ከ«ዶናልድ ጆን ትራምፕ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 2፦
'''ዶናልድ ጆን ትራምፕ ''' ወይም '''ዶናልድ ጆን ትራምጵ '''(እ.ኤ.አ. ጁን 14 ቀን 1946 ተወለደ) አሜሪካዊ ነጋዴ ፣ ፖለቲከኛ ፣ በ[[ቴሌቪዥን]] ፕሮግራሞቹ ታዋቂ እና 45ኛው የ[[ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ]] ፕሬዚደንት ነው። ሥልጣኑንም እ.ኤ.አ. በጃኑዌሪ 20 ቀን 2017 ተረክቧል።
 
በክዊንስ [[ኒው ዮርክ ከተማ]] የተወለደው አቶ ትራምፕ በሪልበ[[ሪል ስቴትእስቴት]] ሥራ ላይ ተሰማርቶ የነበረው የፍሬድ ትራምፕ ልጅ ነው። በኮሌጅ እያለም ኤሊዛቤት ትራምፕ ኤንድ ሰንስ በተባለው ድርጅት ይሠራ ነበር። በእ.ኤ.አ. 1968 ከኮሌጅ ከተመረቀ በኋላ ያንን ድርጅት ተቀላቀለ። በእ.ኤ.አ. 1971 ደግሞ ሙሉ ሥልጣን ከተሠጠው በኋላ የድርጅቱን ስም ወደ "ዘ ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን" ለወጠው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ካሲኖዎችን ፣ የጎልፍ ሜዳዎችን ፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች በእርሱ ስም የሚጠሩ ንብረቶችን አፍርቷል። እ.ኤ.አ. ከ2005 እስከ 2015 ድረስ [[ዘ አፕሬንቲስ]] የተባለ ፕሮግራምን በ[[ኤን ቢ ሲ]] ላይ ያቀርብ ነበር።
 
እ.ኤ.አ. በ2000 ላይ፣ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ተወዳድሮ ሁለት የ[[ሪፎርም ፓርቲ]] እጩነትን አሸንፎ ነበር። በእ.ኤ.አ. ጁን 16 2015 ላይ ደግሞ ለፕሬዚደንትነት እንደሚወዳደር አሳወቀ። ይህን ጊዜ ግን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ነው። በስደት፣ በነፃ ገበያ እና በጦር ጣልቃ ገብነት ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ታዋቂ ሆኗል። በእነኚህ አነጋጋሪ አስተያየቶቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ሜይ 2016 ከሪፐብሊካን የፕሬዚደንታዊ እጩነት ውድድሮች ውስጥ 28ቱን ውድድሮች ካሸነፈ በኋላ እና የተቀሩት ተቀናቃኞቹ እነ [[ቴድ ክሩዝ]] እና [[ጆን ካሲች]] ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ፥ ትራምፕ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ከጁላይ 18 እስከ 21 በተካሄደው የ2016ቱ የሪፐብሊካኖች አገር አቀፍ ስብሰባ ላይ እጩ መሆኑ በይፋ ታወጀ። በእ.ኤ.አ. ኖቬምበር 8 ቀን 2016 ላይ የፕሬዚደንትነት ምርጫውን አሸነፈ። ማሸነፉንም ተከትሎ ብዙ የተቃውሞ ሠልፎች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በ70 ዓመቱም ሥልጣን ላይ በመውጣቱ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ፕሬዚደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ያደርገዋል።