ከ«ቦሊቪያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ቦሊቪያ''' በ[[ደቡብ አሜሪካ]] የሚገኝ አገር ነው። [[ዋና ከተማ]]ው [[ላፓዝ]] ነው።
 
11 ሚሊዮን ሕዝብ ያሉበትና ምንም የባሕር ጠረፍ የሌለው አገር ነው። በ[[2001]] ዓም ስሙ በይፋ ከ«'''የቦሊቪያ ሪፐብሊክ'''» ወደ «'''የቦሊቪያ ብዙ-ብሔሮች ሪፐብሊክ'''» ተቀየረ። ስሙ «ቦሊቪያ» ከ[[1817]] ዓም. ጀምሮ ስለአብዮታዊው አለቃ [[ሲሞን ቦሊቫር]] ክብር ደረሰ። ከ[[1974]] ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ኖርዋል።
 
ቦሊቪያ ከፍተኛ [[አንዴስ ተራሮች]] ሰንሰለት አለው፤ ላፓዝም ከማናቸውም የአለም ዋና ከተሞች ይልቅ ከባሕር ደረጃ በላይ ከፍተኛነት አለው። በጫፎቹም [[አመዳይ]] ይታያል። በዝቅተኛ ሥፍራዎች በጣም የሞቀ በረሃ አለ። እጅግ ብዙ የተለያዩ አትክልትና እንስሳት በቦሊቪያ ይገኛሉ።
 
አብዛኞቹ ሕዝቦች ከኗሪ ብሔሮች እንደ [[ቀቿ]]ና [[አይማራ]] ናቸው፤ ቋንቋዎቻቸው ሁሉ ከ[[እስፓንኛ]] ጋራ መደበኛ የስራ ቋንቋዎች ሁኔታ አላቸው።
 
ልዩ ልዩ የጨፈራና የዘፈን አይነቶች አሉ። አበሳሰሉ በተለይ [[ባቄላ]]፣ [[በቆሎ]]፣ [[ድንች]] ይጠቀማል። [[እግር ኳስ]] በተለይ የተወደደው እስፖርት ነው።
 
{{መዋቅር-መልክዐምድር}}