ከ«ዔግሎም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
 
መስመር፡ 6፦
እስራኤላውያን እንደገና ወደ እግዚአብሐር ሲጮኹ፣ [[ብንያማዊ]]ው የጌራ ልጅ [[ናዖድ]] ግራኙ ይነሣል። እሱ ሰይፉን ደብቆ ለወፍራም ንጉሡ ግብርን አስመስሎት ገደለው። ይህ የተደረገበት ቦታ ጌልገላ ተባለ ሲል (3:19)፣ የ[[ኢያሪኮ]] ዙሪያ ማለት ነው። ከዚህ በኋላ ናዖድ ወደ ሴይሮታ (3:26) እና ወደ ተራራማ ኤፍሬም አገር (3:27) አምልጦ እስራኤላውያን ከዚያ ወረዱና የ[[ዮርዳኖስ ወንዝ]] መሻገርያ ይዘው (3:28) አሥር ሺህ ሞዓባውያንን ገደሉ። አገሩም 80 ዓመት ነጻ ነበር (1439-1359 ዓክልበ.)።
 
በቅደም-ተከተል ሲመለከት፣ እስራኤል ለዔግሎን የተገዙባቸው 18 ዓመታት የ[[ግብጽ]] ፈርዖን [[3 ቱትሞስ]] በ[[ሶርያ]] አካባቢ ይዘመት ነበር። በተለይ በአንድ ዘመቻ በ1449 ዓክልበ. በከነዓን በ[[ሻሱ]] ወገን ላይ እንደ ዘመተ ይዘግባል። «ሻሱ» ማለት «ዘላኖች» ሲሆን አንዳንዴ በሞዓብ ወይም [[ኤዶምያስ]]፣ አንዳንዴም ከዮርዳኖስ ምዕራብ ተገኙ። በአንድ አስተሳሰብ ሻሱ ሞዓባአውያንሞዓባውያን ነበሩ፤ ሌሎች ግን የእስራኤል ወላጆች ያደርጓቸዋል። እነዚህም ሻሱ ከ[[ሐቢሩ]] ብሔር ደግሞ የተለዩ ነበሩ። በመሳፍንት እስራኤላውያን የተገኙባቸው የኤፍሬም ተራሮች ከዮርዳኖስ መሻገርያ በላይ እንደ ነበሩ ይመስላል።
 
በ[[አይሁድ]] ተረቶች ዘንድ በ[[መጽሐፈ ሩት]] ያለችው ሞዓባዊት [[ሩት]] የንጉሥ ዔግሎም ልጅ ነበረች፣ ከዚህም በላይ ዔግሎም የቀድሞው ሞዓብ ንጉሥ (በ[[ሙሴ]] ዘመን) የ[[ባላቅ]] ልጅ ልጅ ነበረ። ሆኖም ለዚህ መረጃ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምንም መሠረት የለም።