ከ«የባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 34፦
 
አንድ ሌላ ጽላት A-117 እንደ ጽላት «ለ» ያላቸውን ስሞች ከአሦራዊ ነገሥታት ዘመናት ጋራ ለማስማማት ይሞክራል፣ ሆኖም በትክክል አልተስማሙም። ከ1675 እስከ 1561 ዓክልበ ያህል ድረስ የገዙት አሦር ነገሥታት የዘመን ባልንጀሮቻቸው ቢላቸውም፣ ይህ ልክ እንደማይሆን ሊታወቅ ይቻላል።
 
በአንድ ሰነድ በፐሽጋልዳራመሽ ፯ኛው ዓመት ወንድሙ አዳራጋላማ ደግሞ የጋርዮሽ ንጉሥ ይባላል። ከሌላ ሰነድ አዳራጋላማ ብቻ ንጉሥ የሆነው ከፐሽጋልዳራመሽ 29ኛው አመት በኋላ ነበር። ስለዚህ ወንድሞቹ ለ22 አመት ያህል የጋርዮሽ ዘመን ስለነበራቸው፣ ብዙ የሥርወ መንግሥቱ ነገሥታት ከተከታዮቻቸው ጋራ ረጅም ጋርዮሽ ዘመናት እንዳገኙ ይቻላል።
 
ከዚህ በላይ ስለነዚህ ነገሥታት የምናውቀው ጥቂት ብቻ ነው።
Line 42 ⟶ 40:
* ዳምቂ-ኢሊሹ፦ የአሚ-ዲታና መጨረሻ አመት ስም «የዳምቂ-ኢሊሹ ኃያላት የሠሩት ግድግዳ ያፈረሰበት አመት» ተባለ። የዳምቂ-ኢሊሹ ስም የቀድሞ ኢሲን መጨረሻ ንጉስ [[ዳሚቅ-ኢሊሹ]]ን (1731-1709) ያሳስባል።
* ጉልኪሻር ከባቢሎን መጨረሻ ንጉሥ ሳምሱ-ዲታና ጋር እንደ ታገለ በአንድ ታሪክ ጽላት ተቀረጸ። የብርጭቆ አሠራር የሚገልጽ አንድ ጽላት «ጉልኪሻር ዘውድ ከተጫነበት ዓመት በኋላ በሆነው ዓመት» ተጽፎ ተገኝቷል። ከብዙ መቶ ዘመናት በኋላ በነገሠው በ[[ኤንሊል-ናዲን-አፕሊ]] ዘመን (1113-1109 ዓክልበ.) በተጻፈ ሰነድ ዘንድ፣ ጉልኪሻር የመቅደስን ርስት ከ696 ዓመታት በፊት እንደ ወሰነ ይጠቅሳል፤ በውነት ግን 400 ያህል ዓመታት እንዳለፉ ይሆናል።
* ፐሽጋልዳራመሽ እና አዳራጋላማ የጉልኪሻር ልጆች ይባላሉ። ብዙ ሰነዶች ከዘመኖቻቸው ተገኝተዋል። በአንድ ሰነድ በፐሽጋልዳራመሽ ፯ኛው ዓመት ወንድሙ አዳራጋላማ ደግሞ የጋርዮሽ ንጉሥ ይባላል። ከሌላ ሰነድ አዳራጋላማ ብቻ ንጉሥ የሆነው ከፐሽጋልዳራመሽ 29ኛው አመት በኋላ ነበር። ስለዚህ ወንድሞቹ ለ22 አመት ያህል የጋርዮሽ ዘመን ስለነበራቸው፣ ብዙ የሥርወ መንግሥቱ ነገሥታት ከተከታዮቻቸው ጋራ ረጅም ጋርዮሽ ዘመናት እንዳገኙ ይቻላል። አዳራጋላማ በካሣውያንና በኤላማውያን ላይ ድል እንዳደረገ ይታወቃል።
* ኤዓ-ጋሚል በካሣውያን ንጉሥ [[ኡላም-ቡርያሽ]] በ1463 ዓክልበ. ግድም ወደ [[ኤላም]] እንደ ተባረረ ይዘገባል።