ከ«ጆን ኔፐር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:John_Napier.jpg|rechts|thumb|200px|ጆን ኔፐር]]
'''ጆን ኔፐር''' (1542– 1610) – በድሮ ዘመን የነበር [[ስኮትላንድ|ስኮትላንዳዊ]] [[ሓሳቢ]] (ሒሳብ ተማሪ)፣ [[የተፈጥሮ ህግጋት ጥናት]] ተመራማሪ፣ [[ሥነ ፈለክ]] አጥኚ እና [[ኮኮብ ቆጠራ|ኮኮብ ቆጣሪ]] ነበር።
 
ከሁሉ ስራው በታሪክ ቀደምት ስሙ እሚነሳው [[ሎጋሪዝም]]ን በመፈልስፉ ነበር። ይህን የሂሳብ መሳሪያ የፈለስፈበት ዋና ምክንያት ከ[[ኮምፒውተር]] እና [[ካልኩሌተር]] ርቆ በሚገኝው በእርሱበሚገኘው ዘመን ቁጥሮችን [[ማባዛት]]፣ ጊዜ የሚወስድ፣ ለስህተትም የተጋለጠ መሆኑ ነበር። ሎጋሪዝም እንግዲህ ማባዛትን ወደ [[መደመር]] በመቀየር አስቸጋሪውንና አሰልቺውን የማባዛት ስራ ለማቃለል ይረዳል።
 
ክፍልፋይ ቁጥርን ለማሳየት የምትጠቅመው [[የአስርዮሽ ነጥብ|ነጥብ]] በአውሮጳ ታዋቂ እንድትሆን ያደረገ ኔፐር ነበር። ከዚህ በተረፈ ኔፐር በ[[ሥነ መለኮት]]፣ [[ሥነ አልኬሚ]] ይጠቀሳል። በዘመኑ ደግሞ በ[[ጥንቆላ]] ና በ[[ማሟረት]] ስራ ይታማ ነበር።
መስመር፡ 11፦
የቤቱ ሰራተኞች ዕቃ ሲሰርቁ ይሄው አውራዶሮ የትኛው አገልጋዩ እንደሰረቀው ለማወቅ ይረዳው ነበር ይባላል። ለምሳሌ ዕቃ ከቤቱ ሲጠፋ፣ አገልጋዮቹን አንድ ባንድ ከዶሮው ጋር እቤቱ ውስጥ እየቆለፈ ዶሮውን እንዲነኩ ከውጭ ሆኖ ያዛቸው ነበር። ከዚያ በኋላ አውራ ዶሮው የትኛው አገልጋይ ጥፋተኛ እንደሆነ ይነግረው ነበር ይባላል። ይሁንና ይህን ተግባር ሲከውን በፈሊጥ ነበር። ጥቁር አውራዶሮውን ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ከመቆለፉ በፊት [[ጥላሸት]] ይለቀልቀው ነበር። ጥፋተኛ የሆኑት አገልጋዮች ዶሮው ይናገርብናል ብለው ስለሚፈሩ ዶሮውን አይነኩም፣ ጥፋት የሌለባቸው ባንጻሩ ይነኩታል። በኋላ ላይ ኔፐር እጃቸውን አንድ ባንድ ሲመረምር፣ እጃቸው ንጹህ የሆኑት ጥፋተኛ እንደሆኑ ያውቃል ማለት ነው።
 
ኔፐር ጠንቋይ እንደሆነ በአገሩ የተማበት ሌላ ምክንያትም አለ። አንድ ቀን ኔፐር ያሰጣውን [[ጥራጥሬ]] የጎረቤቱ [[እርግብ|እርግቦች]] እየለቀሙበት ይደርሳል። በዚህ የተናደደው ኔፐር ጎረቤቱን ጠርቶ እርግቦቹ እኔፐር ግቢ ሁለተኛ ከመጡ የእርሱ ንብረት እንደሚያደርጋቸው ያስጠነቅቀዋል። በሚቀጥለው ቀን እርግቦቹ ኔፐር ግቢ ውስጥ ታዩ፣ ሆኖም ግን በሚያስፈራ መልኩ ከቆይታ በኋላ ሁሉም ተዝለፍልፈው ወድቀው በኔፐር እየተለቀሙ አዘጋጀላቸው አቅማዳ ውስጥ ሲታጨቁ ታዩ። ኔፐር ሆየ ባለፈው ቀን ጥራጥሬውን የሚያሰክር [[ብራንዲ]] ውስጥ ከዘፈዘፈ በኋላ ነበር ለስጦሽ የዘረጋው። ጠዋት ላይ እርግቦቹ አተሩን ሲለቅሙ እየተሳከሩ መብረር አቅቷቸው መሬት ላይ እየተንደፋደፉ ተፈነገሉ።
 
[[መደብ: ሒሳብ ተመራማሪዎች]]