ከ«ጥንታዊ ግብፅ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 58፦
 
[[ስዕል:Ibscha.jpg|350px|thumb|left|በ፪ ሰኑስረት ዘመን የገቡት ሰማውያን እረኞችና ነጋዴዎች]]
በ፪ ሰኑስረት ዘመን (1905 ዓክልበ.) ብዙ ሴማውያን ወደ [[ጌሤም]] የገቡ በዚህ ዘመን እንደ ነበር ይመስላል፤ ስለዚህ ይህ ፈርዖን በመጽሐፍ ቅዱስ [[ዮሴፍ]]ን እንደ ግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር የሾመው እንደ ሆነ በአንዳንድ ደራሲ ታስቧል። በዚህም ሥርወ መንግስት ያሉት የሌሎቹ ፈርዖኖች ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሁላቸው በስማቸው ተዘግበዋል፣ የ፪ ሰኑስረት ጠቅላይ ሚኒስትር ስም ግን በመዝገቦቹ አልተረፈልንም። በ1898 ዓክልበ. ልጁን [[3 ሰኑስረት]] እንደ ጋርዮሽ ፈርዖን አስነሣው፤ በ1888 ዓክልበ. ዓረፈ።
 
፫ ሰኑስረት (1888 ዓክልበ.) በኩሽ፣ [[ምድያም]]ና ከነዓን ላይ ዘመተ፤ መታወቂያው የግሪክ ታሪክ ጽሐፊዎች የጠቀሱት [[ሴሶስትሪስ]] ከሆነ እስከ [[እስኩቴስ]]ም ድረስ እንደ ዘመተ ይባል ነበር። በ1879 ዓክልበ. ልጁን [[3 አመነምሃት]] እንደ ጋርዮሽ ፈርዖን አስነሣው፤ በ1859 ዓክልበ. ዓረፈ።