ከ«ባቢሎን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 27፦
ሆኖም ይህ የኒፑር ቅድምትነት መተካቱ ለጊዜው በሱመራውያን መካከል ተቃውሞ ያገኝ ነበር። ከአካዳውያን፣ [[ጉታውያን]]ና ሱመራውያን ገዥነት በኋላ፣ [[አሞራውያን]] የተባሉት ብሔር ወርሮ አያሌ ከተማ-ግዛቶች መሠረቱ። ከዚህም መካከል አንዱ [[ካዛሉ]] ሲሆን አሞራዊው አለቃ [[ሱሙ-አቡም]] በ1807 ዓክልበ. ግድም የባቢሎን ነጻነት ከካዛሉ አዋጀ፤ በዚያን ጊዜ እሱ የባቢሎን መጀመርያ ንጉሥ ሆነ። ከባቢሎን ነገሥታት [[ሃሙራቢ]] [[የሃሙራቢ ሕግ ፍትሕ]] ስለ መፍጠሩ በተለይ ይታወቃል። የባቢሎን መጀመርያ ውድቅት በ1507 ዓክልበ. ([[ኡልትራ አጭር አቆጣጠር]]) በ[[ኬጥያውያን]] ንጉሥ [[፩ ሙርሲሊ]] እጅ ደረሰ። ከዚያ የኬጥያውያን ጓደኞች የነበሩት [[ካሣውያን]] ብሔር ባቢሎንን ገዛ፣ የከተማውም ስም በ[[ካሣኛ]] «'''ካራንዱኒያሽ'''» ተባለ። እነዚህ ካሣውያን እስከ 1163 ዓክልበ. ድረስ ባቢሎኒያን ገዙ።
 
ለረጅም ዘመናት [[አሦር]] በስሜንና የ[[ባቢሎኒያ]] መንግሥት በደቡብ ለመስጴጦምያ ዋና ተወዳዳሪዎቹ ሆኑ። ከ919 ዓክልበ ጀምሮ አሦር ይበረታ ነበር፤ [[እስራኤል]]ንና [[ግብጽ]]ን እስከሚያሸንፋቸው ድረስ። ከ634 ዓክልበ. በኋላ ግን አሦር ወድቆ ባቢሎኒያ በ[[ናቦፖላሣር]] ሥር እንደገና ነጻነት አገኘ። ልጁም [[2 ናቡከደነጾር]] ከብሉይ ኪዳን እንደሚታወቅ፣ [[ኢየሩሳሌም]]ን የ[[ይሁዳ]]ንም ሕዝብ የማረከው ([[የባቢሎን ምርኮ]]) ነቢዩም [[ዳንኤል]] የነበየለት ንጉሥ ነው፤ ዳንኤልም [[የናቡከደነጾር የምስል ሕልም]] አስተረጎመለት። ይህ የባቢሎኒያ መንግሥት በ547 ዓክልበ. ለ[[ፋርስ]] ንጉሥ [[ታላቁ ቂሮስ]] ወደቀ።
 
በ283 ዓክልበ. በግሪኮች ዘመን (ከ[[ታላቁ እስክንድር]] በኋላ)፣ የባቢሎን ኗሪዎችና መቅደስ ወደ [[ሴሌውክያ]] በግድ ተዛወሩ። ከዚህ ጀምሮ ባቢሎን አነስተኛ ሥፍራ ሆነ።