ከ«መጽሐፍ ቅዱስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አንድ ለውጥ 348225 ከ81.234.233.22 (ውይይት) ገለበጠ
Tag: Undo
አንድ ለውጥ 348224 ከ81.234.233.22 (ውይይት) ገለበጠ
Tag: Undo
መስመር፡ 1፦
መጽሐፍ ቅዱስ ነብያት እና ታሪካውያን የጻፉት የክርስትና እና የአይሁዳውያን መጽሓፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በ[[ብሉይ ኪዳን]]ና በ[[አዲስ ኪዳን]] ተከፍሎ 81 መጻሕፍት ያሉት ሲሆን በአንዳንድ እምነቶች ደግሞ 66 ክፍል ብቻ ነው አሉት ብለው ያምናሉ። ከነ[[ዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍት]]ም ጋራ የመጻሕፍት ቁጥር 81 ነው። ዝርዝሩን እንመጣበታለን። መጽሐፍ ቅዱስ ከመቶ 25% የአምላክ ንግግር፣ ከመቶ 25 % የነብያት ንግግር እና ከመቶ 50 % የታሪክ ጽሐፍያን ንግግር ይዟል።
 
== የመጽሐፍ ቅዱስ ምንነት ==
በዚህ ምህዋር እና ዐውድ ላይ “ቀኖና” ስንል የዶግማ ተቃራኒ የሆነውን የሚለወጠው ሕግ ወይም ሥርዓት ሳይሆን የቅዱሳን መጽሐፍትን “መለኪያ” ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው። “ቀኖና” የሚለው ቃል የአማርኛችን ቃል “ካኑን” κανών ከሚል ግሪክ ቃል የተገኘ ነው፤ ይህም ቃል “ካና” κάννα ማለት “አሰመረ” “ለካ” ከሚል የኮይኔ ግሪክ ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ልኬት” ማለት ነው። አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ እንዲሁ ክርስቲያኖች በ 387 ድህረ-ልደት”AD” በካርቴጅ ጉባኤ በመጨመርና በመቀነስ ቀኖና እያሉ ሲያስወጡና ሲያስገቡ ነበር፤ በተለይ የካርቴጅ ጉባኤ መጽሐፍቶችን በሁለት ከፍለው ብሉይ እና አዲስ ብለው አስቀምጠውታል፤ እስቲ ይህንን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦
በ[[እንግሊዝኛ]] ቋንቋ የተለመደው «ባይብል» የሚለው ቃል ከጥንቱ [[የኮይነ ግሪክኛ]] ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ቃሉ የተገኘበት τὰ βιβλία /ታ ቢብሊያ/ የሚለው ሀረግ «መጽሐፍቱ» ወይም «ትንንሽ መጽሐፍት» ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። የዚሁም ቃል መነሻ ከግሪኩ ስም Βύβλος /ቢውብሎስ/ ([[ፓፒሩስ]] ወይም [[ቄጠማ]]፣ የ[[ወረቀት]] ተክል) ሲሆን ይሄ ቃል «ፓፒሩስ» ከተነገደበት ከተማ [[ጌባል]] / ቢውብሎስ ስም መጣ።
 
መጽሐፍ ቅዱስ ለ[[አይሁድና]] [[ክርስትና]] እምነት የእምነት መሰረት የሆኑ ትናንሽ መጽሐፍትን የያዘ አንድ ጥራዝ ነው። በተለምዶ «ብሉይ ኪዳን» በመባል የሚጠራውና በአይሁዳውያን በ24 እና በክርስቲያኖች በ39 መጽሐፍት የሚከፈለው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል በመጀመሪያ በአብዛኛው የተጻፈው በጥንታዊው የ[[ዕብራይስጥ]] ቋንቋ ሲሆን የተጻፉበት ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የተወሰኑ መቶ አመታት ቀደም ብሎ እንደሆነ ይነገራል። እነዚህን መጽሐፍት የጻፉት በወቅቱ የነበሩ የታመኑ አይሁዳውያን ወይም [[እስራኤላውያን]] ናቸው። የመጨረሻዎቹን 27 መጻሕፍት በግሪክኛ የጻፏቸው ክርስቲያኖች ሲሆኑ «አዲስ ኪዳን» በመባል በሰፊው ይታወቃሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ማስረጃም ሆነ በጣም ጥንታዊ የሆኑት ወጎች እንደሚጠቁሙት እነዚህ 66 መጻህፍት የተጻፉት ግብጽ ኃያል ከነበረችበት ጊዜ አንስቶ [[ሮም]] የዓለም ኃያል መንግስት እስከ ነበረችበት ዘመን ባሉት 1600 ዓመታት ውስጥ ነው።
ነጥብ አንድ
“ብሉይ ኪዳን”
ብሉይ ኪዳን ላይ ስላሉት መጽሐፍት የተለያዩ አንጃዎች አንድ አቋም የላቸውም፤ እነርሱን በተናጥን እስቲ እንይ፦
 
በ[[ካቶሊክ ቤተክርስቲያን]] እምነት መሰረት ከ66ቱ መጽሐፍት በተጨማሪ የተካተቱ የተወሰኑ መጽሐፍት ሲኖሩ፣ በ[[ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን]] እነዚህ ተጨማሪ መጻሕፍት (ዲዩቴሮካኖኒካል በመባልም ይታወቃሉ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱትን መጻሕፍት ቁጥር ወደ 81 ያደርሱታል።
A. “የፕሮቴስታንት ቀኖና”
ፕሮቴስታንት የሚቀበለው ሁሉም ጋር ተቀባይነት ያለው አቆጣጠር
የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት 39 ናቸው፤ እነርሱም፦
1. ኦሪት ዘፍጥረት
2. ኦሪት ዘጸአት
3 ኦሪት ዘኁልቁ
4. ኦሪት ዘሌዋውያን
5. ኦሪት ዘዳግም
6. መጽሐፈ ኢያሱ
7. መጽሐፈ መሳፍንት
8. መጽሐፈ ሩት
9. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
10. መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
11. መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
12. መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
13. ዜና መዋዕል ቀዳማዊ
14. ዜና መዋዕል ካልዕ
15. መጽሐፈ ዕዝራ
16. መጽሐፈ ነህምያ
17. መጽሐፈ አስቴር
18. መጽሐፈ ኢዮብ
19. መዝሙረ ዳዊት
20. መጽሐፈ ምሳሌ
21. መጽሐፈ መክብብ
22. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
23. ትንቢተ ኢሳይያስ
24. ትንቢተ ኤርምያስ
25. ሰቆቃው ኤርምያስ
26. ትንቢተ ሕዝቅኤል
27. ትንቢተ ዳንኤል
28. ትንቢተ ሆሴዕ
29. ትንቢተ አሞጽ
30. ትንቢተ ሚክያስ
31. ትንቢተ ኢዮኤል
32. ትንቢተ አብድዩ
33. ትንቢተ ዮናስ
34. ትንቢተ ናሆም
35. ትንቢተ ዕንባቆም
36. ትንቢተ ሶፎንያስ
37. ትንቢተ ሐጌ
38. ትንቢተ ዘካርያስ
39. ትንቢተ ሚልክያስ ናቸው።
 
ከክርስቶስ ስብከት ቀጥሎ ምዕመናን የሆኑት ለረጅም ዘመን ተጨማሪ መጻሕፍቱን ከነ[[መጽሐፈ ሄኖክ]]ና [[ኩፋሌ]] ያንብቡ ነበር። የ[[አይሁድ]] [[ሰንሄድሪን]] ረቢዎች በ100 ዓ.ም. አካባቢ በተለይም ረቢ [[አኪቫ በን ዮሴፍ]] እነዚህን ተጨማሪ መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ቅጂ አጠፉ። እስካሁንም ድረስ በዕብራይስጥ ትርጉም አይታወቁም። አዲስ ኪዳን ከተጻፈ በኋላ፣ ብዙ አጠያያቂ ወንጌሎችና የሌሎች እምነቶች ጽሑፎች ደግሞ ሊሠራጩ ጀመር። [[ግኖስቲክ]] የተባለው እምነት ተከታዮች በተለይ ብዙ ሥነ ጽሑፍ ፈጠሩ፣ ይህ ግን ከኦርቶዶክስ ወንጌል የተዛቡ ትምህርቶች ነበር። በ170 ዓ.ም. በክርስትያኖች ዘንድ የቱ መጻሕፍት ትክክለኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ናቸው? የሚል ጥያቄ ይነሣ ጀመር። [[መሊቶ ዘሳርዲስ]] የተባለ ጳጳስ በዚያን ጊዜ ወደ [[ኢየሩሳሌም]] መጻሕፍት ቤት ጉዞ አድርጎ የ ዕብራውያን መጻሕፍት ምን ምን እንደ ነበሩ ዘገበ። ተጨማሪ መጻሕፍቱ ከዚያ በፊት ስለ ጠፉ አልተዘገቡም። ስለዚህ ከዚህ በቀር ምንም ያልተዘረዘሩት ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ትክክለኛ አይሆኑም የሚል ሀሣብ በ[[ሮሜ መንግሥት]] ክርስቲያኖች ተነሣ። ይህም የአይሁዶች [[ቀኖና]] በ[[ንቅያ ጉባኤ]] ([[317]] ዓ.ም.) በሮሜ መንግሥት ለክርስቲያኖች ጸና።
B. “የአይሁዳውያን ቀኖና”
39 መጽሐፍት አይሁዳውያን እንደጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ 24 የቀኖና መጽሐፍት አርገዋቸዋል፤ አቆጣጠራቸው ግን ይለያል፦
1. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ እና መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ አንድ መጽሐፍ ሻሙኤል ብለው፣
2. መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ እና መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ አንድ መጽሐፍ መላክሂም ብለው፣
3. ዜና መዋዕል ቀዳማዊ እና ዜና መዋዕል ካልዕ አንድ መጽሐፍ ሃያሚን ብለው፣
4. መጽሐፈ ዕዝራ እና መጽሐፈ ነህምያ አንድ መጽሐፍ አዝራ ብለው፣
5. ከሆሴዕ እስከ ሚልኪያስ ያሉት 12 መጽሐፍት አንድ መጽሐፍ ትሬአሳር ብለው ይቆጥሩታል።
 
ከሆሴዕ እስከ ሚልኪያስ ያሉት በአንድ የተጣፉትን 11 መጽሐፍት እና የተጣፉትን 4 መጽሐፍት ስንደምር 15 ይሆናል፤ 15+24= 39 መጽሐፍት ይሆናሉ። አይሁዳውያን መጽሐፍቶቻቸውን “ታንካህ” תַּנַ”ךְ, ሲሉት የሶስቱ መጽሐፍት መነሻ ላይ ያሉት ቃላት መሰረት አርገው ነው፤ እነዚህም “ታ” תַּ ቶራህ፣ “ና” נַ ነቢኢም፣ “ካ” ךְ ኬቱዊም ናቸው። “ቶራህ” תּוֹרָה ማለት “ኦሪት” “ሕግ” “መርሕ” ማለት ነው፣ ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም ያሉትን ለማመልከት ይጠቀሙብታል።
“ነቢኢም” נְבִיאִים ማለት “ነቢያት” ማለት ሲሆን የኢሳያስ ትንቢት፣ የኤርሚያስ ትንቢት፣ የህዝቅኤል ትንቢት ወዘተ ለማመልከት ይጠቀሙብታል።
“ኬቱዊም” כְּתוּבִים ማለት “መጻሕፍት” ማለት ሲሆን የኢዮብ መጽሐፍ፣ የመዝሙር መጽሐፍ፣ የምሳሌ መጽሐፍ፣ የመክብብ መጽሐፍ፣ የመኃልየ መኃልይ መጽሐፍ ወዘተ ለማመልከት ይጠቀሙብታል።
 
C. “የካቶሊክ ቀኖና”
የሮማ ካቶሊክ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 46 ናቸው፤ ካቶሊክ በ 39 ላይ እራሳቸውን የቻሉ 7 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ፦
1. መጽሐፈ ጦቢት፣
2. መጽሐፈ ዮዲት፣
3. መጽሐፈ ጥበብ፣
4. መጽሐፈ ሲራክ፣
5. መጽሐፈ ባሮክ፣
6. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ
7. መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ ናቸው።
 
D. “የኦርቶዶክስ ቀኖና”
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 46 ናቸው፤ የብሉይ ኪዳን መደበኛ የቀኖና መጽሐፍት 39 ሲሆኑ ተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 18 ናቸው፤ ነገር ግን አቆጣረራቸው ልክ እንደ አይሁድ ይለያል። እራሳቸውን የቻሉ 10 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ አቆጣጠራቸው፦
1. መጽሐፈ ሄኖክ፣
2. መጽሐፈ ኩፋሌ(ጁብሊይ)፣
3. መጽሐፈ ጦቢት፣
4. መጽሐፈ ዮዲት፣
5. መጽሐፈ ተግሣጽ፣
6. መጽሐፈ ጥበብ፣
7. መጽሐፈ ሲራክ
8. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ቀዳማይ እና መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ካልዕ፣
9. መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማይ እና መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ፣
10. መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ናቸው።
 
ነባር መጽሐፍት ላይ በመቀነስ ተጨፍልቀው የሚቆጠሩ 2 መጽሐፍት ናቸው፤ እነርሱም፦
11. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማይ እና መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ናቸው፣
12. መጽሐፈ ዕዝራ ቀዳማይ እና መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ(ነህምያ) ናቸው።
 
ከነባር መጽሐፍት ጋር ተደምረው የሚቆጠሩ ደግሞ 8 መጽሐፍት ናቸው፤ እነርሱም፦
13. ከትንቢተ ኢሳይያስ ጋር የሚቆጠረው ጸሎተ ምናሴ ነው።
14. ከትንቢተ ኤርምያስ ጋር የሚቆጠሩ፦ ሰቆቃወ ኤርምያስ፣ ተረፈ ኤርምያስ፣ መጽሐፈ ባሮክ፣ ተረፈ ባሮክ ናቸው።
15. ከትንቢተ ዳንኤል ጋር የሚቆጠሩ መጽሐፈ ሶስና፣ ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ እና ተረፈ ዳንኤል ናቸው።
 
ከ 39 ላይ 8 መጽሐፍት፦ ሳሙኤል ቀዳማይ፣ ሳሙኤል ካልዕ፣ መጽሐፈ ዕዝራ፣ መጽሐፈ ነህምያ፣ ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ትንቢተ ኤርሚያስ፣ ሰቆቃው ኤርሚያስ እና ትንቢተ ዳንኤል ሲቀነሱ 31 መጽሐፍት ይሆናሉ። 31+15= 46 ይሆናል።
 
F. “የሰፕቱአጀንት ቀኖና”
የሰፕቱአጀንት የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና 56 ናቸው፤ የሰፕቱአጀንት”LXX” በ 39 ላይ እራሳቸውን የቻሉ 17 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ፦
1. መጽሐፈ ጦቢት፣
2. መጽሐፈ ዮዲት፣
3. መጽሐፈ ጥበብ፣
4. መጽሐፈ ሲራክ፣
5. መጽሐፈ ባሮክ፣
6. ተረፈ ኤርምያስ፣
7. ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ፣
8. መጽሐፈ ሶስና፣
9. ቤልና ድራጎን፣
10. ጸሎተ ምናሴ፣
11.1ኛ መቃብያን፣
12. 2ኛ መቃብያን፣
13. 3ኛ መቃብያን፣
14. 4ኛ. መቃብያን፣
15. ዕዝራ ሱቱኤል፣
16. የአዛርያ ጸሎት፣
17. መዝሙር 151 ናቸው።
 
G. “የቩልጌት ቀኖና”
ጄሮም በ 382 ድህረ-ልደት በላቲን ቩልጌት ባዘጋጀው ደግሞ የመጽሐፍት ቀኖና 45 ናቸው፤ የቩልጌት በ 39 ላይ እራሳቸውን የቻሉ 6 ጭማሬ መጽሐፍት ሲኖራቸው እነዚህ ጭማሬ፦
1. መጽሐፈ ጦቢት፣
2. መጽሐፈ ዮዲት፣
3.1ኛ መቃብያን፣
4. 2ኛ መቃብያን፣
5. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ቀዳማይ፣
6. መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል ካልዕ
 
== የመጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ባህርያት ==