ከ«ኢትዮጵያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 42፦
ኢትዮጵያ ተፈጥሮ ያደላት ሀገር ናት። ከአፍሪካ ትላልቅ ተራራዎች እንዲሁም ከዓለም ከባህር ጠለል በታች በጣም ጥልቅ ከሆኑ ቦታዎች አንዳንዶቹ ይገኙባታል። [[ሶፍ ዑመር]] ከአፍሪካ ዋሻዎች ትልቁ ሲሆን ፣ [[ዳሎል]] ከዓለም በጣም ሙቅ ቦታዎች አንዱ ነው። ወደ ሰማንኒያ የሚቆጠሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ዛሬ በኢትዮጵያ ይገኛሉ። ከእነዚህም [[ኦሮሞ]]ና [[አማራ]] በብዛት ትልቆቹ ናቸው። ኢትዮጵያ በኣክሱም ሓውልት፣ ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍለው በተሰሩ ቤተ-ክርስትያኖቹዋ እና በ[[ኦሎምፒክ]] የ[[ወርቅ]] ሜዳልያ አሸናፊ አትሌቶቹዋ ትታወቃለች። የ[[ቡና]] ፍሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው በኢትዮጵያ ሲሆን ሀገሪቱዋ በቡናና [[ማር]] አምራችነት በአፍሪካ ቅድሚያ ይዛለች።
 
ኢትዮጵያ ከዓለም ሶስቱ ትላልቅ የአብርሃም ሀይማኖቶች ጋር ታሪካዊ ግንኙነት አላት። [[ክርስትና]]ን በአራተኛው ምዕተ-ዓመት ተቀብላለች። ከሕዝቡ አንድ ሶስተኛውሁለተኛው [[እስላም]] ነው። የመጀመሪያው የእስላም [[ሂጅራ]] ወደ ኢትዮጵያ ነው የተከናወነው። [[ነጋሽ]] በአፍሪካ የመጀመሪያው የእስላም መቀመጫ ናት። እስከ ፲፱፻፸ ዎቹ ድረስ ብዙ [[ቤተ እስራኤል|ቤተ-እስራኤሎች]] በኢትዮጵያ ይኖሩ ነበር። የ[[ራስ ተፈሪ እንቅስቃሴ]] ኢትዮጵያን በትልቅ ክብር ነው የሚያያት።
 
ግርማዊ ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ድህነት በኢትዮጵያ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ሰማኒያ አምስት ከመቶ በላይ የሚሆነው የ[[ናይል]](ኣባይ) ወንዝ ውሀ ከሀገሩ የሚመጣ ቢሆንም በ ፲፱፻፸ ዎቹ በተከሰቱ ድርቆች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ነገር ግን ቀስ በቀስ ሀገሩዋ እያገገመች ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ውስጥ በፍጥነት ከሚያድጉት አንዱ ነው።