ከ«ቅዱስ ጴጥሮስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 180፦
14፤በፍቅር፡አሳሳም፡ርስ፡በርሳችኹ፡ሰላምታ፡ተሰጣጡ።በክርስቶስ፡ላላችኹ፡ለኹላችኹ፡ሰላም፡
ይኹን።አሜን፨
==የሁለተኛዪቱ የጴጥሮስ መልክት ምዕራፍ ==

1፤የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ባሪያና፡ሐዋርያ፡የኾነ፡ስምዖን፡ጴጥሮስ፥በአምላካችንና፡በመድኀኒታችን፡በኢየሱስ፡
ክርስቶስ፡ጽድቅ፡ካገኘነው፡ጋራ፡የተካከለ፡የክብር፡እምነትን፡ላገኙ፤
2-3፤የመለኮቱ፡ኀይል፥በገዛ፡ክብሩና፡በበጎነቱ፡የጠራንን፡በማወቅ፥ለሕይወትና፡እግዚአብሔርን፡ለመምሰል፡
የሚኾነውን፡ነገር፡ዅሉ፡ስለ፡ሰጠን፥በእግዚአብሔርና፡በጌታችን፡በኢየሱስ፡ዕውቀት፡ጸጋና፡ሰላም፡
ይብዛላችኹ።
4፤ስለ፡ክፉ፡ምኞት፡በዓለም፡ካለው፡ጥፋት፡አምልጣችኹ፡ከመለኮት፡ባሕርይ፡ተካፋዮች፡በተስፋ፡ቃል፡
እንድትኾኑ፥በእነዚያ፡ክብርና፡በጎነት፡የተከበረና፡እጅግ፡ታላቅ፡የኾነ፡ተስፋን፡ሰጠን።
5፤ስለዚህም፡ምክንያት፡ትጋትን፡ዅሉ፡እያሳያችኹ፡በእምነታችኹ፡በጎነትን፡ጨምሩ፥
6፤በበጎነትም፡ዕውቀትን፥በዕውቀትም፡ራስን፡መግዛት፥ራስንም፡በመግዛት፡መጽናትን፥በመጽናትም፡
እግዚአብሔርን፡መምሰል፥
7፤እግዚአብሔርንም፡በመምሰል፡የወንድማማችን፡መዋደድ፥በወንድማማችም፡መዋደድ፡ፍቅርን፡ጨምሩ።
8፤እነዚህ፡ነገሮች፡ለእናንተ፡ኾነው፡ቢበዙ፥በጌታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ዕውቀት፡ሥራ፡ፈቶችና፡ፍሬ፡
ቢሶች፡እንዳትኾኑ፡ያደርጓችዃልና፤
9፤እነዚህ፡ነገሮች፡የሌሉት፡ዕውር፡ነውና፥በቅርብም፡ያለውን፡ብቻ፡ያያል፥የቀደመውንም፡ኀጢአቱን፡
መንጻት፡ረስቷል።
10፤ስለዚህ፥ወንድሞች፡ሆይ፥መጠራታችኹንና፡መመረጣችኹን፡ታጸኑ፡ዘንድ፡ከፊት፡ይልቅ፡
ትጉ፤እነዚህን፡ብታደርጉ፡ከቶ፡አትሰናከሉምና።
11፤እንዲሁ፡ወደዘለዓለሙ፡ወደጌታችንና፡መድኀኒታችን፡ወደኢየሱስ፡ክርስቶስ፡መንግሥት፡መግባት፡
በሙላት፡ይሰጣችዃልና።
12፤ስለዚህ፥እነዚህን፡ነገሮች፡ምንም፡ብታውቁ፥በእናንተም፡ዘንድ፡ባለ፡እውነት፡ምንም፡ብትጸኑ፥ስለ፡
እነዚህ፡ዘወትር፡እንዳሳስባችኹ፡ቸል፡አልልም።
13፤ዅልጊዜም፡በዚህ፡ማደሪያ፡ሳለኹ፡በማሳሰቤ፡ላነቃችኹ፡የሚገ፟ባ፟ኝ፡ይመስለኛል።
14፤ጌታችን፡ኢየሱስ፡ክርስቶስ፡እንዳመለከተኝ፡ከዚህ፡ማደሪያዬ፡መለየቴ፡ፈጥኖ፡እንዲኾን፡ዐውቃለኹና።
15፤ከመውጣቴም፡በዃላ፡እነዚህን፡ነገሮች፡እንድታስቡ፡በየጊዜው፡ትችሉ፡ዘንድ፡እተጋለኹ።
16፤የርሱን፡ግርማ፡አይተን፡እንጂ፡በብልኀት፡የተፈጠረውን፡ተረት፡ሳንከተል፡የጌታችንን፡የኢየሱስ፡
ክርስቶስን፡ኀይልና፡መምጣት፡አስታወቅናችኹ።
17፤ከገናናው፡ክብር፦በርሱ፡ደስ፡የሚለኝ፡የምወደ፟ው፡ልጄ፡ይህ፡ነው፡የሚል፡ያ፡ድምፅ፡በመጣለት፡ጊዜ፡
ከእግዚአብሔር፡አብ፡ክብርንና፡ምስጋናን፡ተቀብሏልና፤
18፤እኛም፡በቅዱሱ፡ተራራ፡ከርሱ፡ጋራ፡ሳለን፡ይህን፡ድምፅ፡ከሰማይ፡ሲወርድ፡ሰማን።
19፤ከርሱም፡ይልቅ፡እጅግ፡የጸና፡የትንቢት፡ቃል፡አለን፤ምድርም፡እስኪጠባ፡ድረስ፡የንጋትም፡ኮከብ፡
በልባችኹ፡እስኪወጣ፡ድረስ፥ሰው፡በጨለማ፡ስፍራ፡የሚበራን፡መብራት፡እንደሚጠነቀቅ፡ይህን፡ቃል፡
እየጠነቀቃችኹ፡መልካም፡ታደርጋላችኹ።
20፤ይህን፡በመዠመሪያ፡ዕወቁ፤በመጽሐፍ፡ያለውን፡ትንቢት፡ዅሉ፡ማንም፡ለገዛ፡ራሱ፡ሊተረጕም፡
አልተፈቀደም፤
21፤ትንቢት፡ከቶ፡በሰው፡ፈቃድ፡አልመጣምና፥ዳሩ፡ግን፡በእግዚአብሔር፡ተልከው፡ቅዱሳን፡ሰዎች፡
በመንፈስ፡ቅዱስ፡ተነድተው፡ተናገሩ።
==ምዕራፍ ፪==