ከ«ጨረቃ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Removing Link GA template (handled by wikidata)
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:moon.jpeg|የጨረቃ ምስል ከ[[መሬት]] ሰሜናዊ ክፍል እንደሚታየው |thumbnail|350px|right]]
'''ጨረቃ''' የ[[መሬት]] ብቸኛዋ [[ሳተላይት]] ስትሆን በ[[ሥርዓተ-ፀሐይ]] ውስጥ አምስተኛ ትልቅ ሳተላይት ናት። ከመሬት መሀል እስከ '''ጨረቃ''' መሀል ድረስ ያለው አማካይ ርቀት 384,403 ኪ.ሜ. (238,857 [[ማይል]]) ያህል ነው። ይህ ርቀት ከመሬት አንድ ጫፍ እስከ ሌላኛው ተቃራኒ ጫፍ (diameter) ያለውን ርቀት ሰላሳ (30X) ይበልጣል። ሁለቱ አካላት ሥርዓታቸውን የሚጠብቁበት ማዕከላዊ ነጥብ 1,700 ኪ.ሜ. (1,100 ማይል]]) ማለትም የመሬትን ራዲየስ አንድ አራተኛ (1/4) ከመሬት ጠለል ዝቅ ብሎ ይገኛል። ጨረቃ በመሬት ዙሪያ በየ27.3 ቀናት አንድ ሙሉ ዙር ታጠናቅቃለች። ይህም መዞር ለጨረቃ በየ29.5 ቀናት የሞላና የጎደለ መመልክ መያዝ ዋና ምክንያት ነው።
የጨረቃ ከአንድ ጫፍ እስከ ሌላኛው ተቃራኒ ጫፍ (diameter) ያለው ርቀት 3,474 ኪሜ (2,159 ማይል) ሲሆን ከመሬት ተመሳሳይ አንድ አራተኛ (1/4 X የመሬት ዲያሜትር) በትንሽ ይበልጣል። የመሬትን አንድ አራተኛ ስፋት ሲኖራት ይዘቷ (volume) ግን የመሬትን ሁለት በመቶ (2%) ብቻ ነው። የጨረቃ ስበት [[የመሬት ስበት]]ን አስራ ሰባት በመቶ (17%) ጋር ይነጻፀራል።
ጨረቃ [[ጨረቃ ላይ መውጣት|የሰው ልጅ ያረፈባት]] ብቸኛዋ የጠፈር አካል ናት።