ከ«ዶናልድ ጆን ትራምፕ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 6፦
እ.ኤ.አ. በ2000 ላይ፣ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት ተወዳድሮ ሁለት የ[[ሪፎርም ፓርቲ]] እጩነትን አሸንፎ ነበር። በእ.ኤ.አ. ጁን 16 2015 ላይ ደግሞ ለፕሬዚደንትነት እንደሚወዳደር አሳወቀ። ይህን ጊዜ ግን የሪፐብሊካን ፓርቲን በመወከል ነው። በስደት፣ በነፃ ገበያ እና በጦር ጣልቃ ገብነት ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ታዋቂ ሆኗል። በእነኚህ አነጋጋሪ አስተያየቶቹ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የተቃውሞ እና የድጋፍ ሰልፎች እንዲካሄዱ ምክንያት ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ሜይ 2016 ከሪፐብሊካን የፕሬዚደንታዊ እጩነት ውድድሮች ውስጥ 28ቱን ውድድሮች ካሸነፈ በኋላ እና የተቀሩት ተቀናቃኞቹ እነ [[ቴድ ክሩዝ]] እና [[ጆን ካሲች]] ከውድድሩ ራሳቸውን ስላገለሉ፥ ትራምፕ ለሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ መሆኑ የተረጋገጠ ሆኗል። በእ.ኤ.አ. ከጁላይ 18 እስከ 21 በተካሄደው የ2016ቱ የሪፐብሊካኖች አገር አቀፍ ስብሰባ ላይ እጩ መሆኑ በይፋ ታወጀ። በእ.ኤ.አ. ኖቬምበር 8 ቀን 2016 ላይ የፕሬዚደንትነት ምርጫውን አሸነፈ። ማሸነፉንም ተከትሎ ብዙ የተቃውሞ ሠልፎች በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች ውስጥ ተካሂዶ ነበር። በ70 ዓመቱም ሥልጣን ላይ በመውጣቱ ከእርሱ በፊት ከነበሩት ፕሬዚደንቶች ሁሉ በዕድሜ ትልቁ ያደርገዋል።
 
== ቀደምት የሕይወት ታሪክ ==
ዶናልድ ትራምፕ ከ[[ኒው ዮርክ]] ከአምስቱ ቀጠናዎች አንዱ በሆነው በ[[ክዊንስ]] በእ.ኤ.አ. ጁን 14 1946 ተወለደ። ለእናቱ ሜሪ አን እና ለአባቱ ፍሬድ ትራምፕ ከአምስት ልጆች መሃል አራተኛው ልጃቸው ነበር። እናቱ የተወለደችው በ[[ስኮትላንድ]] [[ሉዊስ ኤንድ ሃሪስ]] ደሴት ላይ [[ቶንግ]] በተባለው ስፍራ ነው። በእ.ኤ.አ. 1930 በ18 ዓመቷ ዩናይትድ ስቴትስን ጎበኘች እናም ከፍሬድ ትራምፕ ጋር ተገናኘች። በእ.ኤ.አ. 1936 ትዳር ይዘው በጃማይካ ኢስቴትስ ክዊንስ መኖር ጀመሩ። በዚህም ስፍራ ፍሬድ ትራምፕ ታላቅ የሪል ኢስቴት ገንቢ ሆኖ ነበር። ዶናልድ ትራምፕ፥ ሮበርት የተባለ አንድ ወንድም፣ ሜሪአን እና ኤሊዛቤት የተባሉ ሁለት እህቶች አሉት። ፍሬድ ጁኒየር የተባለ ወንድሙ ደግሞ ከአልኮል ሱስ ጋር በተያያዘ ምክንያት ሕይወቱ አልፏል ፤ ይህም ከአልኮሆል መጠጥ እና ከትምባሆ እንዲታቀብ እንዳደረገውም ዶናልድ ትራምፕ ይናገራል።