ከ«ክርስትና» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 12፦
 
በ303 ዓም ክርስትና በሮሜ መንግሥት በ[[ጋሌሪዎስ]] ዘመን ሕጋዊ ሆነ። የሚቀጠለው ቄሳር [[ቆስጠንጢኖስ]] በ[[መጋቢት 10]] ቀን [[313]] ዓ.ም. በአዋጅ [[እሑድ]] ለሮማ ዜጎች ሁሉ ስለ ጣኦቱ [[አፖሎ]] የእረፍት ቀን እንዲሆንላቸው አዘዘ። በኋላ [[የንቅያ ጉባኤ]] ጠራ፣ በዚህ ጉባኤ በዚያን ጊዜ በዕብራይስጥ የተገኙት ጸሐፍት ብቻ (አዋልድ መጻሕፍት ሳይሆኑ) በ[[ብሉይ ኪዳን]] እንዲቀበሉ ተስማሙ። ከጥቂት ዓመታት በኋላ ቆስጠንጢኖስ እራሱ ተጠመቀ። ከዚያስ [[የሮሜ ቤተ ክርስቲያን]] የአይሁዶችን ብሉይ ኪዳን የሚያጸድቀው ምንም ቢሆንም፣ እንደ [[አስርቱ ቃላት]] [[ሰንበት]] በ[[ቅዳሜ]] የከበሩት ሁሉ እንደ «አይሁዳውያን» ሀራ ጤቆች በ[[አውሮጳ]] ይቆጠሩ ጀመር።
 
በዚህ ዘመን ያህል ብዙ ሌሎች ተወዳዳሪ ትምህርቶች በሮሜ መንግሥት ይሄዱ ነበር፣ በተለይም፦
 
*[[የአሪያን ቤተ ክርሥቲያን]] - በመሪያቸው [[አሪዩስ]] ትምህርት ኢየሱስ ነቢይ ነበረ እንጂ ወልድ (ከ[[ሥላሴ]] አንዱ) አልነበረም። ይህ ኢምነት በብዙ [[ጅርመናውያን]] ብሔሮች ለጊዜ ይቀበል ነበር።
*[[ሞንታኒስም]] - ነቢያቸው [[ሞንታኑስ]] «እኔ [[ፓራቅሌጦስ]] ([[መንፈስ ውዱስ]]) ነኝ» ብሎ ሰበከ።
*[[ኖስቲሲስም]] - ወይም ኖስቲኮች - አንዳንድ ሐሣዌ የተቆጠሩት ወንጌሎች ጽፈው ነበር፣ ሌሎች ትምህርቶች በምስጢር ጠበቁ።
*[[ማኒኪስም]] - እንደ ኖስቲሲሲም የመሰለ በምስጢር የተማረ የ[[ፋርስ]] ነቢይ [[ማኒ]] ሃይማኖት
*[[ሚትራይሲም]] - ሌላ የፋርስ ([[ዞራስተር]]) ጣኦት በ[[አረመኔ]]ዎች ዘመናዊ ሆነ፣ እሱ ደግሞ በምስጢር ይማር ነበር።
*የዱሮ አረመኔት ወዳጆች - ከ353 እስከ 356 ዓም ድረስ በቄሳሩ [[ዩሊያኖስ ከሐዲ]] ሥር ለአጭር ጊዜ ወደ ሥልጣን ተመለሱ፤ ጸረ-ክርስቲያን ትምህርቶች አስገቡ። ሆኖም ከበፊቱ ይልቅ ጨዋዎች ሆነው ነበር።
 
==ቋንቋዎች==