ከ«ሥልጣኔና እንጉርጉሮው» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ኮፒ-ኤዲት
No edit summary
መስመር፡ 1፦
 
 
'''ሥልጣኔና እንጉርጉሮው''' በ[[ስነ-ልቡና]] ተመራርማሪው [[ሲግመንድ ፍሮይድ]] በ[[1929 እ.ኤ.አ.]] የተጻፈ እንዲሁም በ[[1930 እ.ኤ.አ.]] በ[[ጀርመንኛ]] የታተመ መጽሃፍ ነው። በጀርመንኛ አርእስቱ Das Unbehagen in der Kultur /ዳስ ኡንበሃግን ኢን ደር ኩልቱር/ ወይም «በባህሉ ያለው አለመመቸት» ተሰየመ። ከፍሮይድ ስራዎች ዋና ከሚባሉት ወገን ሲሆን በምዕራቡ አለም ከፍተኛ ተነባቢነት ያለው መጽሃፍ ነው።.<ref>Harv|Gay|1989|loc=p. 722</ref>
 
ግለሰቦች በ[[ሥልጣኔ]] ላይ ያንጎራጉራሉ፡ የዚህ ምክንያቱ በአንድ ግለሰብና በስልጣኔ መካከል የማያባራ ቅራኔ በመኖሩ መሆኑን ፍሮይድ አሰፈረ። የዚህ ቅራኔ መሰረታዊ መንስኤ ግለሰቦች በ[[ደመነፍስ]] ነጻነትን ሲፈልጉ ስልጣኔ ግን ከያንዳንዱ ግለሰብ መታዘዝንና እራስን መግዛት ይጠይቃል። [[የሰው ልጅ]] በራሱ አረመኒያዊ የሆኑ የደመነፍስ ፍላጎቶች አሉት (ለምሳሌ የመግደል፣ የማያልቅ የፍትወተ ስጋ ፍላጎት ወዘተ...) ። ነገር ግን እኒህ ደመነፍስ ፍላጎቶች በ[[ማህበራዊ ኑሮ]] ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ። ስለሆነም በማናችውም የታሪክ ዘመናት የተፈጠሩ ስልጣኔዎች የሰውን ልጅ ደመነፍስ ፍላጎት ለማቀብ [[ህግ]] አውጥተዋል። አትግደል፣ አትድፈር፣ አታመንዝር፣ የሌላ ሰውን ሃብት አትውሰድ ወዘተ... የሚሉ ህጎች ወጥተው ህጎቹን የተላለፈ ከፍተኛ ቅጣት በዘመናትና በስልጣኔያት ሁሉ ሲቀበል ይታያል። ይህ እንግዲህ፣ በፍሮይድ አስተሳሰብ፣ በስልጣኔ ውስጥ የሚንሸራሽሩ ዜጎች በስልጣኔ ላይ የማያባራ ቅሬታ እንዲያበጁ አድርጓል።