ከ«ኤኳዶር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
{{በደቡብ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች}} {{መዋቅር-መልክዐምድር}}
መስመር፡ 26፦
የኤኳዶር ሪፐብሊክ ዴሞክራስያዊ ሀገር ሲሆን በ[[ፕሬዚደንት]] ይመራል። ከደቡብ አሜሪካ 1000 ኪ/ሜ. ወደ ምዕራብ በፓሲፊክ የሚገኙት [[ጋላፓጎስ ደሴቶች]] የኤኳዶር ናቸው። በተጨማሪ ኤኳዶር በተለያዩ ተፈጥሮአዊ መናኸሪያዎች በጣም ብዙ ልዩ ልዩ የዱር አራዊትና አትክልት አሉበት፤ ለምሳሌ [[የጋላፓጎስ ታላላቅ ባሕር ኤሊ]]። እነዚህ ኤሊዎች ከአንድ መቶ ዓመት በላይ በሕይወት ሊኖሩ ይችላሉ፣ አንዱ ኤሊ እንኳን የ170 ዓመታት ዕድሜ ነበረው። የተፈጥሮአዊ መናኸሪያ መብቶች በኤኳዶር 2000 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት ተረጋግጠዋል።
 
ኤኳዶር ነፃነቱን በ[[1822]] ዓ.ም. አገኘ። ከዚያ በፊት በስፓኒሽ መንግሥት ቅኝ ግዛት ለረጅም ጊዜ ስትሆን ለአጭር ጊዜ ደግሞ በ[[ግራን ኮሎምቢያ ሪፐብሊክ]] ውስጥ ተጨመረ። የነፃነቱ ትግል ለረጅም ዘመን ቆይቶ ብዙ የሰው ልጅ ሕይወት ፈጅቶ ነበር። ከዚያ ጀምሮ አገሩ ወይም ሲቪል ወይም ወታደራዊ መንግሥታት በመፈራረቅ ኖሮዋል። ምጣኔ ሀብቱ የተለማ ነው። የኗሪ ብሔሮችና አፍሪካዊ-ኤኳዶራውያን ሕዝብ ሁለቱም በኤኳዶር ባሕል ላይ ተጽእኖ በመሆናቸው የአስተዋጽኦ ሚና አጫውተዋል።
 
{{በደቡብ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ አገሮች}}
{{መዋቅር-መልክዐምድር}}
 
[[መደብ:ኤኳዶር]]