ከ«ጥንታዊ ግብፅ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 48፦
 
==መካከለኛው መንግሥት==
የግብጽ መካከለኛው መንግሥት ወይም [[12ኛው ሥረ መንግሥት]] ገዦች ሁሉ (2002-1819 ዓክልበ.) ከሥነ ቅርስ በደንብ ይታወቃሉ።
 
የሥርወ መንግሥቱ መሥራች [[1 አመነምሃት]] (2002 ዓክልበ.) የዱሮውን ጥንታዊ መንግሥት ፈሊጥ በሥነ ሕንጻ እና በሥነ ጽሑፍ ለማሳደስ ጣረ። በ1982 ዓክልበ. ልጁን [[1 ሰኑስረት]] እንደ ጋርዮሽ ፈርዖን አስነሣው፣ ዋና ከተማቸውም ከጤቤስ ወደ [[እጭታዊ]] ተዛወረ። በ1973 ዓም በ[[ኩሽ መንግሥት]] ላይ ዘመቱ፣ በሚከተለውም ዓመት ልጁ ሰኑስረት በ[[ሊብያ]] እየዘመተ አመነምሃት በሤራ ተገደለ።
 
፩ ሰኑስረት (1972 ዓክልበ.) እንደገና በ1964 ዓክልበ. በኩሽ ላይ ዘመተ፤ ሎሌዎችንም ወደ ሲና ልሳነ ምድር ለማዕደን ላከ። አለቃውም [[ሲኑሄ]] በአንድ ሰነድ ዘንድ በ[[ሶርያ]] ይዘመት ነበር። በ1940 ዓክልበ. ልጁን [[2 አመነምሃት]] እንደ ጋርዮሽ ፈርዖን አስነሣው፤ በ1938 ዓክልበ. ዓረፈ።
 
በ2 አመነምሃት ዘመን (1938 ዓክልበ.) ግብጽ ከኩሽ፣ [[ሊባኖስ]]ና [[ፑንት]] ጋር ንግድ ያካሄድ ነበር፤ ሥራዊቶቹም በሶርያም ይዘመቱ ነበር። በ1907 ዓክልበ. ልጁን [[2 ሰኑስረት]] እንደ ጋርዮሽ ፈርዖን አስነሣው፤ በ1905 ዓክልበ ዓረፈ።
 
በ፪ ሰኑስረት ዘመን (1905 ዓክልበ.) ብዙ ሴማውያን ወደ [[ጌሤም]] የገቡ በዚህ ዘመን እንደ ነበር ይመስላል፤ ስለዚህ ይህ ፈርዖን በመጽሐፍ ቅዱስ [[ዮሴፍ]]ን እንደ ግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር የሾመው እንደ ሆነ በአንዳንድ ደራሲ ታስቧል። በ1898 ዓክልበ. ልጁን [[3 ሰኑስረት]] እንደ ጋርዮሽ ፈርዖን አስነሣው፤ በ1888 ዓክልበ. ዓረፈ።
 
፫ ሰኑስረት (1888 ዓክልበ.) በኩሽ፣ [[ምድያም]]ና ከነዓን ላይ ዘመተ፤ መታወቂያው የግሪክ ታሪክ ጽሐፊዎች የጠቀሱት [[ሴሶስትሪስ]] ከሆነ እስከ [[እስኩቴስ]]ም ድረስ እንደ ዘመተ ይባል ነበር። በ1879 ዓክልበ. ልጁን [[3 አመነምሃት]] እንደ ጋርዮሽ ፈርዖን አስነሣው፤ በ1859 ዓክልበ. ዓረፈ።
 
3 አመነምሃት (1859 ዓክልበ.) ለአንዳንድ ሀረሞችና ሐይቅ በመሥራት ይታወሳል። በ1832 ዓክልበ. ልጁን [[4 አመነምሃት]] እንደ ጋርዮሽ ፈርዖን አስነሣውና ዓረፈ።
 
፬ አመነምሃት (1832 ዓክልበ.) የማዕደን ጉዞ ወደ ሲና ላከ። በ1823 ዓክልበ. ያለ ልጅ አርፎ እኅቱ [[ሶበክነፈሩ]] ተከተልችው።
 
ሶበክነፈሩ (1823 ዓክልበ.) ንግሥት እየሆነች፣ በ1821 ዓክልበ. በጌሤም የሠፈሩት ሴማውያን የራሳቸው ፈርዖን [[ያክቢም ሰኻኤንሬ]] ተፈቀዱ። በ1819 ዓም ዓረፈች።
 
ግብጽ ከዚህ በኋላ እንደገና ስለተከፋፈለ፣ የመካከለኛው መንግስት መጨረሻ ይቆጠራል። በሁለተኛው ጨለማ ዘመን መጀመርያ፣ ሁለት ሥርወ መንግሥታት ነበር፤ በስሜኑ የሴማውያን [[14ኛው ሥርወ መንግሥት]]ና የሶበክነፈሩ ተከታዮች በጤቤስ [[13ኛው ሥርወ መንግሥት]] ናቸው።
 
==ሁለተኛው መካከለኛ ዘመን==