ከ«ሥነ-ፍጥረት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
No edit summary
Tags: Emoji በንፋስ ስልክ -የሞባይል ድረገፅ
መስመር፡ 12፦
# በመናገር /በነቢብ/
#በመስራት /በገቢር/ ናቸው፡፡
 
ሥነ-ፍጥረት በኢስላም
 
ሥነ-ፍጥረት
 
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
 
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
 
"ሥነ-ፍጥረት"creatinology" ማለት ስለ ፍጥረት የሚያጠና የዕውቀት ዘርፍ ነው፤ አምላካችን አላህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፤ "ሸይዕ" شَىْء ማለት "ነገር'thing" ማለት ሲሆን ሁሉንም ነገራት ሁሉ ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
 
አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
6፥102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው*፤ ስለዚህ ተገዙት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
13፥16 *አላህ ሁሉንም ነገር ፈጣሪ ነው*፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው፤ በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
40፥62 ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ *የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُون
 
 
ነጥብ አንድ
"ፍጥረት"
አላህ የፈጠራቸው ፍጥረታት ህልቆ-መሳፍርት ናቸው፤ ከአጽናፍ እስከ አድማስ ያሉትን ትልቅ እና ደቂቅ ፍጥረታት ቢዘረዘሩ አያልቁም፤ እነዚህን ፍጥረታት አላህ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ ነው፦
50፥38 ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ
25፥59 ያ ሰማያትና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ፣ ከዚያም በዐርሹ ላይ የተደላደለ አልረሕማን ነው፡፡ ከእርሱም ዐዋቂን ጠይቅ፡፡ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَىٰ عَلَى الْعَرْشِ ۚ الرَّحْمَـٰنُ فَاسْأَلْ بِهِ خَبِيرًا
 
ይህ ጥቅላዊ ገለጻ ሲሆን በተናጥል አስፈላጊ የሆነው አፈጠጠሩ እንዲህ ይገልጻል፦
42፥9 በላቸው «እናንተ በዚያ ምድርን በሁለት ቀኖች ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን? ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው፡፡ قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَرْضَ فِى يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادًۭا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ
 
ከመጀመሪያው ቀን እስከ አራተኛው ቀናት ባሉት በአራት ቀናት ውስጥ በምድር ላይ የረጉ ጋራዎችን፣ በውስጧም ምግቦችዋን ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፦
42፥10 በእርሷም ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፡፡ በእርሷም በረከትን አደረገ፡፡ በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፡፡ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ مِن فَوْقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقْوَٰتَهَا فِىٓ أَرْبَعَةِ أَيَّامٍۢ سَوَآءًۭ لِّلسَّآئِلِينَ
 
"ጭስ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ዱኻን" دُخَانٌۭ ሲሆን "ጋዝ" ማለት ነው፤ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አላህ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፦
42፥11 ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ
 
"ሱመ" ثُمَّ ማለት አያያዥ መስተጻምር ሲሆን "ከዚያም" ወይም "እንዲሁ" ማለት ነው፤ አያያዥነቱ "ተርቲቢያህ" ማለትም "ቅድመ-ተከተል" ነው፤ ይህም ቅድመ-ተከተል በሁለት ይከፈላል፦ አንዱ "ተርቲበቱል ከላም" ማለት "የንግግር ቅድመ-ተከተል" ሲሆን ሁለተኛው "ተርቲበቱል ዘመን" ማለት የጊዜ ቅድመ-ተከተል ናቸው፣ እዚህ አንቀጽ ላይ ግን ዓውዱ የንግግር ቅድመ-ተከተል ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፤ አላህ ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፤ ጭስ የነበረችውን ሰማይ በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፡፡ فَقَضَىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَاتٍۢ فِى يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ *ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ لَكُم مَّا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًۭا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ فَسَوَّىٰهُنَّ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍۢ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ
 
 
ነጥብ ሁለት
"ማስተንተን"
በሰማያትና በምድር ያሉትን ከአጽናፍ እስከ አድማስ ያሉትን ትልቅ እና ደቂቅ ህልቆ-መሳፍርት ፍጥረታት እኛ ቀስ በቀስ በማስተንተን ማወቅ እንችላለን፤ በአላህ አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም፤ ዓይንህንም ወደ ፍጥረታት እይ ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን? በፍጹም አታይም፦
3፥191 እነርሱም እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ *በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ*፡- «ጌታችን ሆይ! *ይህን በከንቱ አልፈጠርከውም*፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡ الَّذِينَ يَذْكُرُونَ اللَّهَ قِيَامًا وَقُعُودًا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمْ وَيَتَفَكَّرُونَ فِي خَلْقِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ رَبَّنَا مَا خَلَقْتَ هَـٰذَا بَاطِلًا سُبْحَانَكَ فَقِنَا عَذَابَ النَّارِ
67፥3 ያ ሰባትን ሰማያት የተነባበሩ ኾነው የፈጠረ ነው፡፡ *በአልረሕማን አፈጣጠር ውስጥ ምንም መዛነፍን አታይም*፡፡ ዓይንህንም መልስ፡፡ «ከስንጥቆች አንዳችን ታያለህን?» الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ طِبَاقًا ۖ مَّا تَرَىٰ فِي خَلْقِ الرَّحْمَـٰنِ مِن تَفَاوُتٍ ۖ فَارْجِعِ الْبَصَرَ هَلْ تَرَىٰ مِن فُطُورٍ
 
ለእኛም በሰማያት ያለውን እና በምድርም ያለውን ሁሉ በሙሉ ከአላህ ሲኾን የገራልን ነው፤ በዚህ አፈጣጥር ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ተዓምራት አልለበት፦
45፥13 ለእናንተም በሰማያት ያለውን እና በምድርም ያለውን ሁሉ በሙሉ ከእርሱ ሲኾን የገራላችሁ ነው፡፡ በዚህ *ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች* ተዓምራት አልለበት፡፡ وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችንና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም ከፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ዓይነቶችን ያደረገ ነው፡፡ ሌሊትን በቀን ይሸፍናል፡፡ በዚህም ውስጥ *ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች* ምልክቶች አሉ፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ ۖ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ
 
ሰማያትና ምድር ከጌታችንም ጸጋዎች ናቸው፦
55፥7 *ሰማይንም አጓናት*፡፡ ትክክለኛነትንም ደነገገ፡፡ وَٱلسَّمَآءَ رَفَعَهَا وَوَضَعَ ٱلْمِيزَانَ
55፥10 *ምድርንም ለፍጡሩ አደላደላት*፡፡ وَٱلْأَرْضَ وَضَعَهَا لِلْأَنَامِ
55፥13 *ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?* فَبِأَىِّ ءَالَآءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
 
በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለእኛ ያገራልን ግልጽም ድብቅም ሲኾኑ የሞላላልን ጸጋዎቹንም ናቸው፦
31፥20 አላህ *በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ ለእናንተ ያገራላችሁ ጸጋዎቹንም ግልጽም ድብቅም ሲኾኑ የሞላላችሁ መኾኑን አታዩምን?* أَلَمْ تَرَوْا أَنَّ اللَّهَ سَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَأَسْبَغَ عَلَيْكُمْ نِعَمَهُ ظَاهِرَةً وَبَاطِنَةً ۗ
 
ሰማያትና ምድር፣ በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ እኛ የደረስንበት ግልጽም ያልደረስንበት ድብቅም ለእኛ ያገራልን የአላህንም ጸጋ ናቸው፤ የአላህንም ጸጋ ብትቆጥረው አንዘልቀውም፦
16፥18 *የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም*፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡ وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ۗ إِنَّ اللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ
 
 
መደምደሚያ
በተረፈ ዘፍጥረት 1፥1-31 የፈጣሪን ፍጥረት በከፊት እንጂ በሙሉ አይዘረዝርም። ለምሳሌ ሰባት ሰማያት፣ መላእክት፣ ውኃ፣ ፈንገስ፣ ባክቴሪያ፣ ጀርም ወዘተ መቼ እንደተፈጠሩ፣ ከምን እንደተፈጠሩ እና እንዴት እንደተፈጠሩ አይናገርም። አላህ የዓለማት ጌታ ነው፤ “ዓለሚን” عَٰلَمِين ማለት “ዓለማት” ማለት ሲሆን የዘመናችን የሥነ-ፈለክ አስተንታኞች “መልቲ-ቨርስ”multi-verse” ይሉታል፤ ይህም ህልቆ-መሳፍት የሆነውን አድማስና አፅናፍ ለማመልከት ይጠቀሙበታል፤ “አዕለም” أَعْلَم የዐለሚን ነጠላ ሲሆን ‘ዐልለመ” عَلَّمَ “አሳወቀ” ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን “ዓለም” ወይም “የታወቀ” ማለት ነው፤ አላህ በእኛ ዘመን ባሉት ያሳወቀው እኛ ያለንባት አንድ ዓለም “ዩኒ-ቨርስ”uni-verse” ነው፤ የእኛ ዓለም ከ 170 billion እስከ 200 billion “ረጨት”galaxy” ይዟል፤ “ረጨት” ማለት የከዋክብት ስብስብ ሲሆን የእኛ ረጨት “ፍኖተ-ሃሊብ”Milky Way” ረጨት ይባላል፤ ይህ ረጨት ውፍረቱ 1000 የብርሃን አመት ይገመታል፤ ከአንዱ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ያለው ርቀት በዲያሜትር ሲለካ ደግሞ 100,000 የብርሃን ዓመት ይሆናል፤ በውስጡ ከ100 እስከ 400 ቢልዮን ከዋክብቶች እንደያዘ ይገመታል።
ይህንን የከዋክብት ረጨት”constellation” አምላካችን አላህ የዛሬ 1407 ዓመት በቁርአን “ቡሩጅ” بُرُوج ይለዋል፦
85:1 #የቡርጆች الْبُرُوجِ ባለቤት በሆነችው ሰማይ እምላለሁ፤
25:61 ያ በሰማይ #ቡርጆችን بُرُوجًا ያደረገና በርሷም አንጸባራቂን ፀሐይ አብሪ ጨረቃንም ያደረገ ጌታ ክብሩ በጣም ላቀ።
15:16 በሰማይም ላይ #ቡርጆችን بُرُوجًا በእርግጥ አድርገናል፡፤ ለተመልካቾችም አጊጠናታል፡፡
 
አላህ የዛሬ 1400 ዓመት በተከበረው ቃሉ በቁርአን “በአጽናፎቹ ውስጥ ያሉትን ታምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን” ብሎ ቃል ገብቶ ነበር፦
41፥53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ #በአጽናፎቹ #ውስጥ እና በራሶቻቸውም ውስጥ #ያሉትን #ታምራቶቻችንን በእርግጥ #እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?
 
ታዲያ በበረሃ ግመል ገፊ ነው ተብሎ በሚነገርላቸው ላይ ይህ ሁሉ እውቀት እንዴት ተዥጎደጎደ? ስንል፤ ይህንን እውቀት የዛሬ 1407 ዓመት ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው ይሆናል መልሱ፦
25:6 ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለውን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፤ እርሱ መሐሪ አዛኝ ነውና፤ በላቸው።
 
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://t.me/Wahidcom
 
ወሰላሙ አለይኩም
 
===ፍጥረታት የተገኙበት መንገድና ሁኔታ===