ከ«ፋሲካ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ፋሲካ''' [[ኢየሱስ ክርስቶስ]] ከሙታን መካከል የተነሳበትን የ[[ትንሳዔ]] ቀን ማሰብያ ዕለት ነው።
 
ስሙ ''ፋሲካ'' የመጣው ከ[[አረማይክ]] /ፓስኻ/፣ [[ግሪክኛ]] /ፓስቃ/፣ [[ዕብራይስጥ]] /ፐሳኽ/ ሲሆን፤ [[የአይሁድ ፋሲካ]] በዓል [[ዕብራውያን]] በ[[ሙሴ]] መሪነት ከ[[ግብፅ]] [[ፈርዖን]] ግዛት በተዓምራትና በመቅሠፍቶች የወጡበትን ጊዜ ለማክበር ነበር። ይህ ታሪክ በተለይ በ[[ብሉይ ኪዳን]] [[ኦሪት ዘጸአት]] ይገለጻል። በተለይ በዘጸአት 12፡23 በአሥረኛው መቅሠፍት ጊዜ "እግዚአብሔር ያልፋል" ሲል፥ "ያልፋል" የሚለው ግሥ በዕብራይስጡ /ፐሳኽ/ ስለ ሆነ፣ ስሙ ''ፋሲካ'' ከዚያው ቃል ደረሰ።
 
በ[[አዲስ ኪዳን]] ዘንድ ደግሞ ኢየሱስ ለፋሲካ በዓል አዲስ ትርጉም ሰጠው። በ[[መጨረሻው እራት]] ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የበዓሉን ዝግጅት ሲጠብቅ ሥጋ ወደሙ እንደ መስዋዕቱ ሆኖ ባካፈለው ኅብስትና ወይን በኩል እንደሚገኝ አመለከተ። ኢየሱስም ተሰቅሎ ከ፫ ቀን በኋላ በእግዚአብሔር ኃይል ተነስቶ ዳግመኛ ለደቀመዛሙርቱ ታይቶ፣ በነዚህ ዘመኖች ፍፃሜ ለ[[ፍርድ ቀን]] በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ እንደሚመለስ ነገራቸው። ይህ ሁሉ አሁን በ[[ክርስትና]] ወይም በ[[አብያተ ክርስቲያናት]] በፋሲካ በዓል የሚከበር ነው።