ከ«ቅዱስ ጴጥሮስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 46፦
 
==ምዕራፍ ፪==
 
1፤እንግዲህ፡ክፋትን፡ዅሉ፡ተንኰልንም፡ዅሉ፡ግብዝነትንም፡ቅንአትንም፡ሐሜትንም፡ዅሉ፡አስወግዳችኹ፥
2-3፤ጌታ፡ቸር፡መኾኑን፡ቀምሳችኹ፡እንደ፡ኾነ፥ለመዳን፡በርሱ፡እንድታድጉ፡አኹን፡እንደ፡ተወለዱ፡
ሕፃናት፡ተንኰል፡የሌለበትን፡የቃልን፡ወተት፡ተመኙ።
4፤በሰውም፡ወደተጣለ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ግን፡ወደተመረጠና፡ክቡር፡ወደኾነው፡ወደ፡ሕያው፡ድንጋይ፡ወደ፡ርሱ፡እየቀረባችኹ፥
5፤እናንተ፡ደግሞ፡እንደ፡ሕያዋን፡ድንጋዮች፡ኾናችኹ፥በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ለእግዚአብሔር፡ደስ፡የሚያሠኝ፡
መንፈሳዊ፡መሥዋዕትን፡ታቀርቡ፡ዘንድ፡ቅዱሳን፡ካህናት፡እንድትኾኑ፡መንፈሳዊ፡ቤት፡ለመኾን፡ተሠሩ።
6፤በመጽሐፍ፦እንሆ፥የተመረጠና፡የከበረን፡የማእዘን፡ራስ፡ድንጋይ፡በጽዮን፡አኖራለኹ፥በርሱም፡
የሚያምን፡አያፍርም፡ተብሎ፡ተጽፏልና።
7፤እንግዲህ፡ክብሩ፡ለእናንተ፡ለምታምኑት፡ነው፤ለማያምኑ፡ግን፡ዐናጢዎች፡የጣሉት፡ድንጋይ፡ርሱ፡
የማእዘን፡ራስ፡የዕንቅፋትም፡ድንጋይ፡የማሰናከያም፡አለት፡ኾነ፤
8፤የማያምኑ፡ስለ፡ኾኑ፡በቃሉ፡ይሰናከሉበታልና፤ለዚህ፡ደግሞ፡የተመደቡ፡ናቸው።
9፤እናንተ፡ግን፡ከጨለማ፡ወደሚደነቅ፡ብርሃኑ፡የጠራችኹን፡የርሱን፡በጎነት፡እንድትናገሩ፡የተመረጠ፡
ትውልድ፥የንጉሥ፡ካህናት፥ቅዱስ፡ሕዝብ፥ለርስቱ፡የተለየ፡ወገን፡ናችኹ፤
10፤እናንተ፡ቀድሞ፡ወገን፡አልነበራችኹም፡አኹን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ወገን፡ናችኹ፤እናንተ፡ምሕረት፡
ያገኛችኹ፡አልነበራችኹም፡አኹን፡ግን፡ምሕረትን፡አግኝታችዃል።
11፤ወዳጆች፡ሆይ፥ነፍስን፡ከሚዋጋ፡ሥጋዊ፡ምኞት፡ትርቁ፡ዘንድ፡እንግዳዎችና፡መጻተኛዎች፡እንደ፡
መኾናችኹ፡እለምናችዃለኹ፤
12፤ስለሚመለከቱት፡ስለ፡መልካም፡ሥራችኹ፥ክፉ፡እንደምታደርጉ፡በዚያ፡እናንተን፡በሚያሙበት፡
ነገር፥በሚጐበኝበት፡ቀን፡እግዚአብሔርን፡ያከብሩት፡ዘንድ፡በአሕዛብ፡መካከል፡ኑሯችኹ፡መልካም፡ይኹን።
13፤ስለ፡ጌታ፡ብላችኹ፡ለሰው፡ሥርዐት፡ዅሉ፡ተገዙ፤ለንጉሥም፡ቢኾን፥ከዅሉ፡በላይ፡ነውና፤
14፤ለመኳንንትም፡ቢኾን፥ክፉ፡የሚያደርጉትን፡ለመቅጣት፡በጎም፡የሚያደርጉትን፡ለማመስገን፡ከርሱ፡
ተልከዋልና፥ተገዙ።
15፤በጎ፡እያደረጋችኹ፥የማያውቁትን፡ሞኞች፡ዝም፡ታሠኙ፡ዘንድ፡እንዲህ፡የእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡ነውና፤
16፤ሐራነት፡ወጥታችኹ፡እንደእግዚአብሔር፡ባሪያዎች፡ኹኑ፡እንጂ፡ያ፡ሐራነት፡ለክፋት፡መሸፈኛ፡እንዲኾን፡
አታድርጉ።
17፤ዅሉን፡አክብሩ፥ወንድሞችን፡ውደዱ፥እግዚአብሔርን፡ፍሩ፥ንጉሥን፡አክብሩ።
18፤ሎሌዎች፡ሆይ፥ለበጎዎችና፡ለገሮች፡ጌታዎቻችኹ፡ብቻ፡ሳይኾን፡ለጠማማዎች፡ደግሞ፡በፍርሀት፡ዅሉ፡
ተገዙ።
19፤በግፍ፡መከራን፡የሚቀበል፡ሰው፡እግዚአብሔርን፡እያሰበ፡ሐዘንን፡ቢታገሥ፡ምስጋና፡ይገ፟ባ፟ዋልና።
20፤ኀጢአት፡አድርጋችኹ፡ስትጐሰሙ፡ብትታገሡ፥ምን፡ክብር፡አለበት፧ነገር፡ግን፡መልካም፡አድርጋችኹ፡
መከራን፡ስትቀበሉ፡ብትታገሡ፥ይህ፡ነገር፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ምስጋና፡ይገ፟ባ፟ዋል።
21፤የተጠራችኹለት፡ለዚህ፡ነውና፤ክርስቶስ፡ደግሞ፡ፍለጋውን፡እንድትከተሉ፡ምሳሌ፡ትቶላችኹ፡ስለ፡
እናንተ፡መከራን፡ተቀብሏልና።
22፤ርሱም፡ኀጢአት፡አላደረገም፥ተንኰልም፡በአፉ፡አልተገኘበትም፤
23፤ሲሰድቡት፡መልሶ፡አልተሳደበም፥መከራንም፡ሲቀበል፡አልዛተም፤ነገር፡ግን፥በጽድቅ፡ለሚፈርደው፡
ራሱን፡አሳልፎ፡ሰጠ፤24፤ለኀጢአት፡ሞተን፡ለጽድቅ፡እንድንኖር፥ርሱ፡ራሱ፡በሥጋው፡ኀጢአታችንን፡በዕንጨት፡ላይ፡
ተሸከመ፤[*]፡
25፤በመገረፉ፡ቍስል፡ተፈወሳችኹ።እንደ፡በጎች፡ትቅበዘበዙ፡ነበርና፥አኹን፡ግን፡ወደነፍሳችኹ፡እረኛና፡
ጠባቂ፡ተመልሳችዃል።
[*]፤በግእዝ፡እንዲህ፡ተጽፏል።ወበእንተ፡ኃጥኣዊነ፡ውእቱ፡ተሰቅለ፡ዲበ፡ዕፅ፡በሥጋሁ፡ከመ፡ያውፅአነ፡እምኃጥኣዊነ፡ወበጽድቁ፡
ያሕይወነ።
==ምዕራፍ ፫==