ከ«የማቴዎስ ወንጌል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 1,464፦
ውጭም፡ወጥቶ፡መራራ፡ልቅሶ፡አለቀሰ።
== '''ምዕራፍ ፳፯''' ==
1፤ሲነጋም፡የካህናት፡አለቃዎችና፡የሕዝቡ፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ሊገድሉት፡በኢየሱስ፡ላይ፡ተማከሩ፤
2፤አስረውም፡ወሰዱት፥ለገዢው፡ለጰንጤናዊው፡ጲላጦስም፡አሳልፈው፡ሰጡት።
3፤በዚያን፡ጊዜ፡አሳልፎ፡የሰጠው፡ይሁዳ፡እንደ፡ተፈረደበት፡አይቶ፡ተጸጸተ፥ሠላሳውንም፡ብር፡ለካህናት፡
አለቃዎችና፡ለሽማግሌዎች፡መልሶ፦
4፤ንጹሕ፡ደም፡አሳልፌ፡በመስጠቴ፡በድያለኹ፡አለ።እነርሱ፡ግን፦እኛስ፡ምን፡አግዶን፧አንተው፡
ተጠንቀቅ፡አሉ።
5፤ብሩንም፡በቤተ፡መቅደስ፡ጥሎ፡ኼደና፡ታንቆ፡ሞተ።
6፤የካህናት፡አለቃዎችም፡ብሩን፡አንሥተው፦የደም፡ዋጋ፡ነውና፥ወደ፡መባ፡ልንጨምረው፡አልተፈቀደም፡
አሉ።
7፤ተማክረውም፡የሸክላ፡ሠሪውን፡መሬት፡ለእንግዳዎች፡መቃብር፡ገዙበት።
8፤ስለዚህ፥ያ፡መሬት፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡የደም፡መሬት፡ተባለ።
9፤በዚያን፡ጊዜ፡በነቢዩ፡በኤርምያስ፡የተባለው፦ከእስራኤል፡ልጆችም፡አንዳንዶቹ፡የገመቱትን፥የተገመተውን፡
ዋጋ፡ሠላሳ፡ብር፡ያዙ፥
10፤ጌታም፡እንዳዘዘኝ፡ስለሸክላ፡ሠሪ፡መሬት፡ሰጡት።የሚል፡ተፈጸመ።
11፤ኢየሱስም፡በገዢው፡ፊት፡ቆመ፤ገዢውም፦የአይሁድ፡ንጉሥ፡አንተ፡ነኽን፧ብሎ፡
ጠየቀው፤ኢየሱስም፦አንተ፡አልኽ፡አለው።
12፤የካህናት፡አለቃዎችም፡ሽማግሌዎችም፡ሲከሱት፡ምንም፡አልመለሰም።
13፤በዚያን፡ጊዜ፡ጲላጦስ፦ስንት፡ያኽል፡እንዲመሰክሩብኽ፡አትሰማምን፧አለው።
14፤ገዢውም፡እጅግ፡እስኪደነቅ፡ድረስ፡አንዲት፡ቃል፡ስንኳ፡አልመለሰለትም።
15፤በዚያም፡በዓል፡ሕዝቡ፡የወደዱትን፡አንድ፡እስረኛ፡ሊፈታላቸው፡ለገዢው፡ልማድ፡ነበረው።
16፤በዚያን፡ጊዜም፡በርባን፡የሚባል፡በጣም፡የታወቀ፡እስረኛ፡ነበራቸው።
17፤እንግዲህ፡እነርሱ፡ተሰብስበው፡ሳሉ፡ጲላጦስ፦በርባንን፡ወይስ፡ክርስቶስ፡የተባለውን፡ኢየሱስን፡
ማንኛውን፡ልፈታላችኹ፡ትወዳላችኹ፧አላቸው፤
18፤በቅንአት፡አሳልፈው፡እንደ፡ሰጡት፡ያውቅ፡ነበርና።
19፤ርሱም፡በፍርድ፡ወንበር፡ተቀምጦ፡ሳለ፥ሚስቱ፦ስለ፡ርሱ፡ዛሬ፡በሕልም፡እጅግ፡መከራ፡
ተቀብያለኹና፥በዚያ፡ጻድቅ፡ሰው፡ምንም፡አታድርግ፡ብላ፡ላከችበት።
20፤የካህናት፡አለቃዎችና፡ሽማግሌዎች፡ግን፡በርባንን፡እንዲለምኑ፡ኢየሱስን፡ግን፡እንዲያጠፉ፡ሕዝቡን፡
አባበሉ።
21፤ገዢውም፡መልሶ፦ከኹለቱ፡ማንኛውን፡ልፈታላችኹ፡ትወዳላችኹ፧አላቸው፤እነርሱም፦በርባንን፡አሉ።
22፤ጲላጦስ፦ክርስቶስ፡የተባለውን፡ኢየሱስን፡እንግዲህ፡ምን፡ላድርገው፧አላቸው፤ዅሉም፦ይሰቀል፡አሉ።
23፤ገዢውም፦ምን፡ነው፧ያደረገው፡ክፋት፡ምንድር፡ነው፧አለ፤እነርሱ፡ግን፦ይሰቀል፡እያሉ፡ጩኸት፡
አበዙ።
24፤ጲላጦስም፡ሁከት፡እንዲዠመር፡እንጂ፡አንዳች፡እንዳይረባ፡ባየ፡ጊዜ፥ውሃ፡አንሥቶ፦እኔ፡ከዚህ፡
ጻድቅ፡ሰው፡ደም፡ንጹሕ፡ነኝ፤እናንተ፡ተጠንቀቁ፡ሲል፡በሕዝቡ፡ፊት፡እጁን፡ታጠበ።
25፤ሕዝቡም፡ዅሉ፡መልሰው፦ደሙ፡በእኛና፡በልጆቻችን፡ላይ፡ይኹን፡አሉ።
26፤በዚያን፡ጊዜ፡በርባንን፡ፈታላቸው፥ኢየሱስን፡ግን፡ገርፎ፡ሊሰቀል፡አሳልፎ፡ሰጠ።
27፤በዚያን፡ጊዜ፡የገዢው፡ወታደሮች፡ኢየሱስን፡ወደገዢው፡ግቢ፡ውስጥ፡ወሰዱት፡ጭፍራውንም፡ዅሉ፡
ወደ፡ርሱ፡አከማቹ።
28፤ልብሱንም፡ገፈው፡ቀይ፡ልብስ፡አለበሱት፥
29፤ከሾኽም፡አክሊል፡ጐንጉነው፡በራሱ፡ላይ፥በቀኝ፡እጁም፡መቃ፡አኖሩ፥በፊቱም፡ተንበርክከው፦የአይሁድ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፡እያሉ፡ዘበቱበት፤
30፤ተፉበትም፡መቃውንም፡ይዘው፡ራሱን፡መቱት።
31፤ከዘበቱበትም፡በዃላ፡ቀዩን፡ልብስ፡ገፈፉት፥ልብሱንም፡አለበሱት፡ሊሰቅሉትም፡ወሰዱት።
32፤ሲወጡም፡ስምዖን፡የተባለው፡የቀሬናን፡ሰው፡አገኙ፤ርሱንም፡መስቀሉን፡ይሸከም፡ዘንድ፡አስገደዱት።
33፤ትርጓሜው፡የራስ፡ቅል፡ስፍራ፡ወደሚኾን፥ጎልጎታ፡ወደሚባለው፡ስፍራ፡በደረሱ፡ጊዜም፥
34፤በሐሞት፡የተደባለቀ፡የወይን፡ጠጅ፡ሊጠጣ፡አቀረቡለት፤ቀምሶም፡ሊጠጣው፡አልወደደም።
35፤ከሰቀሉትም፡በዃላ፡ልብሱን፡ዕጣ፡ጥለው፡ተካፈሉ፥
36፤በዚያም፡ተቀምጠው፡ይጠብቁት፡ነበር።
37፤ይህ፡ኢየሱስ፡የአይሁድ፡ንጉሥ፡ነው፡የሚል፡የክሱን፡ጽሕፈት፡ከራሱ፡በላይ፡አኖሩ።
38፤በዚያን፡ጊዜ፡ኹለት፡ወንበዴዎች፡አንዱ፡በቀኝ፡አንዱም፡በግራ፡ከርሱ፡ጋራ፡ተሰቀሉ።
39፤የሚያልፉትም፡ራሳቸውን፡እየነቀነቁ፡ይሰድቡት፡ነበርና።
40፤ቤተ፡መቅደስን፡የምታፈርስ፡በሦስት፡ቀንም፡የምትሠራው፥ራስኽን፡አድን፤የእግዚአብሔር፡ልጅስ፡
ከኾንኽ፡ከመስቀል፡ውረድ፡አሉት።
41፤እንዲሁም፡ደግሞ፡የካህናት፡አለቃዎች፡ከጻፊዎችና፡ከሽማግሌዎች፡ጋራ፡እየዘበቱበት፡እንዲህ፡አሉ።
42፤ሌላዎችን፡አዳነ፥ራሱን፡ሊያድን፡አይችልም፤የእስራኤል፡ንጉሥ፡ከኾነ፥አኹን፡ከመስቀል፡ይውረድ፡
እኛም፡እናምንበታለን።
43፤በእግዚአብሔር፡ታምኗል፤የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኝ፡ብሏልና፥ከወደደውስ፡አኹን፡ያድነው።
44፤ከርሱ፡ጋራ፡የተሰቀሉት፡ወንበዴዎች፡ደግሞ፡ያንኑ፡እያሉ፡ይነቅፉት፡ነበር።
45፤ከስድስት፡ሰዓትም፡ዠምሮ፡እስከ፡ዘጠኝ፡ሰዓት፡ድረስ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ጨለማ፡ኾነ።
46፤በዘጠኝ፡ሰዓትም፡ኢየሱስ፦ኤሎሄ፥ኤሎሄ፥ላማ፡ሰበቅታኒ፧ብሎ፡በታላቅ፡ድምፅ፡
ጮኸ።ይህም፦አምላኬ፡አምላኬ፥ስለ፡ምን፡ተውኸኝ፧ማለት፡ነው።
47፤በዚያም፡ከቆሙት፡ሰዎች፡ሰምተው፦ይህስ፡ኤልያስን፡ይጠራል፡አሉ።
48፤ወዲያውም፡ከነርሱ፡አንዱ፡ሮጠ፤ሰፍነግም፡ይዞ፡ሖምጣጤ፡ሞላበት፥በመቃም፡አድርጎ፡አጠጣው።
49፤ሌላዎቹ፡ግን፦ተው፥ኤልያስ፡መጥቶ፡ያድነው፡እንደ፡ኾነ፡እንይ፡አሉ።
50፤ኢየሱስም፡ኹለተኛ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኾ፡ነፍሱን፡ተወ።
51፤እንሆም፥የቤተ፡መቅደስ፡መጋረጃ፡ከላይ፡እስከ፡ታች፡ከኹለት፡ተቀደደ፥ምድርም፡
ተናወጠች፥አለቶችም፡ተሰነጠቁ፤
52፤መቃብሮችም፡ተከፈቱ፥ተኝተው፡ከነበሩትም፡ከቅዱሳን፡ብዙ፡ሥጋዎች፡ተነሡ፤
53፤ከትንሣኤውም፡በዃላ፡ከመቃብሮች፡ወጥተው፡ወደ፡ቅድስት፡ከተማ፡ገቡና፡ለብዙዎች፡ታዩ።
54፤የመቶ፡አለቃም፡ከርሱም፡ጋራ፡ኢየሱስን፡የሚጠብቁ፡መናወጡንና፡የኾነውን፡ነገር፡አይተው፦ይህ፡
በእውነት፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነበረ፡ብለው፡እጅግ፡ፈሩ።
55፤ኢየሱስን፡እያገለገሉ፡ከገሊላ፡የተከተሉት፡ብዙ፡ሴቶች፡በሩቅ፡ኾነው፡ሲመለከቱ፡በዚያ፡ነበሩ፤
56፤ከነርሱም፡መግደላዊት፡ማርያምና፡የያዕቆብና፡የዮሳ፡እናት፡ማርያም፡የዘብዴዎስም፡የልጆቹ፡እናት፡ነበሩ።
57፤በመሸም፡ጊዜ፡ዮሴፍ፡የተባለው፡ባለጠጋ፡ሰው፡ከአርማትያስ277፡መጣ፥ርሱም፡ደግሞ፡የኢየሱስ፡ደቀ፡
277 ዕብ.፥ራማህ።
መዝሙር፡ነበረ፤
58፤ይኸውም፡ወደ፡ጲላጦስ፡ቀርቦ፡የኢየሱስን፡ሥጋ፡ለመነው።
59፤ጲላጦስም፡እንዲሰጡት፡አዘዘ።ዮሴፍም፡ሥጋውን፡ይዞ፡በንጹሕ፡በፍታ፡ከፈነው፥
60፤ከአለት፡በወቀረው፡በዐዲሱ፡መቃብርም፡አኖረው፥በመቃብሩም፡ደጃፍ፡ታላቅ፡ድንጋይ፡አንከባሎ፡ኼደ።
61፤መግደላዊት፡ማርያምም፡ኹለተኛዪቱም፡ማርያም፡በመቃብሩ፡አንጻር፡ተቀምጠው፡በዚያ፡ነበሩ።
62፤በማግስቱም፡ከመዘጋጀት፡በዃላ፡በሚኾነው፡ቀን፥የካህናት፡አለቃዎችና፡ፈሪሳውያን፡ወደ፡ጲላጦስ፡
ተሰበሰቡና፦
63፤ጌታ፡ሆይ፥ያ፡አሳች፡በሕይወቱ፡ገና፡ሳለ፦ከሦስት፡ቀን፡በዃላ፡እነሣለኹ፡እንዳለ፡ትዝ፡አለን።
64፤እንግዲህ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡መጥተው፡በሌሊት፡እንዳይሰርቁት፡ለሕዝቡም፦ከሙታን፡ተነሣ፡እንዳይሉ፥የዃለኛዪቱ፡ስሕተት፡ከፊተኛዪቱ፡ይልቅ፡የከፋች፡ትኾናለችና፡መቃብሩ፡እስከ፡ሦስተኛ፡ቀን፡
ድረስ፡እንዲጠበቅ፡እዘዝ፡አሉት።
65፤ጲላጦስም፦ጠባቂዎች፡አሏችኹ፤ኼዳችኹ፡እንዳወቃችኹ፡አስጠብቁ፡አላቸው።
66፤እነርሱም፡ኼደው፡ከጠባቂዎች፡ጋራ፡ድንጋዩን፡ዐትመው፡መቃብሩን፡አስጠበቁ።
== '''ምዕራፍ ፳፰''' ==