ከ«የቬትናም ጦርነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''የቬትናም ጦርነት''' ከ1948 ዓ.ም. እስከ 1967 ዓ.ም. ድረስ በቬትናም የነበረ ጦርነት ነበር። {{መ...»
 
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Guèrra de Vietnam (1965).png|300px|thumb|የቬትናም ጦርነት በ1957 ዓም]]
'''የቬትናም ጦርነት''' ከ[[1948]] ዓ.ም. እስከ [[1967]] ዓ.ም. ድረስ በ[[ቬትናም]] የነበረ ጦርነት ነበር።
 
ይህ ጦርነት እንደ [[ኮሪያ ጦርነት]] ሳይሆን ከ[[ተመድ]] ምንም በረከት ያላገኘ ሥራ ነበር። ከ[[1946 ዓም የጀኔቭ ጉባኤ]] በኋላ የ[[ፈረንሳይ]] ቅኝ አገር የነበረችው [[የፈረንሳይ ኢንዶቻይና]] በ[[ላዎስ]]፣ [[ካምቦዲያ]]፣ [[ስሜን ቬትናም]]ና [[ደቡብ ቬትናም]] ተከፋፈለች። በቅርቡ ግን ከስሜን ቬትናም (በ[[ሶቪዬት ሕብረት]]ና በ[[ቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ]] ድጋፍ) እና ከደቡብ ቬትናም (በ[[ዩናይትድ እስቴትስ]] ድጋፍ) ኹኔታው ወደ እርስ-በርስ ጦርነት መራ።
 
በአሜሪካዊው ፕሬዚዳንት [[ጆን ኤፍ ኬኔዲ]] ዘመን በየወገኑ የቻይና ወይም የአሜሪካ ሚለታሪ አማካሪዎች በቬትናም ተገኙ። ባጠቃላይ አሜሪካውያን ግን ስለ ቬትናም ባሕል ወይም ታሪክ ያወቁት እምባዛም ነበር።
 
በተለይ ኬኔዲ በጥይት ተገድሎ [[ሊንዶን ጆንሶን]] በ[[ኅዳር]] [[1956]] ዓም ፕሬዚዳንት ከሆነ በኋላ፣ ሰበብ አድርጎ ቬትናም ትልቅ የአሜሪካ ጦርነት እንዲሆን አሰበ። በ[[ነሐሴ]] ወር 1956 ዓም ስሜኑን በቦምብ መደብደብ ጀመረ፣ ይህ እስከ [[1961]] አም ድረስ ያለመቋረጥ ተቀጠለ። ከ[[1957]] ዓም ጀምሮ ጆንሶን ብዙ የአሜሪካ ወጣት ልጆች ወደ ሥራዊት በግዴታ ምዝገባ አስገብቶ ወደ ቬትናም ጦርነት ይላኩ ነበር።
 
ከ[[1960]] ዓም ጀምሮ አሜሪካ በስሜን ቬትናም ላይ እንደማይሸንፍ ግልጽ ሆነ። በዚህም ሰዓት በአሜሪካዊ ሕዝብ አስተያየት ትልቅ ጸረ-ጦርነት እንቅስቃሴ ተነሣ። ነገር ግን የአሜሪካ መንግሥት ጦርነቱን አላስጨረሱም። ብዙ የማያስፈልግ መከራ ተደረገ። ከደቡብም ቬትናም ሕዝብ ግማሹ ስሜኑን ቬትናም ከአሜሪካውያን በላይ እንደ መረጡ ይመስል ነበር።
 
በ1961 ዓም በተደረገ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ የጆንሶን [[ዴሞክራት]] ወገን በጭራሽ ተሸነፈ። አዲሱ ፕሬዚዳንት [[ሪቻርድ ኒክሰን]] እንደ ቃሉ ወታደሮች ከቬትናም ማስወጣት ጀመረ። ይህ ግን እጅግ ቀስ ብሎ ተደረገ። በ[[1962]] ዓም ደግሞ የአሜሪካና የደቡብ ቬትናም ኃያላት ወደ ካምቦዲያ ገብተው ወረሩ፤ ከዚህ አንሥቶ በአሜሪካ ትልቅ ተቃውሞች ተደረጉ።
 
በታህሳስ ወር [[1965]] ዓም ጦርነት ሳይጨርስ ኒክሰን ስሜኑ ቬትናም በፍጹም እንደ ምንጣፍ በቦምብ እንዲደበደብ አዘዘ። አሁን ለዚህ መልስ ተቃወሞቹ የተደረጉ በአለም ዙሪያና በተለይ በ[[አውሮፓ]] ተደረጉ። በመጨረሻ የ[[ምዕራብ ጀርመን]] ፕሬዚዳንት [[ቪሊ ብራንት]] ለኒክሰን ተናግሮ መደብደቡን አሁን ካልጨረስክ የአውሮፓ ግንኙነቶችህ በአደጋ ውስጥ ገብተው ነበር ብሎ አሳመነው።<ref>Edward W. Knappman, ed. South Vietnam: Volume 7, US-Communist Confrontation in Southeast Asia 1972–1973. p. 226.</ref> መደብደቡም በዚያች ቀን ተወ፤ በአንድ ወርም ውስጥ የአሜሪካ ሥራዊት በሙሉ ከቬትናም ወጡ።
 
ከዚህ በኋላ እርስ-በርስ ጦርነት ከስሜንና ደቡብ መካከል እስከ 1967 ዓም ድረስ የስሜኑ ኃያላት [[ሳይጎን]]ን እስከያዙ ድረስ ተቀጠለ፤ ከ1967 ዓም ጀምሮ አንድ የተዋሀደ አገር [[ቬትናም]] ሆኗል።
 
{{መዋቅር-ታሪክ}}