ከ«ፖርቱጋል» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Tags: በንፋስ ስልክ Mobile app edit
Tags: በንፋስ ስልክ Mobile app edit
መስመር፡ 22፦
 
== ታሪክ ==
የፖርቱጋልየፖርቹጋል የጥንት ስም ሉዚታኒ ነው። በመጀመሪያም በአገሪቱ የነበሩት ሕዝቦች ሴልቶ ኢቤሪክ የሚባሉ የህንዶ-ኤውሮፓዊ ወገን ሆነው በኋላ ወደ ላቲንነት በልማድና በኑሮ በሃይማኖትም የተለወጡ ናቸው። የፖርቱጋል ሕዝብ በጀርመንና በኖርማንዲ በሮማውያንና በዐረቦች ሞሪ (ማውሪታኒ) ከሚባሉ በአፍሪካ ሰሜን ሕዝብና በዕብራውያንም የተቀያየጠ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ባንድነት ሰፊ ዘመን በሮማ መንግሥት ስለ ተገዙ በዘርም በልማድም አብዛኛውም ወደ ላቲንነት ተለውጠዋል። የሮማ መንግሥት ከወደቀ በኋላ በአምስተኛውና በስምንተኛው መቶ ዓመተ ምሕረት መካከል በነበረው ጊዜ ውስጥ እየተከታተለ ቢዚጎትና ስቤብ የሚባሉ የጀርመኖች ቀጥሎም የዐረቦች ወረራ ደርሶባቸዋል። በአስረኛው መቶ ዓ.ም. ግን አስቱሪዩ የሚባሉት የክርስቲያን ወገኖች እስላሞቹን አጥፍተው [[ሊስቦን]] ገብተው ገዥ ሆነው መንግሥታቸውን አቋቋሙ። ከዚያ ከ፲፪ እስከ ፲፬ መቶ ዓ.ም ድረስ ቤተ መንግሥቱን [[የቡርጎኝ ሥርወ መንግሥት]] ሲገዛው ቆይቶ በኋላ ሔቢዝ ለተባለው ቤተ መንግሥት አሳለፈው። በነዚህ መሪነት ጊዜ ይኸውም ማለት በ፲፬ኛውና በ፲፭ኛው መቶ ዓመተ ምሕረት ላይ የፖርቱጋል መንግሥት ከሌላው ሁሉ ይልቁንም በባሕርና በመርከብ ኃይል ሆነ።
 
በዚህ በ፲፭ኛው መቶ ዓ.ም. ላይ የ[[ቱርክ]]፣ የ[[መስኮብ]]፤ የ[[ጀርመን]]፤ የ[[እንግላንድ|እንግሊዝ]]፤ የ[[ፈረንሳይ]]ና የኤስፓኝ መንግሥታት እንደ ኃያላን መንግሥታት መቆጠራቸው አልቀረም። ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ የፖርቱጋል መንግሥት በሌላው እንኳን ባይሆን በመርከብና አገር በመያዝ ከቀሩት ይበልጥ ነበር። የቀሩት የኤውሮፓ መንግሥታት እዚያው ወሰናቸው ላይ ገዥነታቸውን ለማጽደቅ እርስ በርሳቸው ሲጨቃጨቁ የፖርቱጋል መንግሥት ግን ደኅና ደኅና መርከቦችን አዘጋጅቶ እየላከ ከመንግሥቱና ከኤውሮፓ ርቆ የሚገኘውን የ[[አሜሪካ]]ን፤ የ[[እስያ]]ን፤ የ[[አፍሪካ]]ን አገሮች ያስመረምር ነበር። መርማሪዎቹም እነ[[ቫስኮ ደጋማ]]፤ እነ[[ፔሬዝ]]፤ እነ[[አንድራድ]]፤ እነ[[ካብራል]] በመርከብ እየሄዱ ለመከላከል ጉልበት የሌለውንና በጠባዩ ሀብት ያለበትን አገር መርምረው ሲመለሱ መንግሥቱ ወታደር በመርከብ እየላከ ብዙ አገር ያዘ።