ከ«ተለፒኑ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 21፦
:ልዑል አልጋ ወራሹ - በኲር ልጅ ብቻ ንጉሥ ሆኖ ይጫን! በኲር ልዑል ባይኖር፣ ሁለተኛው ወንድ ልጅ ንጉሥ ይሁን። ነገር ግን ማንም ልዑል ወንድ ልጅ ባይኖር፣ የታላቅዋን ሴት ልጅ ባለቤት ወስደው እሱ ንጉሥ ይሁን!»
 
ተለፒኑ በራሱ በኩል ንጉሥ የሆነው ንግሥቱ የአሙና ልጅ በመሆንዋ ስለ ነበር፣ ይህን መርህ እንደ ሕግ ለማጽናት አስቦ ነበር። በአንድ መስመር ተለፒኑ «በአባቴ ዙፋን ስቀመጥ» ስላለ፣ ማለቱ የንግሥቱ አባት ይሆናል። ''[[የኬጥያውያን ሕግጋት]]'' ቋንቋ ለዚህ ጽላት ተመሳሳይ ሲሆን መጀመርያው እንደ ሕገ መንግሥት የወጣው በተለፒኑ ዘመን እንደ ሆነ ታስቧል። የኬጥያውያን ጉባኤ ወይም «[[ፓንኩሽ]]» (እንደ ምክር ቤት) በዚያ ተመሠረተ።
 
ተለፒኑ ደግሞ ከ[[ኪዙዋትና]] ታላቅ ንጉሥ ኢሽፑታሕሹ ጋራ ስምምነት እንደ ተዋወለ ይታውቃል። የተለፒኑ ሴት ልጅ ሐራፕሺሊ ወይም ሐራፕሼኪ ስትሆን የ[[አሉዋምና]] ሚስት ሆነች፣ ነገር ግን በተለፒኑ ላይ ስላመጹ እሱ ወደ ማሊታሽኩር አሳደዳቸው። የተለፒኑ መጀመርያ ተከታይ የዚዳንታ ልጅ ዙሩ ልጅ ታሑርዋይሊ እንደ ሆነ ይመስላል። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ግን አሉዋምና ተከተላቸው። አሉዋምና ከታሑርዋይሊ እንደ ቀደመ የሚል አስተሳሰብ ደግሞ ብዙ ይታያል።