ከ«ማኒኪስም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Manichaean clergymen, Khocho, Ruin alpha, 10th-11th century AD, wall painting - Ethnological Museum, Berlin - DSC01743.JPG|450px|thumb|የዊግር ብሔር ማኒኪስም ቄሳውንት ስዕል በፍርስራሽ ተገኝቶ]]
'''ማኒኪስም''' በ[[ፋርስ]] ነቢይ [[ማኒ]] (208-268 ዓም የኖረ) ትምህርቶች የተመሠረተ ሃይማኖት ነበር። ይህ አነስተኛ ሃይማኖት ለጊዜው በምዕራብ በ[[ሮሜ መንግሥት]]ና ወደ ምሥራቁ እስከ [[ቻይና]] ድረሥ ይስፋፋ ነበር። በምዕራብ፣ ተከታዮቹ እንደ ክርስቲያኖች ለማስመሰል ጣሩ፣ በምሥራቁም እንደ ቡዲስቶች አስመሰሉ። ስለዚህ ብዙ ጊዜ በድብቅ ያስተማሩት እምነት ነበር፤ ከሌሎቹ ሃይማኖቶችም ዘንድ ብዙ ጊዜ ማሳደድ ያገኙ ነበር። በጎ በክፋት ላይ ማሽነፉን የካደ ሃይማኖት ነበር። በአሁኑ [[ሞንጎሊያ]] አካባቢ በተገኘው በ[[ዊግር ኻጋናት]] መንግሥት ከ754 እስከ 832 ዓም ድረስ፣ ማኒኪስም [[የመንግሥት ሃይማኖት]] ነበር።
 
ነቢዩ ማኒ አምስት መጻሕፍት በ[[አራማይስጥ]]ና አንድ መጽሐፍ በ[[መካከለኛ ፋርስኛ]] እንደ ጻፈ ተባለ፤ ሌሎች ግን የሰው ጽሑፍ እንደ ራሱ ያሳለፈ ሌባ አሉት። ከነዚህ መጻሕፍት ከፍርስራሽ በቀር አሁን በሙሉ አይታወቁም። ከ፭ቱ አራማይስጥ መጻሕፍት ግን አንዱ ትኩረት የሚስብ «[[የረጃጅሞች መጽሐፍ]]» ደግሞ ከማኒ ዘመን በፊት በ[[ቁምራን ብራናዎች]] መካከል (100 ዓክልበ - 50 ዓም) በፍርስራሽ ተገኝቷል። የማኒ ድርሰት አለመሆኑን ከማስረዳት በላይ፣ ይህ ጽሑፍ ከ[[መጽሐፈ ሄኖክ]] ተመሳሳይነት አለው፣ ሆኖም በ[[ማየ አይኅ]] ውስጥ ከጠፉት ክፉ ዘሮች አስተያየት ይነገራል።
 
{{መዋቅር-ሃይማኖት}}