ከ«ቅዱስ ጴጥሮስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 262፦
22፤ውሻ፡ወደ፡ትፋቱ፡ይመለሳል፥ደግሞ፦የታጠበች፡ዕሪያ፡በጭቃ፡ለመንከባለል፡ትመለሳለች፡እንደሚባል፡እውነተኛዎች፡ምሳሌዎች፡ኾኖባቸዋል።
==ምዕራፍ ፫==

1-2፤ወዳጆች፡ሆይ፥አኹን፡የምጽፍላችኹ፡መልእክት፡ይህች፡ኹለተኛዪቱ፡ናት።በቅዱሳን፡ነቢያትም፡
ቀድሞ፡የተባለውን፡ቃል፡በሐዋርያታችኹም፡ያገኛችዃትን፡የጌታንና፡የመድኀኒትን፡ትእዛዝ፡እንድታስቡ፡
በኹለቱ፡እያሳሰብዃችኹ፡ቅን፡ልቡናችኹን፡አነቃቃለኹ።
3፤በመጨረሻው፡ዘመን፡እንደ፡ራሳቸው፡ምኞት፡የሚመላለሱ፡ዘባቾች፡በመዘበት፡እንዲመጡ፡ይህን፡በፊት፡ዕወቁ፤
4፤እነርሱም፦የመምጣቱ፡የተስፋ፡ቃል፡ወዴት፡ነው፧አባቶች፡ከሞቱባት፡ጊዜ፥ከፍጥረት፡መዠመሪያ፡
ይዞ፡ዅሉ፡እንዳለ፡ይኖራልና፥ይላሉ።
5፤ሰማያት፡ከጥንት፡ዠምረው፡ምድርም፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ከውሃ፡ተጋጥማ፡በውሃ፡መካከል፡እንደ፡
ነበሩ፡ወደ፟ው፡አያስተውሉምና፤
6፤በዚህም፡ምክንያት፡ያን፡ጊዜ፡የነበረ፡ዓለም፡በውሃ፡ሰጥሞ፡ጠፋ፤
7፤አኹን፡ያሉ፡ሰማያትና፡ምድር፡ግን፡እግዚአብሔርን፡የማያመልኩት፡ሰዎች፡እስከሚጠፉበት፡እስከፍርድ፡
ቀን፡ድረስ፡ተጠብቀው፡በዚያ፡ቃል፡ለእሳት፡ቀርተዋል።
8፤እናንተ፡ግን፡ወዳጆች፡ሆይ፥በጌታ፡ዘንድ፡አንድ፡ቀን፡እንደ፡ሺሕ፡ዓመት፥ሺሕ፡ዓመትም፡እንደ፡
አንድ፡ቀን፡እንደ፡ኾነ፡ይህን፡አንድ፡ነገር፡አትርሱ።
9፤ለአንዳንዶች፡የሚዘገይ፡እንደሚመስላቸው፡ጌታ፡ስለተስፋ፡ቃሉ፡አይዘገይም፥ነገር፡ግን፥ዅሉ፡ወደ፡
ንስሓ፡እንዲደርሱ፡እንጂ፡ማንም፡እንዳይጠፋ፡ወዶ፡ስለ፡እናንተ፡ይታገሣል።
10፤የጌታው፡ቀን፡ግን፡እንደ፡ሌባ፡ኾኖ፡ይመጣል፤በዚያም፡ቀን፡ሰማያት፡በታላቅ፡ድምፅ፡
ያልፋሉ፥የሰማይም፡ፍጥረት፡በትልቅ፡ትኵሳት፡ይቀልጣል፥ምድርም፡በርሷም፡ላይ፡የተደረገው፡ዅሉ፡
ይቃጠላል።
11-12፤ይህ፡ዅሉ፡እንዲህ፡የሚቀልጥ፡ከኾነ፥የእግዚአብሔርን፡ቀን፡መምጣት፡እየጠበቃችኹና፡
እያስቸኰላችኹ፥በቅዱስ፡ኑሮ፡እግዚአብሔርንም፡በመምሰል፡እንደ፡ምን፡ልትኾኑ፡ይገ፟ባ፟ችዃል፧ስለዚያ፡ቀን፡ሰማያት፡ተ
ቃጥለው፡ይቀልጣሉ፡የሰማይም፡ፍጥረት፡በትልቅ፡ትኵሳት፡ይፈታል፤
13፤ነገር፡ግን፥ጽድቅ፡የሚኖርባትን፡ዐዲስ፡ሰማይና፡ዐዲስ፡ምድር፡እንደተስፋ፡ቃሉ፡እንጠብቃለን።
14፤ስለዚህ፥ወዳጆች፡ሆይ፥ይህን፡እየጠበቃችኹ፡ያለነውርና፡ያለነቀፋ፡ኾናችኹ፡በሰላም፡በርሱ፡እንድትገኙ፡
ትጉ፥
15፤የጌታችንም፡ትዕግሥት፡መዳናችኹ፡እንደ፡ኾነ፡ቍጠሩ።እንዲህም፡የተወደደው፡ወንድማችን፡ጳውሎስ፡
ደግሞ፡እንደተሰጠው፡ጥበብ፡መጠን፡ጻፈላችኹ፥በመልእክቱም፡ዅሉ፡ደግሞ፡እንደ፡ነገረ፡ስለዚህ፡ነገር፡
ተናገረ።
16፤በእነዚያ፡ዘንድ፡ለማስተዋል፡የሚያስቸግር፡ነገር፡አለ፥ያልተማሩትና፡የማይጸኑትም፡ሰዎች፡ሌላዎችን፡
መጻሕፍት፡እንደሚያጣምሙ፡እነዚህን፡ደግሞ፡ለገዛ፡ጥፋታቸው፡ያጣምማሉ።
17፤እንግዲህ፡እናንተ፥ወዳጆች፡ሆይ፥ይህን፡አስቀድማችኹ፡ስለምታውቁ፥በዐመፀኛዎቹ፡ስሕተት፡ተስባችኹ፡ከራሳችኹ፡ጽናት፡እንዳትወድቁ፡ተጠንቀቁ፤18፤ነገር፡ግን፥በጌታችንና፡በመድኀኒታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋና፡ዕውቀት፡እደጉ።ለርሱ፡አኹንም፡
እስከ፡ዘለዓለምም፡ቀን፡ድረስ፡ክብር፡ይኹን፤አሜን፨