ከ«ኡሩካጊና» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

40 bytes added ፣ ከ1 ዓመት በፊት
no edit summary
 
[[Image:Issue of barley rations.JPG|thumb|300px|የኡሩካጊና ገብስ መቁነን ሰነድ ከ፬ኛው ዓመት፦ ለአዋቂዎች 15-20 ሊተር፣ ለሕጻናት 10 ሊተር ያሕል በየወሩ ይላል።]]
 
'''ኡሩካጊና''' ([[ሱመርኛ]]፦ 𒌷𒅗𒄀𒈾፤ ወይም '''ኡሩ-ኢኒም-ጊና'''? 2102-2095 ዓክልበ. ገደማ የነገሠ) በ[[ሱመር]] ውስጥ የ[[ላጋሽ]] ከተማ ገዢ ንጉስ ነበረ። የ[[ሉጋላንዳ]] መረን ግዛት በወደቀ ጊዜ፣ ኡሩካጊና በላጋሽ ንጉስ ሆነ።
 
ኡሩካጊና ያዋጀው ሕገ ፍትሕ (2098 ዓክልበ. ግ.) በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያው የ[[ሕገ መንግሥት]] ሰነድ ነው። ሰነዱ እራሱ ገና አልተገኘም፤ ነገር ግን ለዜጎቹ አንዳንድ መብት እንደ ፈቀደላቸው ይታወቃል። ለምሳሌ ለመበለትና ለደሀ አደጎች ቀረጥ እንዳስቀረላቸው ድሆችንም ከሃብታሞች አራጣ እንደጠበቃቸው ይታወቃል። ከተማውም ለሞተ ሰው መቃብር ወጪውን ለመክፈል ተገደደ።<ref>{{cite web|url=http://history-world.org/reforms_of_urukagina.htm |title=The Reforms of Urukagina |publisher=History-world.org |date= |accessdate=2009-02-17}}</ref> በተጨማሪ 1 ሚስት ቀድሞ ብዙ ባሎችን የምታገባበትን ልማድ (አእኑስያ ጋብቻን) ከለከለ።
8,739

edits