ከ«ኢድሪሚ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

10 bytes added ፣ ከ2 ዓመታት በፊት
no edit summary
ለኢድሪሚ ሁለት ሌሎች ጽላቶች ይታወቃሉ። ከነዚህ አንዱ ከኢድሪሚና ከኪዙዋትና ንጉሥ [[ፒሊያ]] መካከል የተደረገው ውል ነው። በዚህ ውል መሠረት ከአንዱ አገር ወደ ሌላው የሸሹት ባርዮች እንዲመለሱ አስቻለ። ባርያውን የያዘው ሰው 500 [[ሰቀል]] [[መዳብ]] ለወንድ፣ 1000 ለሴት ባርያ እንዲከፈል አዘዘ። ወይም የባርያው ጌታ እራሱ ባርያውን ለመያዝ እርስ በርስ ወደ ኪዙዋትናም ሆነ ሙኪሽ መግባቱን በነጻ ፈቀደው።
 
ኢድሪሚ ብዙ ጣኦታት እንዳገለገለ ስለ ጻፈ በእርግጥ አረመኔ ንጉሥ ነበር። በከነዓን ውስጥ ቢቆይ [[ብሉይ ኪዳን]] ከ[[እስራኤል]] ውጭ በዚህ ዘመን ለነገሡት አረመኔ ነገሥታት ብዙ ትኩረት አይሰጥም፤ ግን [[ጎቶንያል]] ፈራጃቸው የሆነበት ወቅት ያሕል ይመስላል። የግብጽ ፈርዖን [[3 ቱትሞስ]] ደግሞ በኢድሪሚ ዘመን በ[[መጊዶ]]ና በሶርያ ይዘምት ነበር።
 
የኢድሪሚ ልጅ [[ኒፕመቃ]] በሙኪሽ ዙፋን ላይ ተከተለው።
20,425

edits