ከ«መጽሐፍ ቅዱስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 2፦
 
== የመጽሐፍ ቅዱስ ምንነት ==
በ[[እንግሊዝኛ]] ቋንቋ የተለመደው «ባይብል» የሚለው ቃል ከጥንቱ [[የኮይነ ግሪክኛ]] ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ቃሉ የተገኘበት τὰ βιβλία /ታ ቢብሊያ/ የሚለው ሀረግ «መጽሐፍቱ» ወይም «ትንንሽ መጽሐፍት» ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። የዚሁም ቃል መነሻ ከግሪኩ ስም Βύβλος /ቢውብሎስ/ ([[ፓፒሩስ]] ወይም [[ቄጠማ]]፣ የ[[ወረቀት]] ተክል) ሲሆን ይሄ ቃል «ፓፒሩስ» ከተነገደበት ከተማ [[ጌባል]] / ቢውብሎስ ስም መጣ።
 
መጽሐፍ ቅዱስ ለ[[አይሁድና]] [[ክርስትና]] እምነት የእምነት መሰረት የሆኑ ትናንሽ መጽሐፍትን የያዘ አንድ ጥራዝ ነው። በተለምዶ «ብሉይ ኪዳን» በመባል የሚጠራውና በአይሁዳውያን በ24 እና በክርስቲያኖች በ39 መጽሐፍት የሚከፈለው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል በመጀመሪያ በአብዛኛው የተጻፈው በጥንታዊው የ[[ዕብራይስጥ]] ቋንቋ ሲሆን የተጻፉበት ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የተወሰኑ መቶ አመታት ቀደም ብሎ እንደሆነ ይነገራል። እነዚህን መጽሐፍት የጻፉት በወቅቱ የነበሩ የታመኑ አይሁዳውያን ወይም [[እስራኤላውያን]] ናቸው። የመጨረሻዎቹን 27 መጻሕፍት በግሪክኛ የጻፏቸው ክርስቲያኖች ሲሆኑ «አዲስ ኪዳን» በመባል በሰፊው ይታወቃሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ማስረጃም ሆነ በጣም ጥንታዊ የሆኑት ወጎች እንደሚጠቁሙት እነዚህ 66 መጻህፍት የተጻፉት ግብጽ ኃያል ከነበረችበት ጊዜ አንስቶ [[ሮም]] የዓለም ኃያል መንግስት እስከ ነበረችበት ዘመን ባሉት 1600 ዓመታት ውስጥ ነው።