ከ«ኪዳነ ወልድ ክፍሌ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 2፦
 
==የህይወት ታሪክ==
አለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ በ[[ሸዋ]] ክፍለ ሀገር በይፋትና ጥሙጋ አውራጃ በ፲፰፻፷፬ ዓ.ም. ተወለዱ። ለትምህርት ሲደርሱ በአካባቢያቸው የነበረውን የአገራቸውን ትምህርት ተማሩ። በኋላም ወደ [[ጎንደር]] ተጉዘው የመጻሕፍትን ትርጓሜ አጠኑ። በጊዜው የነበራቸው የቀለም አቀባበል፣ የሚስጥር መመራመርና መራቀቅ በጉባኤው ላይ «የቀለም ቀንድ» የሚል ቅጽል ተሰጣቸው።<ref name="natbio">[[የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ]]፣ ''ብሔራዊ ቢብሎግራፊ (የደራሲያን አጭር የሕይወት ታሪክ)'' ፤ ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. [http://www.nale.gov.et/National%20Bibliography/BIBLIO.%20OF%20ETHIOPIAN%20WRITERS%20.pdf ] (ታኅሣሥ ፲፪ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. የተነበበ)</ref>ማናቸው ማናቸው
 
አለቃ ኪዳነወልድ ከ[[ግዕዝ]]ና [[አማርኛ]] ሌላ [[አረብኛ]]፣ [[ዕብራይስጥኛ]]፣ [[ላቲን]]፣ ሌሎችንም ቋንቋዎች አጠናቅቀው ያውቁ ነበር። አለቃ ኪዳነወልድ በ[[እየሩሳሌም]] ለ፳፪ ዓመት ተቀምጠዋል። በዚህም ወቅት ብሉይና ሀዲስ በሦስት ቋንቋ ጠንቅቀው አመሳክረው ተርጉመዋል። ኪዳነወልድ ክፍሌ በ፲፱፻፳፮ ዓ.ም. የመጀመሪያውን መዝገበ ፊደል አውጥተው ከልዩልዩ ቋንቋዎች ጋር በማመሳከር አሳትመዋል። የኢትዮጵያ ፊደል አመጣጡንና ባህሉን በውል አስተባብረው በማቅረባቸውም በጊዜው ተቋቁመው ለነበሩት ትምህርት ቤቶች መመሪያና መማሪያ ለመሆን በቅተዋል። ቀጥለውም ትንሽ አማርኛ ፊደል ከአረብና ከዕብራይስጥ አቆራኝተው አሳትመዋል።<ref name="natbio" />