ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 404፦
፱. በግዕዝ ኮምፕዩተር መክተቢያ ከኮምፕዩተሩ ጋር ስለማይመጣ መክተቢያ መግዛት ያስፈልጋል። የኮምፕዩተርም ዋና ጥቅም የተጻፈን ነገር ማስቀመጥ ስለሆነ ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው። በተጨማሪም ኣንድን ጽሑፍ እንደፌስቡክ ከኣሉ ገጾች ውስጥ ወስዶ ማስቀመጥ ብቻ በቂ ኣይደለም። በቋንቋዎቻችን የተጻፉ መረጃዎች እንደሌሎች ቋንቋዎች በብዛት እንዲኖሩ በእጥፍ ብዛት መጻፍ ይጠበቅብናል። በኣለፉት ጥቂት ዓመታት ብዙ ጽሑፎች በኢትዮጵያውያን ትጋት ስለቀረቡ በኮምፕዩተር እንግሊዝኛውን ወደ ዓማርኛና ዓማርኛውን ወደ እንግሊዝኛ መተርጐም ተጀምሯል። ፲. የዓማርኛ ትክክለኛዎቹ ኆኄያት "ዓማርኛ" ናቸው። ሌሎች ምሳሌዎችም “ኃይል”፣ “ሕዝብ” እና “ዓቢይ” ናቸው። ለምሳሌ ያህል “አቢይ”፣ “ኣቢይ”፣ “ዐቢይ”፣ ወይም “ዓብይ” ትክክል ኣይመስለኝም ይላሉ ዶክተሩ። ምሳሌ [https://mahberemariam.wordpress.com/2014/02/20/%E1%88%B5%E1%89%A5%E1%8A%A8%E1%89%B5-35/] የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ባሕረ ሓሳብ መጽሓፍ ገጽ 47 እና 48 ስለ ዓቢይ ጾምና ዓቢይ ቀመር ቀርበዋል። ፲፩. በኣጠቃላይ በኣለፉት 45 ዓመታት የኢትዮጵያውያን የዕውቀትና የዓማርኛ ቋንቋዎች ችሎታዎች ኣቆልቍለዋል። በተለይ በእዚህ ዕድሜ ክልል ውስጥ የኣሉ ምሁራን ዓማርኛ ሲናገሩ እንግሊዝኛ እንዳይቀላቅሉ ሊያስተውሉ ይገባል። ፲፪. ኣንድኣንድ ዓማርኛ ተናጋሪዎች “Torture” በሚለው ቃል ምትክ “Torch” የሚለውን ይጠቀማሉ። መዝገበ ቃላት መጠቀም ሳይጠቅም ኣይቀርም። [https://ethsat.com/2018/05/esat-tikuret-minalachew-simachew-with-dr-abera-mola/] ፊደል በሚገባ ስለ ኣልቆጠሩ በ“ነው” ምትክ “ነዉ" ይጠቀማሉ።
 
፲፫. ኣንድኣንድ ዓማርኛ ፀሓፊዎች በነጠላ ሰረዝ ምትክ የላቲኑን ኮማ (Comma) እንዲሁም በድርብ ሰረዝ ምትክ የላቲኑን ሰሚ ኮለን (Semi-colon) መጠቀም ስለጀመሩ ዶክተሩ እየተቃወሙ ናቸው። ፲፬. ኣንድኣንድ ዓማርኛ ፀሓፊዎች መጽሓፎች ሲያሳትሙ ገጾቹን ለየብቻቸው እያተሙ ይጠርዛሉ። የመጽሓፍና መጽሔት ገጾች ሲታጠፉ ቍጥሮቹና ርዕሶቹ መሳሳም ይገባቸዋል። ለምሳሌ ያህል ገጽ ኣንድ ከግራ ግርጌ ማዕዘን ከሆነ ገጽ ሁለት ከቀኝ ግርጌ ማዕዘን ላይ መሆን ይኖርበታል። ፲፭. ኣንድኣንድ ምሁራን ለዓማርኛ ቃለ ምልልስ ሲቀርቡ በዓማርኛ መናገር እንዳለባቸው ኣስቀድሞ ማስጠንቀቅ ያስፈልጋል። እንግሊዝኛ እየቀላቀሉ የሚያስቸግሩትን በማረም የኣሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጥሩ ሥራ ይዟል። ፲፮. ኣንድኣንድ ኢትዮጵያውያን ዓማርኛውን ኣራት ነጥብ በሌለው ከመጻፍ እንዲቆጠቡና ኣራት ነጥብ በሌለውም መጻፊያ እየጻፉ ጊዜያቸውን ከማባከን ቢቆጠቡ ይጠቅማል።
 
፲፯. ኣንድኣንድ ፀሓፊዎች ሞክሼዎች የሚሏቸውን ቀለሞች በሌሏቸው ዓማርኛውን እየጻፉ ችግሮች እየፈጠሩ ናቸው። ለምሳሌ ያህል “መሳሳት"ና “መሣሣት" ወይም “ዓለማቀፍ"ና “ኣለማቀፍ" ኣንድ ኣይደሉም።
 
===የግዕዝ ቁምፊዎች===