ከ«አሰልበርህት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Removing Link GA template (handled by wikidata)
No edit summary
መስመር፡ 3፦
'''አ<u>ሰ</u>ልበርህት''' ([[552]] -[[608]] ዓ.ም.) ከ572 ወይም 582 ዓ.ም. አካባቢ እስከ 608 ዓ.ም. ድረስ የ[[ኬንት]] ንጉሥ ነበረ። ከ[[እንግላንድ|እንግሊዝ]] ንገስታትም መጀመርያው የተጠመቀ እሱ ነበር። ስለዚህ በ[[ሮማ ካቶሊክ]]፣ በ[[ምሥራቅ ኦርቶዶክስ]]ና በ[[አንግሊካን]] ሃይማኖቶች «ቅዱስ» ይባላል።
 
በ[[አንግሎ-ሳክሶን ዜና መዋዕል]] ዘንድ፣ እሱ አባቱን የኬንት ንጉሥ [[ኤዮርመንሪክ]]ን ተከተለ። የ[[ፍራንኮች]] ንጉሥ [[ቻሪበርት]] ልጅ [[ቤርታ]]ን አገባት። እሷ ክሪስቲያን ነበረችና ከዚህ የተነሣ ንጉሥ ተጠምቆ [[ክርስትና]] በእንግሊዝ ሕዝብ መካከል ይፋዊ ሆነ። [[አውግስጢኖስ ዘካንተርቡሪ]] ከ[[ሮማ]] በ[[588589]] ዓ.ም. ተልከው የእንግሊዝ ሕዝብ መጀመርያ ሊቀ ጳጳስ ሆኑ።
 
አ<u>ሰ</u>ልበርህት ከኬንት በላይ በዘመኑ መጨረሻ በሌሎች የእንግሊዝ ደሴት መንግሥታት በ[[ኤሴክስ]]ና [[ምሥራቅ ኤንግላ]] ላይ ገዥነት ነበረው። በእርሱ ተጽእኖ የኤሴክስ ንጉሥ [[ሳበርህት]] እና የምስራቅ ኤንግላ ንጉስ [[ራድዋልድ]] በ[[596]] ዓም ግድም ተጠመቁ።
 
በተጨማሪ በ[[594]] ዓ.ም. ንጉሥ አ<u>ሰ</u>ልበርህት ለአገሩ ሕገ መንግሥት አወጣ። ይህ ሕገ መንግሥት በ[[ሮማይስጥ]] ሳይሆን የተጻፈው በ[[ጥንታዊ እንግሊዝኛ]] ነበረ። በኋላ ዘመን የእንግሊዝ ንጉሥ [[ታላቁ አልፍሬድ]] ከዚህ ሕገ መንግሥት ወስደው የተሻሸለ ሕገ መንግሥት አወጡ።