ከ«ኬንያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 29፦
|የግርጌ_ማስታወሻ =
}}
'''የኬንያ ሪፐብሊክ''' በምስራቅ [[አፍሪካ]] የምትገኝ ሀገር ናት። በሰሜን ከ[[ኢትዮጵያ]]፣ በሰሜን-ምስራቅ ከ[[ሶማሊያ]]፣ በደቡብ ከ[[ታንዛኒያ]]፣ በምስራቅ ከ[[ዩጋንዳ]]፣ በስሜን-ምዕራብ ከ[[ደቡብ ሱዳን]]፣ በደቡብ-ምስራቅ ከ[[ሕንድ ውቅያኖስ]] ጋር ድንበር ትጋራለች። የኬንያ ስም የመጣው በአፍሪካ በከፍታ ሁለተኛ ከሆነው ከ[[ማውንት ኬንያ]] ተራራ ነው።
 
አውሮፓውያን አካባቢውን ማሰስ የጀመሩት ከ፲፱ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ሲሆን [[የብሪታንያ መንግሥት]] [[የምሥራቅ አፍሪካ ፕሮቴክቶሬት]]ን በ1895 እ.ኤ.አ. አቋቁሟል። ይህ ፕሮቴክቶሬት በ1920 እ.ኤ.አ. [[የኬንያ ግዛት]] ተብሎ ተሰይሟል። ነፃ የኬንያ ሪፐብሊክ በዲሴምበር 1963 እ.ኤ.አ. ታወጀ።
 
የኬንያ ስም የመጣው በአፍሪካ በከፍታ ሁለተኛ ከሆነው ከ[[ደብረ ኬንያ]] ተራራ ነው። በዚሁ ተራራ ዙሪያ የሚኖሩት ነገዶች ስሙን «ኪኛ» (በ[[ካምባኛ]])፣ «ኪሪማራ» (በ[[አመሩኛ]])፣ «ኪሬኛ» (በ[[ኤምቡኛ]])፣ «ኪሪኛያጋ» (በ[[ኪኩዩ]])፣ ወይም «ኬሪ» (በ[[መዓሳይኛ]]) ይሉታል። የነዚህ ስሞች ሁሉ ትርጉሞች «ቡራቡሬ» ሲሆኑ ይህም ደግሞ «[[ሰጎን]]» ማለት ነው፤ [[አመዳይ]] ያለበት የተራራው ጫፍ ለተመልካች ቡራቡሬ ወንድ ሰጎንን ያሳስባልና።
 
በኦገስት 2010 እ.ኤ.አ. በተካሄደ ውሳኔ ሕዝብ (referendum) መሠረት ከብሪታንያ የተወረሰው ሕገ መንግሥት በአዲስ ሕገ መንግሥት ተለውጧል። በአሁኑ ጊዜ ኬንያ በ፵፯ ካውንቲዎች (የአስተዳደር ክፍሎች) ተዋቅራለች። እነዚህ ካውንቲዎች በሕዝብ በተመረጡ ሰዎች የሚስተዳደሩ ሲሆን በናይሮቢ ከሚገኘው ማዕከላዊ መንግሥት በነፃነት ይንቀሳቀሳሉ።