ከ«ካሣውያን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''ካሣውያን''' (አካድኛ፦ ካሹ፣ ካሥኛ፦ ጋልዙ) በጥንት ከዛግሮስ ተራሮች (ኢራን) የመጣና ደ...»
(No difference)

እትም በ16:37, 22 ኖቬምበር 2018

ካሣውያን (አካድኛ፦ ካሹ፣ ካሥኛ፦ ጋልዙ) በጥንት ከዛግሮስ ተራሮች (ኢራን) የመጣና ደቡብ መስጴጦምያን (ኢራቅን) የገዛ ብሔር ነበሩ።

ቋንቋቻው ካሥኛ የተጻፈ ቋንቋ እንደ ነበር አይመስልም፤ ስለርሱ ከስሞቻቸውና እጅግ ጥቂት ቃላት በስተቀር ዕውቀት የለንም። ከምናውቀው ትንሽ ምጠን ግን ካሥኛ ከሌሎቹ ልሳናት ጋር ዝምድና እንደ ነበረው አይታስብም። የሴማዊ ቋንቋዎች ወይንም የሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ዘመድ አይመስልም።

ከባቢሎን ውድቀት (1507 ዓክልበ.) በፊት

ካሣውያን መጀመርያ የሚጠቀሱ በባቢሎን ንጉሥ ሳምሱ-ኢሉና ፱ኛው ዓመት ስም «ሳምሱ-ኢሉና የካሣውያን ሥራዊት ያሸነፈበት ዓመት» ወይም 1654 ዓክልበ. ሊታይ ይችላል። እንዲሁም ተከታዩ አቢ-ኤሹሕ ምናልባት 1621 ዓክልበ. ግድም ካሣውያንን እንዳሸነፈ ዘግቧል።

በጥንታዊ ነገሥታት ዝርዝሮች በኩል የካሣዋያን ነገሥታት በንጉሥ «ጋንዳሽ» ጀመሩ። እንዲሁም በኒፑር በተገኘ በአንዱ ተማሪ ጽሑፍ ዘንድ (700 ዓክልበ ግ.)፣ «ጋዳሽ» ከ«ባባላም» ጥፋት በኋላ «የአለም አራት ሩቦች፣ የሱመርአካድና ባቢሎን ንጉሥ» ሆነ። ይህ ግን ከብዙ ዘመን በኋላ በመጻፉ እንደ ትክክል መረጃ አይቆጠረም። ብዙ መምህሮች አሁን እንደሚያስቡት፣ ከጋንዳሽ እስከ 2 አጉም ድረስ የተዘረዘሩት ነገሥታት ከባቢሎን ውድቀት በፊት በዛግሮስ ተራሮች የገዙት ነበሩ።

እነዚህም ቅድመኞቹ ካሣዊ ነገስታት ስሞች ከተለያዩ ጥንታዊ ዝርዝሮች ታውቀዋል። ዝምድናዎቹም ከአጉም-ካክሪሜ ጽላት ጽሑፍ ተገኝተዋል፦

  • ጋንዳሽ «26 ዓመት»
  • ታላቁ 1 አጉም «22 ዓመት»
  • 1 ካሽቲሊያሹ «22 ዓመት» «የታላቁ አጉም ልጅ»
  • አቢ-ራታሽ «የካሽቲሊያሽ ልጅ»
  • 2 ካሽቲሊያሹ ?
  • ኡዚጉሩማሽ «የአቢ-ራታሽ ልጅ ልጅ»
  • ሓርባ-<...>
  • <...>ኢፕ<...>
  • <...> (2 አጉም ካክሪሜ? «የኡሺጉሩማሽ ልጅ»)

ከዚህ በተረፈ ከአጉም ካክሪሜ በፊት ስለ ነበሩት ስሞች ሌላ መረጃ አልተገኘም። ጋንዳሽ የ«ባባላም» ወይም ባቢሎን ገዢ ሳይሆን ፣ ምናልባት ከሳምሱ-ኢሉማ ጋር በ1654 ዓክልበ. ገደማ የታገለው አለቃ ይሆናል የሚል አስተሳሰብ አሁን ዘመናዊ ነው፣ ማስረጃ ግን ገና አልተገኘም። እንደገና «ካሽቲሊያሽ» የተባለ ንጉሥ በኻና አገር (ተርቃ) ዝርዝር ላይ ስላለ (1621-1599 ዓክልበ.ግ.) ምናልባት ካሣውያን ለጊዜው በዚያ ኤፍራጥስ ወንዝ አገር ላይ መቀመጫ እንዳገኙ ታስቧል።

በአጉም-ካክሪሜ ጽሑፍ ማዕረጉ «የካሣውያንና የአካዳውያን ንጉሥ፣ የባቢሎኒያ ንጉሥ፣ ቱፕልያሽን (ኤሽኑናን) የሰፈረው፣ የአልማንና የፓዳን ንጉሥ፣ እና የጉታውያን ሞኞች ንጉሥ» ይሰጣል። ከባቢሎን ውድቀት ቀጥሎ መጀመርያው እዚያ የነገሠው ይታስባል። ሌሎች ወደ ስሜን የተዘረዘሩት ብሔሮች - ኤሽኑና፣ አልማን፣ ፓዳን፣ ጉታውያን - ከዚያ በፊት በካሣያን ገዥነት ሥር እንደ ሆኑ ይቻላል። የ«አልማን»ና «ፓዳን» መታወቂያዎች እርግጠኛ አይደሉም፤ አንዳንድ መምህሮች የዛግሮስ ብሔሮች ይሆናሉ ሲሉ፣ ሆኖም የፓዳን-አራም አገር (ካራን አካባቢ) ያሳስባሉ።

ከባቢሎን ውድቀት (1507 ዓክልበ.) በኋላ