ከ«ሪሙሽ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
 
መስመር፡ 3፦
'''ሪሙሽ''' ከ2064 እስከ 2056 ዓክልበ. ግድም ድረስ ([[ኡልትራ አጭር አቆጣጠር]]) የ[[አካድ]] ንጉሥ ነበረ። የ[[ታላቁ ሳርጎን]] ልጅና ተከታይ ነበር። እናቱ ምናልባት ንግሥት [[ታሽሉልቱም]] ነበረች። የሱመር ነገሥታት ዝርዝር ቅጂዎች ለ7፥ 9 ወይም 15 ዓመታት እንደ ገዛ ቢሉንም፣ በሥነ ቅርስ ከዘመኑ የተገኙት ሰነዶች አንድ የዓመት ስም ብቻ ተገኝቷል፤ እሱም «[[አዳብ]] የጠፋበት ዓመት» ይባላል።
 
በአባቱ ሳርጎን መሞት ሪሙሽ ንጉሥ በሆነበት ወቅት ሳርጎን አሸንፎ የገዛቸው አገራት ሁሉ በአመጽ ተነሡ። ሪሙሽ የ[[ኡር]] ገዥ ካኩ፣ የ[[ላጋሽ]] ገዥ ኪቱሺድ፣ የ[[ካዛሉ]] ገዥ አሻረድ፣ የ[[አዳብ]] ገዥ መስኪጋላ፣ የ[[ዛባላም]] ገዥ ሉጋል-ጋልዙ ሁላቸውን በዘመቻዎች ማረካቸው፣ በነዚያ ከተሞች ብዙ ሰዎችን ገደለ። የ[[ማርሐሺ]] ገዢ አባልጋማሽና ሻለቃው ሲድጋው ከ[[አዋን]] ገዥ ኤማህሲኒ ጋር በአመጽ ተነሥተው ከ[[ሱስን]]ና ከአዋን መካከል በውግያ ተሸነፉ። አካዳውያን ከኤላምና ከማርሐሺ 30 [[ምና]] [[ወርቅ]]፣ 3600 ምና ብርና 300 ባርዮቭ ማረኩ። ሪሙሽ አመጸኞቹን በ[[ሱመር]]ና በ[[ኤላም]] ቢያሸንፍም፣ ከ[[ሐቡር ወንዝ]] ስሜን ግን ሥልጣኑን ለመስፋፋት አልቻለም። በመጨረሻ በራሱ ሎሌዎች በግድያ ሞቶ ወንድሙ [[ማኒሽቱሹ]] እንደ ተከተለው ይመስላል።
 
{{S-start}}