ከ«አዶልፍ ሂትለር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 31፦
 
በነበረው ዘረኛ አስተዳደሩ 6 ሚሊዮን የ[[አውሮፓ]] [[አይሁዶች]]ን እና የተለያዩ ሀገራት ህዝቦችን በገፍ አስጨርሷል።
 
በሂትለር ሥር የናዚዎች ፍልስፍና በ[[ሂንዱኢዝም]] እንደሚገኘው በዘር የተከፋፈለ [[ካስት ሲስተም]] መመሥረት አይነተኛ ነበር። «[[አርያኖች]]» የተባሉት ዘሮች በተለይም የ[[ጀርመናውያን]] ብሔሮች ከሁሉ ላዕላይነት እንዲገኙ አሠቡ። ይህ ዝብረት የተነሣ በ[[ርግ ቬዳ]] ዘንድ ወደ [[ሕንድ]] የወረሩት ነገዶች «አርያን» ስለ ተባሉ ነው፤ በጥንትም «[[አሪያና]]» የ[[አፍጋኒስታን]] አካባቢ ስም ነበር። በሂትለር እንደ ተዛበው ግን ታሪካዊ ባይሆንም የ«አርያኖች» ትርጓሜ ጀርመናውያን ብቻ ነበሩ፤ [[ስላቮች]] (በተለይ የ[[ሩስያ]]ና የ[[ፖሎኝ]] ሕዝቦች) ግን አርያኖች ሳይሆኑ እንደ ዝቅተኞች ተቆጠሩ። የሂትለር እብደት እየተራመደ በ1926 ዓም የ[[ሀንጋሪ]] ሕዝብ ደግሞ «አርያኖች» ተደረጉ፣ በ1928 ዓም የ[[ጃፓን]] ሕዝብ እንኳን በይፋ «አርያኖች» ተደረጉ፤ በ1934 ዓም የ[[ፊንላንድ]] ሕዝብ ወደ «አርያኖች» በሂትለር ዐዋጅ ተጨመሩ።
 
{{መዋቅር-ሰዎች}}