ከ«መጥምቁ ዮሐንስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

50 bytes added ፣ ከ3 ዓመታት በፊት
no edit summary
በኋላ ኢየሱስ ተዓምራት እየሠራ ዮሐንስ ተከታዮቹን ወደ ኢየሱስ ልኮ የምንጠብቀው መሲኅ ይህ ነው ወይ ብለው ጠየቁት። ተዓምራት መሥራቴን ንገረው ብሎ መለሳቸው። ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ገልጾ በ[[ትንቢተ ሚልክያስ]] እንደ ተነበየ የሚመጣው [[ኤልያስ]] ነው በማለት አስተማረ (ማቴ. ፲፩)። ሆኖም ዮሐንስ እራሱ ኤልያስ አይደለሁም ስላለ (ዮሐ ፩)፣ ሉቃስ ፩ እንደ ጻፈው በኤልያስ ኃይልና መንፈስ እንደ ተወለደ እንጂ የኤልያስ ነፍስ ትስብዕት ተመልሶ መሆኑ አይታመንም።
 
ዮሐንስ ደግሞ [[የሮሜ መንግሥት]] ደንበኛ-ንጉሥ [[ሄሮድያስ]]ን ገሰጸው። ሄሮድያስ የወንድሙን ሚስት ማግባቱ በ[[ሕገ ሙሴ]] ዘንድ ሕገ ወጥ መሆኑን አሳወቀው። ስለዚህ መቀያየም ሄሮድያስ ዮሐንስን በወህኒ አሠረው በኋላም በሴት ልጁ በ[[ሄሮድያዳ]] ምክር ራሱን አስቆረጠው።
 
ከዚያ ትንሽ በኋላ ኢየሱስ ተዓምራት ስለ መሥራቱ ዝነኛ ሲሆን፣ ሄሮድያስ እንደ መሰለው ዮሐንስ በትንሳኤ ተመልሷል ብሎ ገመተ። ሌሎችም ኢየሱስ እንደ ኤልያስ በትንሳኤ ተመልሷል ብለው ያስቡ ነበር (ማር. ፮፣ ማቴ. ፲፬)።
8,739

edits