ከ«ሰብታ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ሰብታ''' በ''[[ኦሪት ዘፍጥረት]]'' ምዕ. 10 መሠረት የ[[ኩሽ (የካም ልጅ)|ኩሽ]] ሦስተኛ ልጅ ነበር።
 
በአንዳንድ ሊቃውንት ዘንድ፣ ሰብታ በ[[አረቢያ]] ዳርቻ (በ[[ቀይ ባህር]] ላይ) ይገኝ የነበረው [[ሳቦታ]] በተባለ ሥፍራ ሰፈረበት። ይህ ሳቦታ የ[[ሃስረሞት]] ዋና ከተማ ነበረች። ሌላ ሊቃውንት እንደሚያስቡት፣ በ[[ሞሮኮ]] ዳርቻ (በ[[ጂብራልታር ወሽመጥ]] ላይ) የሚገኘው [[ሴውታ]] የሰብታ ልጆች መኖራያ ይሆናል። በዚህ ሃሣብ ልጆቹ በሳህራ በረሃ ሠፈሩ።
 
ዳሩ ግን በ[[1ኛው ክፍለ ዘመን]] የጻፈው አይሁዳዊ መምህር [[ፍላቭዩስ ዮሴፉስ]] እንዳለው፣ «የሰብታ ልጆች [[ግሪክ (ሕዝብ)|ግሪኮች]] አሁን አስታቦራውያን የሚሏቸው ናቸው።» በጥንት «አስታቦራስ» ማለት አሁን በ[[ሱዳን]]ና በ[[ኢትዮጵያ]] [[አትባራ ወንዝ]] የሚባል ስለ ሆነ፣ የሰብታ ኩሽ ልጆች በዚያ እንደ ሰፈሩ አመለከተ። በልማዳዊ መዝገብ የተወረሰው [[የኢትዮጵያ ነገሥታት|የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝር]] ደግሞ ሰብታ ለ30 አመታት በ[[ኩሽ መንግሥት]] ላይ ንጉሥ ሆነ ይላል፤ ይህም ከ[[ካም]]፣ ኩሽና ሃባሢ በኋላ ሲሆን አመቶቹ ሲቆጠር ምናልባት ከ2264 እስከ 2234 ዓክልበ. ይሆናል። [[አባ ጎርጎርዮስ]] እንዳሉ የሰብታ ሌላ ስም «አቢሲ» ስለ ሆነ [[ሀበሻ]] የሚለው ስም ከዚህ ነው። በነገሥታት ዝርዝሩ ግን ሰብታ የሀባሢ ተከታይ ይባላል።
 
በ[[አኒዩስ ቪተርቦ]] ባሳተመ በአንዱ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ይህ የኩሽ ልጅ ሰብታ (ወይም «ሳባትዮስ ሳጋ» ተብሎ) ከዚያ ዘመን በፊት በ[[ሳካ]]ዎች ([[እስኩቴስ]]) በ[[አርሜኒያ]]ና [[ባክትሪያ]] ላይ የነገሠ ሲሆን፣ የ[[መስጴጦምያ]] ንጉሥ [[ኒኑስ]] ከዚያ አባረረው። ከዚያም ዘመን በኋላ ከአፍሪካ ወደ [[ጣልያን]] ሂዶ በዚያው አገር ደቡብ ክፍል ነገሠ። ከዚህ በላይ [[ሳጉንቶ]] ከተማ በ[[እስፓንያ]] እንደ መሠረተ የሚል ልማድ አለ።
 
ሌላ ሊቃውንት እንደሚያስቡት፣ በ[[ሞሮኮ]] ዳርቻ (በ[[ጂብራልታር ወሽመጥ]] ላይ) የሚገኘው [[ሴውታ]] የሰብታ ልጆች መኖራያ ይሆናል። ይህም የሴውታ ስያሜ በ[[አረብኛ]] «ሰብታ» ስለ ሆነ ነው። ሆኖም የአረብኛው ከተማው ስም «ሰብታ» የመጣ ከ[[ሮማይስጥ]] ስያሜው «ሰፕታ ፍራትሬስ» (ማለት «ሰባት ወንድሞች»፣ ባካባቢው ስላሉ ፯ ኮረብቶች) ሲሆን፣ ከኩሽ ልጅ ሰብታ ጋር ግንኙነት እንዳለው አይመስልም።
 
{{S-start}}