ከ«ቴሌቪዥን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 22፦
በ[[1927 እ.ኤ.አ.]] [[ኸርበርት አይቭስ]] የተሰኘው የ[[ቤል ላብራቷር]] ተቀጣሪ 16 የምስል ገጽታ በሰከንድ ከ[[ዋሽንግተን ዲሲ]] ወደ [[ኒውዮርክ ከተማ]] በሽቦ መላክ ቻለ። ቀጠል አድርጎም በ[[ራዲዮ]] ወደ [[ዊፓኒ]] [[ኒው ጀርሲ]] ለመላክ በቃ። በዚያው አመት [[ፊሎ ፍራንስዎርዝ]] የመጀመሪያውን የተሟላና በኤሌክትሪክ [[ስካኒንግ]] ብቻ የሚስራውን የቴሌቭዥን ስርዓት በተግባር አዋለ።.በጥር 1928 እ.ኤ.አ. (1920 ዓም) መጀመርያው የቴሌቪዥን ማሰራጫ ጣቢያ በ[[ስከነክተዲ]]፣ [[ኒው ዮርክ]] ተከፈተ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ያሰራጫል።
 
በርግጥም የመጀመሪያው በሰፊው ተግባራዊ የሆነ የቴሌቭዥን ስርዓት ስራ ላይ የዋለው በ[[ጀርመን]] አገር ሲሆን ይኸውም በ[[1929 እ.ኤ.አ.]] ነው። በ[[1936 እ.ኤ.አ.]] ([[1928]] ዓም) ጀርመን ሃገር ተደርጎ የነበረውን የ[[ኦሎምፒክ ውድድር]] በቴሌቭዥን ሊሰራጭ ቻለ፣ ህዝቡም ውድድሩን እቤቱ ሆኖ ቀጥታ ሲካሄድ ለማየት ቻለ።
 
ከዚያ መጀመርያው ጥቁርና-ነጭ ፕሮግራሚንግ በ[[ዩናይትድ ኪንግደም]] 1928 ዓም፤ በአሜሪካ 1933 ዓም ተደረገ። በ[[አፍሪካ]] መጀመርያው ጣቢያዎች በ[[1952]] ዓም በ[[ናይጄሪያ]]ና [[ደቡብ ሮዴዝያ]] (አሁን [[ዚምባብዌ]]) ተሰራጩ፣ በ[[ኢትዮጵያ]] የቴሌቪዥን ስርጭት አገልግሎት ([[ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን]]) የጀመረው በ[[1956]] ዓም ሆነ።