ከ«ታሪክ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አንድ ለውጥ 330958 ከሰኢድ (ውይይት) ገለበጠ
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Colonisation2.gif|thumb|550px|የቅኝ አገራት መስፋፋት 1484-2000 ዓም]]
 
'''ታሪክ''' በትክክል እንደሚሰፈን ከተጻፉት መዝገቦች አንስቶ ይጀምራል። ከዚያ አስቀድሞ ምንም የተጻፉት መዝገቦች ሳይኖሩ የነበረው ወቅት [[ቅድመ-ታሪክ]] ይባላል።
 
በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከ[[ጥንታዊ ግብጽ]] [[ሥነ ቅርስ]] ታውቀዋል። ለምሳሌ [[የመንደሮች መኳያ ሰሌዳ]] እና [[የጊንጥ ዱላ]] ከዚህ ዘመን ናቸው። ስለዚህ ከ3125 ዓክልበ. በፊት ያለፈው ሁሉ የአለም «ቅድመ-ታሪክ» ነው።
 
በሌላ አገር ግን የጽሑፍ መዝገቦች እንዲሁም የታሪክ መጋረጃ መከፈቱ እንደ ግብጽ ጥንታዊ አይሆንም። ለምሳሌ ከሜክሲኮ ስሜን የኖሩት ስሜን አሜሪካ ኗሪዎች እንደ ብዙ አሕጉር ሰዎች ለረጅም ዘመን የጽሑፍ አካል ባጠቃላይ ያልነበራቸው ሆነው ቀሩ። ከዚሁ የመዝገቦች ጉድለት የተነሣ ከ1500 ዓም በፊት ያለው ጊዜ ሁሉ የስሜን አሜሪካ ቅድመ-ታሪክ ሊባል ይችላል። ከ1500 በፊት የተቀረጹት አንዳንድ ጽሑፎች በተለይም የ[[ፊንቄ]] ቋንቋ በሰፊ በ[[አሜሪካዎች]] ቢገኙም ሁላቸው በፈረንጅ ሊቃውንት አጠያያቂ ተብለዋል። ሆኖም ስለነዚህ የፊንቄ ቅርሶች ወዘተ. በአሜሪካ ተገኝተው የሚገልጹ መጻሕፍት ሊገኙ ይቻላል።
 
ከግብጽ [[ጥንታዊ መንግሥት]] ዘመን ቀጥሎ ጥንታዊ የሆኑት የ[[ኩኔይፎርም]] ጽሑፍ መዝገቦች ከ[[መስጴጦምያ]] ከ2500 ዓክልበ. ያህል ጀምሮ ሊታዩ ይቻላል። የአንዳንድ ሌላ አገር መዝገቦች ለምሳሌ የ[[ቻይና]] መዝገቦች በልማድ ተጠብቀው ደግሞ ከዚህ ዘመን ያህል ጀምሮ ይዘግባሉ፤ ነገር ግን በቻይና በሥነ ቅርስ ረገድ ከ1500 በፊት የተቀረጸው ጽሑፍ ቢኖር አልተረፈም ወይም አልተገኘም። ከ1500 ዓክልበ. በፊት የነበረውን [[የሥያ ሥርወ መንግስት]] የምናውቀው በኋላ በተዘገቡት ጽሑፎች ብቻ ሲሆን የዚያ ዘመን ታሪክ «[[አፈ ታሪክ]]» ሊባል ይችላል።
 
 
* [[አፈ፡ታሪክ]]
* [[አርኬዬሎጂ (ሥነ፡ቅርስ)]]