ከ«ባቢሎን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 21፦
'''ባቢሎን''' ([[አካድኛ]]፦ ባቢሊ፣ [[ዕብራይስጥ]]፦ ባቤል) በ[[መስጴጦምያ]] የነበረ ጥንታዊ ከተማ ነው። ስሙ በአካድኛ ከ/ባብ/ (በር) እና /ኢሊ/ (አማልክት) ወይም «የአማልክት በር» ማለት ነበር። በዕብራይስጥ ግን ስሙ «ደባልቋል» እንደ ማለት ይመስላል (ዘፍ. 11:9)። «ባቢሎን» የሚለው አጠራር እንደ [[ግሪክኛ]]ው ነው።
 
መጀመርያው «ባቢሎን» የደቡብ [[ሱመር]] ከተማ የ[[ኤሪዱ]] መጠሪያ ስም እንደ ነበር ይመስላል።<ref>[http://oi.uchicago.edu/pdf/saoc62.pdf "Babylon as a Name for Other Cities..."] p. 25-33. {{en}}</ref> በ[[ሱመራውያን ነገሥታት ዝርዝር]] ዘንድ፣ ከ[[ማየ አይኅ]] ቀጥሎ ኤሪዱ የዓለሙ መጀመርያው ከተማ ሲሆን፣ ንጉሡ [[ኤንመርካር]] (2450 ዓክልበ. አካባቢ) ታላላቅ [[ዚጉራቶች]]ን (የቤተ መቅደስ ግንቦች) በኤሪዱ እና በ[[ኦሬክ]] እንዳሠራ ይለናል። ይህም በሌሎች ልማዶች እንደሚተረክ የባቢሎንና የኦሬክ መሥራች [[ናምሩድ]] [[የባቢሎን ግንብ]]ን እንደ መሥራቱ ታሪክ ይመስላል።
 
ከሱመር ጽላቶች እንደምናውቅ፣ የኤሪዱ ግንብ ከተተወ በኋላ፣ የሱመር ዋና ከተማ (ዋና ቤተ መቅደስ የተገኘበት) ወደ [[ኒፑር]] ተዛወረ። ከዚያ ዘመን በኋላ የ[[አካድ]] ንጉሥ [[ታላቁ ሳርጎን]] (2070 ዓክልበ. ግድም) አዲስ የዋና መቅደስ ከተማ ወደ ስሜኑ ሠርቶ ማዕረጉን ከኒፑር አንዳዛወረ እናንብባለን። በአንዱ ዜና መዋዕል ዘንድ ሳርጎን «የባቢሎን ጒድጓድ አፈር ቆፍሮ አዲስ ባቢሎን በአካድ ፊት ሠራ»፣ በሌላም «ከጒድጓዱ አፈር ቆፍሮ በአካድ ፊት ከተማ ሠራ፣ ስሙንም 'ባቢሎን' አለው።» ከዚህ መረጃ ሳርጎን የኤሪዱን አፈር ወስዶ አዲሱን ባቢሎን በሥፍራው እንደመሠረተው መገመት እንችላለን። ሳርጎንም እንደ ፊተኛው ኤንመርካር «የአራት ሩቦች ንጉሥ» በመባሉ በሌሎች መንግሥታት ሁሉ በላይ ሆኖ በመላው ዓለም ላይ ይግባኝ ማለት እንደ መጣሉ ነበር።