ከ«ስነፈሩ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot: Changing %E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%88%AA%E1%8A%AB_%E1%89%B3%E1%88%AA%E1%8A%AD to
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Snofru Eg Mus Kairo 2002 b.jpg|thumb|300px|የስነፈሩ {{PAGENAME}}ሐውልት]]
'''{{PAGENAME}}ሆሩስ ነብመዓት ስነፈሩ''' ከ2967-2955 ዓክልበ. [[የግብጽ የቀድሞ ዘመነ መንግሥት]] ፈርዖን ነበረ። በኋላ በ[[ግሪክኛ]] የጻፈው [[ማኔጦን]] ስሙን «'''ሶሪስ'''» ሲለው፣ በአቆጣጠሩ የ፬ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያው ፈርዖን ይባላል። ንግሥቱ [[ኸተፕሐረስ]] ተባለች።
{{መዋቅር-ታሪክ}}
 
«[[ንጉሣዊ ዜና መዋዕል]]» በተባለው በተፈረሰው ጽላት «የፓሌርሞ ድንጋይ» በተባለው ክፍል፣ ለስነፈሩ ዘመን አንዳንድ ሳጥኖች ይታያሉ፤ የ፯ኛውና ፰ኛው የላሞች ቁጠራ ያመልክታሉ። ከ[[ኒነጨር]] ዘመን ጀምሮ የላሞች ቁጠራ በየሁለት ሳጥኖች እንደ ተደረገ ይታወቃል፤ እያንዳንዱ ሳጥን ፮ ወር ከሆነ የላሞች ቁጠራ በየዓመቱ ይደረግ ነበር ማለት ነው። ብዙዎች ሊቃውንት ግን የላሞች ቁጠራ በየ፪ ዓመታት ነበርና እያንዳንዱ ሳጥን ፩ አመት ይሆናል ባዮች ናቸው። በፓሌርሞ ድንጋይ በስነፈሩ ዘመን ግን ቁጠራው የተካሄደው በየሳጥኑ ወይም በየ፮ቱ ወር እንደ ሆነ ይመስላል። ለስነፈሩ ዘመን እስከ 24 የላሞች ቁጠራዎች ድረስ ስለ ተመዘገቡ፣ ምናልባት ፲፪ ዓመታት ብቻ ገዙ። በተለያዩ አስተሳስቦች ግን ከ24 እስከ 48 ዓመታት ድረስ ገዙ።
[[መደብ:ፈርዖን]]
[[ስዕል:Sneferu Wadi Maghara.png|300px|thumb|left|ስነፈሩ በዘመቻ ላይ]]
ስነፈሩ ሦስት ፒራሚዶች ሠሩ፤ እነርሱም [[ጠማማው ፒራሚድ]]፣ [[ቀይ ፒራሚድ]]ና [[የመይዱም ፒራሚድ]] ይባላሉ። ከዜና መዋዕሉ ስነፈሩ በደቡብና በምዕራብ እንደ ዘመተ፣ ብዙ ሺህ ምርከኞችና ከብቶችም ከዚያ እንዳመጣ ይታወቃል። የመርከብ ሃይል ደግሞ ይጠቀሳል፤ ፵ መርከቦች ከማዶ ባሕር የ[[አርዘ ሊባኖስ]] እንጨት እንዳመጡ ይዘገባል።
 
ስነፈሩ የ[[ካርቱሽ]] ምልክትና የ[[ሰረኽ]] ምልክት ነበሩት። ቀዳሚዎቹ [[ነፈርካ]]ና [[ሁኒሱት]] ሰረኽ ሳይኖራቸው ካርቱሽን ብቻ የጠቀሙት ነበር።
 
ስነፈሩ ከአንድ ሺህ ዓመታት በኋላ በ[[መካከለኛ መንግሥት]] እንደ መልካም ገዢ ይታወስ ነበር። ከዚያውም መካከለኛ መንግሥት ዘመን የታወቀ አንዳንድ ጽሑፍ በስነፈሩ ዘመን የተከሠተ ትርዒት ወይም ልብ ወለድ ታሪክ ያሳያል። እነርሱም [[የዌስትካር ፓፒሩስ]]ና ''[[የነፈርቲ ትንቢት]]'' ናቸው።
 
በዌስትካር ፓፒሩስ ባሉት ታሪኮች፣ አንዱ ታሪክ እንዲህ ይላል፦ ንጉሥ ስነፈሩ ሰልችቶት በሚኒስትሩ ምክር ሃያ ሴቶችን በመርከብ ላይ በሐይቅ ይወስዳል። በጉዞው ግን አንዲቱ መርከቡን የምትነዳው ዕንቁውን በሐይቅ ውስጥ አወደቀች። እንቁ እስከሚገኝ ድረስ ምኒስትሩ ሐይቁን በተዓምር አስለየው።
 
''የነፈርቲ ትንቢት'' በሚባል ድርሰት እንደገና ንጉሥ ስነፈሩ ሰልችቶት ሆኗል። አንዱን ቄስ ነፈርቲን ጠርቶ ለንጉሡ ትንቢት እንዲያውራ ይጠየቃል፣ ንጉሡም ያወራውን ትንቢት ጻፈ። ነቢዩ ለስነፈሩ፦ ወደፊት ሀገሩ አዲስ እንዲመሠረት ያስፈልጋል፤ እስከ መጨረሻውም ጥፍር ድረስ በሙሉ ይጠፋል፤ ማንም የሚጠብቃት አይተርፍምም፤ ሆኖም ወደፊት «አመኒ» የሚባል ንጉሥ ነግሦ መንግሥቱን አዲስ ይሠራዋል ብሎ ነበየለት። የዚህ ትውፊት መንስዔ በእርግጡ ሊታወቅ ባይቻለንም ፈርዖኑ «[[1 አመነምሃት]]» የሚለውን የዙፋን ስም መውሰዱን ለማጽደቅ እንደ ታሠበ ይሆናል፤ ስለዚህ ከእርሱ ዘመን (2002-1972 ዓክልበ.) መጻፉ ይታመናል።
 
የእስላም ታሪኮች ስለ ፈርዖኑ '''ሳውሪድ''' የጻፉት ደግሞ ስለ ስነፈሩ ወይም «ሶሪስ» ሳይሆን አይቀርም። በነርሱ ዘንድ የሳውሪድ ሕልም አስተርጓሚዎች የግብጽን ጥፋት በ[[ማየ አይኅ]] ነበዩለት። ይህን ትንቢት ሰምቶ ሦስት ሀረሞች አሠራ፤ የመንግሥቱ ጥበብ ሁሉ ለወደፊቱ ተቀርጸው እንዲይዙ ተሠሩ። መጀመርያው ሀረም እንደሚሉ ብዙ ውድ ድንጋይ ነበረበት፤ ሁለተኛው ሀረም ከአረንጓዴ ዕንቁ በተሠሩ ዕቃዎች ውስጥ የመንግሥቱ ሁሉ ታሪክ መጻሕፍት ነበሩበት፤ በሦስተኛውም የሃይማኖትና የሳይንስ መጻሕፍት ሁሉ እንዳገባ ይላሉ።
 
 
[[መደብ:የቀድሞ ዘመን ፈርዖኖች]]