ከ«ስነፈሩ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
 
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Snofru Eg Mus Kairo 2002 b.jpg|thumb|300px|የስነፈሩ ሐውልት]]
'''ሆሩስ ነብመዓት ስነፈሩ''' (ምናልባት ከ2967-2955 ዓክልበ. ግድም) [[የግብጽ የቀድሞ ዘመነ መንግሥት]] ፈርዖን ነበረ። በኋላ በ[[ግሪክኛ]] የጻፈው [[ማኔጦን]] ስሙን «'''ሶሪስ'''» ሲለው፣ በአቆጣጠሩ የ፬ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያው ፈርዖን ይባላል። ንግሥቱ [[ኸተፕሐረስ]] ተባለች።
 
«[[ንጉሣዊ ዜና መዋዕል]]» በተባለው በተፈረሰው ጽላት «የፓሌርሞ ድንጋይ» በተባለው ክፍል፣ ለስነፈሩ ዘመን አንዳንድ ሳጥኖች ይታያሉ፤ የ፯ኛውና ፰ኛው የላሞች ቁጠራ ያመልክታሉ። ከ[[ኒነጨር]] ዘመን ጀምሮ የላሞች ቁጠራ በየሁለት ሳጥኖች እንደ ተደረገ ይታወቃል፤ እያንዳንዱ ሳጥን ፮ ወር ከሆነ የላሞች ቁጠራ በየዓመቱ ይደረግ ነበር ማለት ነው። ብዙዎች ሊቃውንት ግን የላሞች ቁጠራ በየ፪ ዓመታት ነበርና እያንዳንዱ ሳጥን ፩ አመት ይሆናል ባዮች ናቸው። በፓሌርሞ ድንጋይ በስነፈሩ ዘመን ግን ቁጠራው የተካሄደው በየሳጥኑ ወይም በየ፮ቱ ወር እንደ ሆነ ይመስላል። ለስነፈሩ ዘመን እስከ 24 የላሞች ቁጠራዎች ድረስ ስለ ተመዘገቡ፣ ምናልባት ፲፪ ዓመታት ብቻ ገዛ። በተለያዩ አስተሳስቦች ግን ከ24 እስከ 48 ዓመታት ድረስ ገዛ ወይም በ2600 ዓክልበ. እንደ ነገሠ ይገመታሉ።