ከ«የኢትዮጵያና አዳል ጦርነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 9፦
ስለ አዳል ሱልጣኔት በትንሹ (ከ1415- 1577 ዓ.ል.)
BY;- NORA HAMED
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
 
 
አስራ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ሰለሞናዊ ነጋሲ የነበረው ወጣቱ አጼ ዳዊት በ1413 ዓ.ል. በአጠገቡ በነበረው የኢፋት ሱልጣኔት ላይ ሀይለኛ ጥቃት ከፈተ። የሱልጣኔቱ ገዠ የነበረውን ሱልጣን ሰዓደዲንን በዜይላ ከተማ ከገደለው በኋላም ኢፋትን ከአጼው ግዛተ መንግስት ጋር ቀላቀለው። ሆኖም አጼ ዳዊት በቁጥጥር ስር ካዋለው የኢፋት ግዛት በሙሉ ሀይሉ ለመግዛት የቻለው ከአዋሽ ወንዝ በስተምዕራብ ያለውን ብቻ ነው። ከወንዙ በስተ-ምስራቅ ያለውና እስከ ዘይላ ድረስ የተንጣለለው ምድር ወዲያውኑ ነበር ከእጁ ያፈተለከው። አባታቸው በዘይላ ሲገደል በስደተኝነት ወደ የመን የሸሹት አስራ አንዱ የሰዓደዲን ልጆች በ1415 ዓ.ል. ከስደት ተመልሰው በምስራቃዊው የኢፋት ግዛት ላይ አዲስ ሱልጣኔት መሰረቱ። ዋና ከተማቸውን ከሀረር አጠገብ በነበረችውና “ደከር” በምትባለው መሬት ላይ ቆረቆሩ። ዳግማዊ ሰብረዲን የሚባለውን የሰዓደዲን ልጅ በወላስማው ወንበር ላይ ካስቀመጡ በኋላ ህልውናቸውን በይፋ አበሰሩ። ከእንግዲህ ወዲያም ለማንም እንደማይገብሩና ሀገራቸውንም ከጥቃት እንደሚከላከሉ በይፋ አወጁ። ለአዲሱ ሱልጣኔትም “አዳል” የሚል ስያሜ ሰጡ።
 
Line 15 ⟶ 17:
የአዳል ሱልጣኔት የተወለደው ከላይ በተገለጸው ሁኔታ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ ከታዩት ሱልጣኔታዊ መንግስታት ውስጥ እጅግ-ገናና ስም የነበረው ይኸው የአዳል ሱልጣኔት ነው። ይህ ሱልጣኔታዊ መንግስት የኢትዮጵያን ታሪክ ለመቀየር የቻሉትን እንደ አሚር ማሕፉዝ ሙሐመድ፣ ኢማም አሕመድ ኢብራሂም አል-ጛዚ (አሕመድ ግራኝ) እና አሚር ኑር ሙጃሂድን የመሳሰሉ ታላላቅ መሪዎችን አፍርቷል። በርካታ ጸሀፍት ስለርሱ ከትበዋል። በልዩ ልዩ ህዝቦች ስነ-ቃል ውስጥ እስካሁን ድረስ ያልቀዘቀዙ ወጎች እንዲከሰቱ ምክንያት ሆኗል። አሁንም ስለርሱ ታሪክ የሚያወሱ በርካታ ድርሳናት እየተጻፉ ነው። ከዚህ እልፍ ሲል ደግሞ “አዳል” የሚለው የሱልጣኔቱ መጠሪያ የሰው ስም ሆኖ ይገኛል። በተለይ የሚያስደንቀው ደግሞ በዚህ ስያሜ የሚጠሩት ከሙስሊሞች ይልቅ ክርስቲያኖች መሆናቸው ነው። ለዚህም ብዙዎች የሚያስታውሷቸውን እንደ ጋሻው አዳል፣ ዘሪሁን አዳልና ራስ አዳል ተሰማ (በኋላ ንጉስ ተክለ ሀይማኖት ተብለው በጎጃም የተሾሙት) የመሳሰሉ ስሞችን መጥቀስ ይቻላል። በሌላ በኩል የሰለሞናዊው አጼ መንግስት ከአዳል ሱልጣኔት ጋር በጦር ሜዳ እየተላለቀ ከነበሩት ክፍለ ጦሮች መካከል አንዱን “አዳል መብረቅ” በሚል ስያሜ ይጠራው ነበር። እርሱም በበኩሉ አዳልን እየጠላው ያደንቀው ነበር ማለት ነው። ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው የሱልጣኔቱ ስመ-ገናናት በሁሉም ወገኖችና ህዝቦች ዘንድ ተደናቂነት ነበረው።
 
“አዳል” የሚለው ስም ምንጭ በትክክል አይታወቅም። አንዳንዶች “አዳ አሊ” (በአፋርኛ የአሊ ቤት ለማለት ነው) ከሚል ስርወ-ቃል እንደተገኘ ይገምታሉ። አንዳንዶች ደግሞ ጥንት የሀረር አሚር ከነበረው “አሚር ኢዳል” ስም የተገኘ እንደሆነ ይናገራሉ። ሆኖም ግን እርግጠኛው ነገር ከአፋርኛ የተገኘ እንደሆነ ይናገራሉክርክር የለውም ። የስያሜው ጥንታዊነት ግን በብዙ ምንጮች የተረጋገጠ ነው። ለምሳሌ አቡ ፈድሉላህ አል-ዑመሪ የሚባለው ግብጻዊ ምሁር በ1349 ዓ.ል. በጻፈውና “መሳሊከል አብሳር ፊ መማሊከል መሳር” በሚባለው ዝነኛ መጽሀፍ ውስጥ አዳል ተደጋግሞ የተጠቀሰ ስም ነው።
 
ከ1415 ዓ.ል. በፊት “አዳል” በኢፋት ሱልጣኔት ስር የነበረ የአንድ አውራጃ ስም ነበር። የአጼ ዓምደ ጽዮን (1314-1344 ዓ.ል) ዜና መዋዕል ዘጋቢ እንደጻፈው ከሆነ የዚህ አውራጃ ዋና ከተማ “ተላቅ” የሚል ስያሜ ነበረው። “ፉቱሕ አል- ሐበሽ” የተሰኘው መጽሀፍ ደራሲ ሱልጣኔቱን “አዳል” ከሚለው ስም በተጨማሪ “በሪ ሰዓደዲን” (የሰዓደዲን በር) እና “ዳር ሰዓደዲን” (የሰዓደዲን ሀገር) በሚሉ ስሞችም ይጠራዋል። ይህም ሱልጣኔቱን ያቋቋሙት የሱልጣን ሰዓደዲን ልጆች እንደ ሰማዕት በሚያዩት አባታቸው ስም ያወጡለት የክብር ስያሜ ነው። የግዕዝ ምንጮችም ስለኢትዮጵያ ኢስላማዊ ግዛቶች በሚጽፉበት ጊዜ “አዳል” የሚለውን ስም በእጅጉ ይደጋግሙታል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ስያሜው ከግዛት መጠሪያነት ያልፍና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሙሉ በወል የሚጠሩበት ስም ሆኖ ይገኛል። በኢትዮጵያ ምድር ከታዩት ሱልጣኔቶች እምብዛም በማያደናግር ሁኔታ ታሪኩ የተጻፈለት “አዳል” ብቻ ነው (ከአንዳንድ አሻሚ ነጥቦች በስተቀር)። እጅግ ሰፊ ግዛት የሚያካልለውም “አዳል” ነው። ከሀረር ከተማ ታሪክ ጋር በእጅጉ የተቆራኘውም “አዳል” ነው።