጉ።