ከ«ክርስትና» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 5፦
በወንጌል መሠረት ኢየሱስ ከተሰቀለ በኋላ፣ እንደገና በሕይወት ከመቃብር ተነሥቶ ለደቂቀ መዝሙሮቹ እንደገና ታይቶ ከዚያ ወደ ሰማይ ዓረገ። ከዚህ በኋላ የ[[አይሁድ]] ጉባኤ [[ጴጥሮስ]]ንና ሌሎችን ሐዋርያት አስገረፋቸው፣ በኢየሱስ ስም እንዳያስተምሩ ከለከሉዋቸው። ጴጥሮስ ግን፦ «ከሰው ይልቅ ለ[[እግዚአብሔር]] ልንታዘዝ ይገባል» ብሎ መለሳቸው (የሐዋርያት ሥራ 5:29)።
 
[[የኢየሱስ ወንድም ያዕቆብ]] በ[[ኢየሩሳሌም]] የቤተክርስቲያን መጀመርያ መሪ ሆኑ። ከትንሽ በኋላ አይሁድ ያልሆኑ አሕዛብ ምዕመናን እንዲሆኑ ፈቀደ፣ [[ግርዘት]] ወይም ሌሎች የ[[ሕገ ሙሴ]] ከባድ ደንቦች አላስገደዳቸውም፣ ነገር ግን ከሕገ ሙሴ «ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደምም፣ ከተናቀም (ከመብላት)፣ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ» አስገደዳቸው። ከዚያ በተለይ በ[[ቅዱስ ጳውሎስ]] ስብከት ምክንያት ክርስትና ወንጌልም በቶሎ በ[[ሮማ መንግሥት]] እስከ ሮሜ ከተማ ድረስ ተስፋፋ። በተጨማሪ ልዩ ልዩ ሐዋርያት ወንጌሉን እስከ [[አክሱም መንግሥት]]ና እስከ [[ሕንድ]] ድረስ ቶሎ ወሰዱ።
 
በ41 ዓም የሮሜ ቄሣር [[ክላውዴዎስ]] «አይሁዶችን» ከሮሜ ከተማ ባስወጣቸው ዘመን፣ ብዙዎቹ ክርስቲያኖች እንደ ነበሩ ይመስላል። ክርስቲያኖች በሮሜ መንግሥት ብዙ ጊዜ እስከ [[303]] አም ድረስ ከቄሣሮቹ መከራዎች ቢያገኙም፣ ሃይማኖቱ ግን ምንጊዜም እየተበዛ ነበር።